1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ድህረ ምርጫ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ቃለ መጠይቅ

ረቡዕ፣ ግንቦት 26 2018

የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል እንደ ክልል ከተዋቀረ ወዲህ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንደ ክልል ምርጫ ሲከናወንበት ። አራት ብዝኃ ከተሞችን አካትቶ በተዋቀረው በዚህ ክልል ታምራት ዲንሳ የፕሬዚደንቱ እና የፖለቲካ መቀመጫ በኾነው የከፋ ቦንጋ ከተማ ዛሬ ይገኛል ።

https://p.dw.com/p/5EoEs
የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል እንደ ክልል ከተዋቀረ ወዲህ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንደ ክልል ምርጫ ሲከናወንበት
የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል እንደ ክልል ከተዋቀረ ወዲህ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንደ ክልል ምርጫ ሲከናወንበት ምስል፦ Tamirat Dinssa/DW

ድህረ ምርጫ ቃለ መጠይቅ ከቦንጋ

የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል  እንደ ክልል ከተዋቀረ ወዲህ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንደ ክልል ምርጫ ሲከናወንበት ። አራት ብዝኃ ከተሞችን አካትቶ በተዋቀረው በዚህ ክልል ታምራት ዲንሳ የፕሬዚደንቱ እና የፖለቲካ መቀመጫ በኾነው የከፋ  ቦንጋ ከተማ ዛሬ ይገኛል ።  22 የምርጫ ክልሎች ያሉት የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ  171 የክልል ወንበሮች አሉት ። ከ1780 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች አማካኝነት ነው በክልሉ የዘንድሮው አገር አቀፍ ምርጫ የተከናወነው ። ትናንት  በጅማ እና አጋሮ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን የተመለከተው ባልደረባችን ታምራት ዛሬ ደግሞ እስከ ቦንጋ ከተማ ድረስ ያየውን፣ ያስተዋለውን ያካፍለናል ።

ሲመሠረት አራት ብዝኃ ከተሞችን በማካተት የተዋቀረው የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል  የቦንጋ ከተማ ከኦሮሚያ ክልል  ጅማ ከተማ 105 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ይገኛል ። 

አንጻራዊ ሰላም ያለባቸው ተብለው ከሚጠቀሱ ክልሎች መካከል አንዱ እና ተጠቃሽ ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ነው ያለው ታምራት የከፋው ቦንጋ ከተማ እስኪደርሱ ድረስ «ምንም አይነት ችግር» እንዳልገጠማቸው ገልጧል ።

ጥቅጥቅ ደኖች በብዛት በሚገኙበት አረንጓዴያማው መስመር ላይ እነ ታምራት ያነጋገሯቸው ሰዎች  «አካባቢው ፀጥታው የተጠበቀ» መኾኑን እንደነገሯቸው ገልጧል ። የአካባቢው ሰው እንደማንኛውም ሰው ለውጥ እንደሚሻ፣ «የኑሮ ውድነቱ እንዲቀረፍ፣ የዋጋ ግሽበት ወደ ቦታው እንዲመለስለት» ምኞታቸው መኾኑን መግለጣቸውንም አክሎ ዘግቧል ።  

ከታምራት ዲንሳ ጋር የተደረገውን ቃለ-መጠይቅ በድምፅ ማገናኛው በኩል ማድመጥ ይቻላል

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ

#ምርጫ2018  #EthiopiaElection2026