ውይይት፦ በ«እናት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት»
ረቡዕ፣ ኅዳር 17 2012
ማስታወቂያ
የሀገር ጉዳይ ያገባናል በሚሉ ወጣቶች ስብስብ የተመሰረተው «እናት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት» ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሆቴል ውስጥ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መክሯል። ወጣት ኢትዮጵያውያኑ ምክር አዘሉን ውይይት ያከናወኑት «ለችግር ተጋላጭ የኾነ ማኅበረሰብን ማገዝ» በሚል መርኅ ነበር። ለሚቀጥለው ትውልድ መልካም አርዓያን ለማስተላለፍ በማሰብም ታዋቂ አረጋውያንን እና ምሑራንን አወያይተዋል። የውይይቱ ዋነኛ ዓላማ የሰላም ጉባኤ ማከናወን መኾኑ በውይይቱ ወቅት ተገልጧል። በጉባኤው የታደመው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ- ጊዮርጊስ በታዳሚያን መካከል የተሰጡ የተለያዩ አስተያየቶችን በማሰባሰብ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ- ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ተስፋለም ወልደየስ