የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፦ የሕዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች አባላት ጠቅላላ ምርጫን በየ5 ዓመቱ በመላ አገሪቱ በተመሳሳይ ጊዜ ያካሂዳል። ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ ሲያገኝ በተለያየ ጊዜ እንዲካሄድ ሊያደርግ ይችላል፡፡