አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መንግሥት የጤና ባለሙያዎችን “እስር” እና የሚፈጽማቸውን “የኃይል እርምጃዎች” እንዲያቆም የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አሳሰበ።
የኢትዮጵያ መንግሥት የጤና ባለሙያዎችን “እስር” እና የሚፈጽማቸውን “የኃይል እርምጃዎች” እንዲያቆም የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አሳሰበ። መንግሥት “የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ በመገንዘብ እውቅና መስጠት” እንደሚገባው ያሳሰበው ፓርቲው ፓርቲው ትላንት ሐሙስ ባወጣው መግለጫ “የማጣጣል እና የፍረጃ ንግግሮች” ሊያቆም ይገባል ብሏል።
ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን፣ ፍትሃዊ ክፍያን እና ህዝቡን ለማገልገል የሚያስፈልጉ የሕክምና ግብዓቶችን የማግኘት ጉዳዮችን አስመልክቶ የመብት ጥያቄ ላነሱ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ኦፌኮ አጋርነቱን ገልጿል። ባለሙያዎቹ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች አስቸኳይ እና ህጋዊ ናቸው ነው ያለው ኦፌኮ መንግሥት የጤና ባለሙያዎችን እንቅስቃሴና ጥያቄያቸውን ያለአግባብ ድብቅ የፖለቲካ አላማ እንዳለው በማስመሰል ህጋዊነቱን ለማጣጣል የሚያደርገው ጥረት እንዳሳሰበው በማሳወቅ እንዲቆም እንጠይቃለንም ብሏል።
የኦፌኮ የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ፓርቲው አጋርነት ያሳየበትን መግለጫ ያወጣው “በግል አሊያም ውጪ ወጥተው መታከም የማይችሉ በአነስተኛ ወጪ ብቻ መታከም የሚችሉ ማህበረሰባችን ማዕከል በማድረግ ነው” መሆኑን ተናግረዋል። መንግሥት ቅሬታዎችን ለመፍታት ከጤና ባለሙያዎች ተወካዮች ጋር ሁሉን አቀፍ እና ግልጽ ውይይቶች ማድረግ እንዳለበት ኦፌኮ አሳስቧል።
ለሚሊዮኖች ሊሰጥ የሚችል የዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እርዳታ እየተበላሸ ነው
በተለያዩ መጋዘኖች ውስጥ የተከማቸ ከ60 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እርዳታ እየተበላሸ ነው ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናገሩ። ሮይተርስ የዜና ወኪል የጠቀሳቸው ምንጮቹ እንዳሉት፣የተከማቸው የምግብ እርዳታ ቁጥራቸው 3.5 ሚሊዮን ለሚደርስ ሰዎች ለአንድ ወር የሚበቃ የምግብ ራሽን ሊሆን የሚችል ነው። ዜና አገልግሎቱ እንደዘገበው የምግብ እርዳታው በመበላሸት ላይ ያለው ዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እርዳታ ማከፋፈል በማቋረጧ ነው። ሮይተርስ ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ያላቸው በስም ያልጠቀሳቸው አምስት ሰዎች በአሜሪካን እርዳታ መቋረጥ ምክንያት የተከማቸው የምግብ እርዳታ ምናልባትም ከጥቅም ውጭ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ለዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት ይሰሩ ነበር ያላቸው ሥስት ሰዎች ደግሞ የትራምፕ አስተዳደር ባለፈው ጥር ዓለም አቀፍ የምግብ እርዳታ መርኃ ግብር እንዲቋረጥ ከወሰነ ወዲህ የምግብ እርዳታው በአራት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መጋዘኖች ውስጥ እንዳለ ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስ የልማት እርዳታ በማቋረጡ ምክንያት በUSAID ሰብዓዊ እርዳታ ቢሮ ስር በሚገኙት በእነዚሁ መጋዘኖች ውስጥ ከአሜሪካን ገበሬዎችና አምራቾች የተሰበሰበ ከ60 ሺህ እስከ 66 ሺህ ሜትሪክ ቶን እርዳታ እንዳለም ጠቁመዋል። ምንጮቹ እንዳሉት ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ሊበላሹ እየተቃረቡ ነው። ምናልባትም በሐምሌ ወር እንዲወገዱ አለያም እንዲቃጠሉ ሳይደረግ አይቀርም። እነዚህ በመበላሸት ላይ ያሉት ምግቦች በመደበኛው አሰራር ለረሀብ የተጋሉጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች ባሉባቸው ሱዳንን ወደመሳሰሉ ሀገራት በአስቸኳይ መከፋፈል የነበረባቸው ናቸው ። በናይጀሪያዋ ቡቻም በእርዳታው መቋረጥ ምክንያት ህጻናት እየሞቱ መሆኑን የሌሎቹም ህጻናት ጤና ለአደጋ ማጋለጡን እኚህ ወላጅ ያስረዳሉ።
«የሚሰጡን ለህጻናት አስፈላጊ የሆኑ የተጨማሪ ምግቦች አቅርቦት ሲቆም ልጄ ታመመ። ተቅማጥ ያዘው ከዚያም ሞተ።አሁን የሌላኛው ልጃችን ጤና ያሳስበናል። እናም ሌላ ለህጻናት ተጨማሪ ምግብ የሚያቀርብ ተቋም አግኝተን ልጃችንን ለማስመዝገብ ተስፋ እንዳርጋለን። ምክንያቱም እኛ ደሀ ነን ።ለልጃችን የሚያስፈልገውን ምግብ ማቅረብ የምንችል አይደለንም።»
ስለጉዳዩ የተጠየቁት የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የእርዳታ አቅርቦቱ እንዲቀጥልና የት መቅረብ እንዳለበትም USAID ከሚመለከታቸው አጋሮች ጋር እየተመካከረ ነው ብለዋል።
ኢስታንቡል ኢራንና የአውሮጳ ኃያላን ቱርክ ውስጥ ስለ ኒዩክልየር ድርድር ተነጋገሩ።
ኢራን ከአውሮጳ ኃያላን ጋር ዛሬ ከዋሽንግተን ጋር ስላካሄደችው የኒዩክልየር ድርድሮች ተነጋገረች። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ስምምነት ለመፈጸም ካልፈጠነች አዲስ ዛቻ ሰንዝረዋል። በኢስታንቡሉ ንግግሩ ላይ የተገኙት የኢራን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ግሀሪባባዲ በኤክስ ገጻቸው በቅርቡ ከዋሽንግተን ጋር ስላካሄዱት ቀጥተኛ ያልሆነ የኒዩክልየር ድርድር እና ኢራን የተጣለባት ማዕቀብ ማንሳትን በሚመለከት ከሶስቱ የአውሮጳ ኃያላን ጋር ሃሳብ መለዋወጣቸውን ጽፈዋል። የአውሮጳ ኃያላን ከኢራኑ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ከመነጋገራቸው በፊት ብሪታንያ ፈረንሳይና ጀርመን በጎርጎሮሳዊው 2015 ዓም የተነሳውን የተመድ ማዕቀብ መልሰው የሚጥሉ ከሆነ ወደ ኋላ ሊመለስ የማይችል ያሉት መዘዝ ሊያስከትልባቸው እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። ። አስፈላጊ ከሆነ ቴህራን ሦስቱን የአውሮጳ ሀገራት ጨምሮ በ2015ቱ ስምምነት ከተሳተፉ ተደራዳሪዎች ጋር እንደገና ልትነጋገር ትችላለች ብለዋል። ትራምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው የ2015ቱን ስምምነት ብቻቸውን በ2018 ዓ.ም አፍርሰው በኢራን የባንክ ስርዓትና የነዳጅ ዘይት ሽያጭ ላይ እንደገና ማዕቀብ ጥለው ነበር። ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝታቸው ባጠናቀቁበት በዛሬው እለት አቡዳቢ ውስጥ እንደተናገሩት አስተዳደራቸው በቅርብ ሳምንታት ከተካሄዱ አራት ዙር ድርድሮች በኋላ ለኢራን የአዲስ ስምምነት ምክረ ሀሳብ ቀርቦላታል። ኢራን በፍጥነት ካልተንቀሳቀሰች መጥፎ ነገር ሊያጋጥማት ይችላል ሲሉም ትራምፕ ዝተዋል።
ዴይር አል ባላህ በእስራኤል የአየር ጥቃት 100 ሰዎች ተገደሉ ሲል የፍልስጤም ዜና አገልግሎት አስታወቀ
እስራኤል ዛሬ በጋዛ ሰርጥ ባካሄደችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 100 ሰዎች ተገድለዋል ሲል የፍልስጤም ዜና አገልግሎት አስታወቀ ። በርካቶች በፍርስራሾች ስር ተቀብረዋል ሲል ዜና አገልግሎቱ ዘግቧል።ቀደም ሲል የሆስፒታል ምንጮች እስራኤል ከትናንት ለሊት አንስቶ እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ ከዴይር አልባላህ እና ከካን ዩኒስ ከተማ ወጣ ባሉ ስፍራዎች ባካሄደችው የአየር ድብደባ የተገደሉ የ48 ሰዎች አስከሬኖች ወደ ኢንዶኔዥያ ሆስፒታል፣ ሌሎች 16 አስከሬኖች ደግሞ ናስር ወደተባለው ሆስፒታል መወሰዳቸውን ተናግረው ነበር። ለሰዓታት በዘለቀው የእስራኤል የአየር ድብደባ ከጃባልያ የስደተኞች መጠለያና ቤት ላህያ ከተባለው ከተማ ሰዎች መውሰድ የቻሉትን ንብረቶቻቸውን ይዘው በራሪዎች በመኪናና እና በእግር ከአካባቢያቸው ሸሽተዋል። አንዳንዶቹ እንዳሉት በድብደባውና በግድያ መሀል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቤታቸውን ለቀው የወጡት ምንም ሳይዙ ነው
እስራኤል ዛሬ የአየር ኃይሏ 150 ጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ፀረ-ታንክና ሚሳይል ጣቢያዎችን ጨምሮ የአሸባሪዎች ያላቸውን ዒላማዎችና ወታደራዊ መዋቅሮችና ማዕከላት መምታቱን አስታውቃለች። ሲከታተላቸው የነበሩ ቅፅር ግቢዎች ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ አንዳንድ አሸባሪ ያላቸውንም ማስወገዱን ገልጿል።
የእስራኤል መንግሥት ቃል አቀባይ ዴቪድ ሜንሰር፣ ሀማስ ታጋቾችን መልቀቅ ካቆመ ወዲህ፣ የእስራኤል ጦር ሲያደርግ እንደቆየው በጋዛ የሚካሂደውን ጥቃት አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ዛሬ ለአሶስየትድ ፕሬስ ተናግረዋል። እስራኤል በጋዛ የምታካሂዳቸው ጥቃቶች ተጠናክረው የቀጠሉት ምግብ፣ ነዳጅ ዘይት፣ መድኃኒትና ሌሎች አቅርቦቶች ወደ ጋዛ እንዳይገቡ በከለከለች በሦስት ወሩ መሆኑ ነው።
ኢስታንቡል የኢስታንቡሉ የሩስያ እና የዩክሬን ንግግር
የዩክሬንና ሩስያ ተወካዮች ከሦስት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ኢስታንቡል ቱርክ ውስጥ ያካሄዱት ቀጥተኛ ንግግር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ከፍተኛ የሚባል ውጤት አለማምጣቱን የዩክሬን ምንጮች አስታውቀዋል።ሩስያ ግን ሁለት ሰዓት ባልደፈነው የሰላም ንግግር መርካትዋን አስታውቃለች። ። ዩክሬን ሰላም ለማውረድ አስፈላጊዎቹን ፈጣን እርምጃዎች ለመውሰድ ዝግጁ ናት ያሉት ዜሌንስኪ ሩስያ ሙሉ እና ቅድመ ሁኔታ የሌለው የተኩስ አቁም ለማድረግና ግድያ እንዲቆም ካልተስማማች በሩስያ ላይ ማዕቀቦች መጣል አለባቸው ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ጽፈዋል። በዩክሬንና ሩስያ የሰላም ንግግር ላይ ሩስያ የያዘችው አቋም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ተቀባይነት የለውም በማለታቸው ፈረንሳይ ጀርመን ብሪታንያና ፖላንድ እንደሚስማሙ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር አስታውቁ። ዛሬ የዩክሬን የብሪታንያ የፈረንሳይ የጀርመንና የፖላንድ መሪዎች በጉዳዩ ላይ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በስልክ ተነጋግረዋል። የአምስቱ ሀገራት መሪዎች ዛሬ ቲራና አልባንያ ውስጥ በተካሄደ የአውሮጳ ፖለቲካዊ ማኅበረሰብ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ነበር ።
ኢስታንቡል ኢራንና የአውሮጳ ኃያላን ቱርክ ውስጥ ስለ ኒዩክልየር ድርድር ተነጋገሩ።
ኢራን ከአውሮጳ ኃያላን ጋር ዛሬ ከዋሽንግተን ጋር ስላካሄደችው የኒዩክልየር ድርድሮች ተነጋገረች። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ስምምነት ለመፈጸም ካልፈጠነች አዲስ ዛቻ ሰንዝረዋል። በኢስታንቡሉ ንግግሩ ላይ የተገኙት የኢራን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ግሀሪባባዲ በኤክስ ገጻቸው በቅርቡ ከዋሽንግተን ጋር ስላካሄዱት ቀጥተኛ ያልሆነ የኒዩክልየር ድርድር እና ኢራን የተጣለባት ማዕቀብ ማንሳትን በሚመለከት ከሶስቱ የአውሮጳ ኃያላን ጋር ሃሳብ መለዋወጣቸውን ጽፈዋል። የአውሮጳ ኃያላን ከኢራኑ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ከመነጋገራቸው በፊት ብሪታንያ ፈረንሳይና ጀርመን በጎርጎሮሳዊው 2015 ዓም የተነሳውን የተመድ ማዕቀብ መልሰው የሚጥሉ ከሆነ ወደ ኋላ ሊመለስ የማይችል ያሉት መዘዝ ሊያስከትልባቸው እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። ። አስፈላጊ ከሆነ ቴህራን ሦስቱን የአውሮጳ ሀገራት ጨምሮ በ2015ቱ ስምምነት ከተሳተፉ ተደራዳሪዎች ጋር እንደገና ልትነጋገር ትችላለች ብለዋል። ትራምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው የ2015ቱን ስምምነት ብቻቸውን በ2018 ዓ.ም አፍርሰው በኢራን የባንክ ስርዓትና የነዳጅ ዘይት ሽያጭ ላይ እንደገና ማዕቀብ ጥለው ነበር። ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝታቸው ባጠናቀቁበት በዛሬው እለት አቡዳቢ ውስጥ እንደተናገሩት አስተዳደራቸው በቅርብ ሳምንታት ከተካሄዱ አራት ዙር ድርድሮች በኋላ ለኢራን የአዲስ ስምምነት ምክረ ሀሳብ ቀርቦላታል። ኢራን በፍጥነት ካልተንቀሳቀሰች መጥፎ ነገር ሊያጋጥማት ይችላል ሲሉም ትራምፕ ዝተዋል።
2024 በዓለማችን ረሀብ የተባባሰበት ዓመት ነበር
ግጭቶችና የአየር ንብረት ለውጥ በጎርጎሮሳዊው 2024 ዓ.ም. በዓለማችን ረሀብ እንዲባባስ ማድረጋቸውን የተመድ አስታወቀ። ድርጅቱ ዛሬ በወጣው ዘገባ መሠረት እጅግ በከፋ የምግብ ዋስትና እጦት ሰበብ በ53 አገራትና ግዛቶች የሚገኙ ከ295 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የችግሩ ሰለባ ሆነዋል። ይኽው የጎርጎሮሳዊው 2025 ዓ.ም. የዓለም የምግብ ቀውስ ዘገባ እንደሚለው ችግሩን ያባባሱት ግጭት የአየር ንብረት ለውጥና የኤኮኖሚ ቀውስ ናቸው።በያዝነው በጎርጎሮሳዊው 2025 ዓም ሰብዓዊ የምግብ እርዳታ በእጅጉ በመቀነሱ ሁኔታዎች ይበልጥ እንደሚባባሱም ድርጅቱ አስጠንቅቋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሚደርሰውን የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት USAID 80 በመቶ ሰብዓዊ መርኃ ግብሮች መዝጋታቸው ችግሩ ከሚያባብሱት ምክንያቶች ውስጥ ይጠቀሳል።
ባለፈው ጎርጎሮሳዊው 2024 ዓም ጋዛ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሄይቲ እና ማሊን ጨምሮ ግጭት በተካሄደባቸው በ20 ሀገራት የሚገኙ ቁጥራቸው 140 ሚሊዮን የሚጠጋ ሰዎች አስከፊ የምግብ ዋስትና ችግር ላይ ይገኛሉ። ሱዳን ረሀብ በሀገርዋ እንደገባ አረጋግጣለች።
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ