1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እና በሂደት የሚያስከትለው ጫና

ሰለሞን ሙጬ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 5 2018

ወደብ ተከራይታና ነዳጅ ከዓለም ገበያ ገዝታ የምታስገባው ኢትዮጵያ በአሜሪካ፣ እስራኤል - ኢራን ጦርነት ምክንያት ኢኮኖሚዋ በብርቱ ሊፈተን እንደሚችል በነዳጅ ማቅረብ ዘርፍ የተሠማሩ ሰው ሥጋታቸውን ገለፁ። ጦርነቱ "የዓለም የንግድ ሥርዓትን አዛብቷል" ያሉ አንድ ተንታኝ በበኩላቸዉ"ጦርነቱ ቢቋጭ እንኳን ጉዳቱ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ነው" ብለዋል።

https://p.dw.com/p/5C673
ፎቶ ከማኅደር፤ የጅቡቲ ወደብ
ፎቶ ከማኅደር፤ የጅቡቲ ወደብ ምስል፦ Solomon Muchie/DW

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እና በሂደት የሚያስከትለው ጫና

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እና በሂደት የሚያስከትለው ጫና

ወደብ ተከራይታ እና ነዳጅ ከዓለም ገበያ ገዝታ የምታስገባው ኢትዮጵያ በአሜሪካ፣ እስራኤል - ኢራን ጦርነት ምክንያት በቀጣይ ኢኮኖሚዋ በብርቱ ሊፈተን እንደሚችል በነዳጅ ማቅረብ ዘርፍ የተሠማሩ ሰው ሥጋታቸውን ገለፁ። ጦርነቱ "የዓለም የንግድ ሥርዓትን አዛብቷል" ያሉ አንድ የዓለም አቅፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ተንታኝ ደግሞ "ጦርነቱ ቢቋጭ እንኳን ውጤቱ የሚያስከትለው ጉዳት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ነው" ብለዋል።

በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሀገራት ሊኖር በሚችል "የማዳበርያ እና የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት" በቀጣይ የምርት ዘመን ሥራቸው ጉልህ ተጽዕኖ ሊጋረጥባቸው እንደሚችል ባለሙያው ጠቅሰዋል።

በዓለም መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴ እና ልውውጥ ላይ ተጨባጭ ጉዳት ለማድረስ ጥቂት ጊዜ የወሰደው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ከተጀመረ 45 ቀናት ሆኖታል። ጦርነቱ እስካሁን ያደረሰውን እና ወደፊት የሚኖረውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት በሚመለከት አስተያየት የጠየቅናቸው የዲፕሎማሲ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተንታኝ በጥቅል አገላለጽ "የዓለም የንግድ ሥርዓትን አዛብቷል" ብለዋል።

በጅቡቲ የአሽከርካሪዎች መቆም - የጉዳቱ የንዱ ማሳያ

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከጅቡቲ ነዳጅ ለማምጣት ከኢትዮጵያ የሄዱ እና በዚያው ከቆሙ እስከ ሁለት ወር የሆናቸው ነዳጅ ጫኝ አሽከርካሪዎች፣ መቆማቸው አንድ ችግር ቢሆንም፣ በየ ዕለቱ ያመላልሱት የነበረው የናፍታ መጠን በከፍተኛ መጠን መቀነስ ሌላኝው ማሳያ ነው። የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሸከርካሪዎች ማሕበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ ይህንን ፈታኝ ችግር ለመቅረፍ እንዲቻል በጅቡቲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር ባለፈው ሳምንት ውይይት መደረጉን ነግረውናል።

ኢትዮጵያ የነዳጅ ምርት የምታስገባው አሁን የጦርነቱ ቀጥታም ይሁን ተዘዋዋሪ ጉዳት ሰለባ ከሆኑ ሀገራት ነው። በዓመት ለዚሁ ሸቀጥ መግዣ ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ፈሰስ ታደርጋለች። እንዲያም ሆኖ ይህንን ቀውስ ተከትሎ በዘርፉ ሙስናና ሌብነት ተበራክቷል የሚሉት አቶ ሰለሞን የዚህ ድምር ውጤት በቀጣይ የሀገሪቱ ምጣኔ ሐብት ላይ ብርቱ ፈተና መደቀኑ አይቀርም የሚል እምነት አላቸው። 

ፎቶ ከማኅደር፤ አዲስ አበባ ከተማ
ፎቶ ከማኅደር፤ አዲስ አበባ ከተማ ምስል፦ Eshete Bekele/DW

ቀጣይ የግብርና ምርት ላይ ምን ተጽዕኖ ይኖር ይሆን? 

ኢኮኖሚዋ ግብርናን መሠረት ያደረገው ኢትዮጵያ ከነዳጅባለፈ የአፈር ማዳበርያ እና ምርጥ ዘር ከውጪ ታስገባለች። ይህ ጦርነት ያስከተለው ምስቅልቅል በሀገሪቱ የቀጣይ ምርት ዘመን ሥራ ላይ ተፅእኖ መፍጠሩ አይቀርም። ተስፋ አሳይቶ ያለውጤት የቀረው የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራን ድርድር በሂደት ጦርነቱን የመቋጨት ዕድል ቢኖረው እንኳን ያስከተለው ውድመት የሚያስከትለው ጉዳት ግን ለረጅም ጊዜ የሚቆይ መሆኑን የአለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ተንታኙ አብራርተዋል።  

መንግሥት ነዳጅን ባሚመለከት የወሰደው ርምጃ

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት፣ የነዳጅና ኢነርጂ እንዱሁም የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶችን ያካተተ ነዳጅ በማዕከላዊነት የሚመራበት "የኹኔታዎች መከታተያ ልዩ ክፍል" መቋቋሙን እና እና ነዳጅ ቅድሚያ ማግኘት ያለባቸውን ተቋማት መለየቱን ማስታወቁ ይታወሳል። ይህ ጦርነት ያደረሰው የሸቀጦች እና የአገልግሎቶች ዋጋ መናር ከወዲሁ ኢትዮጵያ ውስጥ አሳሳቢ በሚባል ኹኔታ እየተስተዋለ ነው።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ