የጀርመን የምርጫ ስርዓትና የኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የጀርመን ጉብኝት
ማክሰኞ፣ መጋቢት 8 2018
ማስታወቂያ
ከጥቂት ወራት በኋላምርጫከምታካሂደው ከኢትዮጵያ የተለያዩ መገናኛና ብዙሀን የተውጣጡ ጋዜጠኞች ፣ባለፈው ሳምንት እዚህ ጀርመን ስለሀገሪቱ የምርጫ ሂደት ግንዛቤ ማስጨበጫ ጉብኝት አድርገዋል። በፌደራል ጀርመን የምርጫ ስርዓቶች እና አተገባበር ላይ ባተኮረው በዚህ የአንድ ሳምንት ጉብኝት የጀርመን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጨምሮ የምርጫ ጉዳይ የሚመለከታቸውን ተቋማት የጎበኙት ጋዜጠኞቹ ገለጻዎችም ተደርገውላቸዋል።
በመጪው እሁድ የአካባቢ ምርጫ በሚካሄድበት ከ16ቱ የጀርመን ፌደራዊ ግዛቶች አንዱ በሆነው በጀርመንኛ መጠሪያው በራይንላንድ ፋልስ በእንግሊዘኛው በራይንላንድ ፕላቲኔት ፌዴራዊ ግዛት ዋና ከተማ ማይንዝም የምርጫ ሂደቱን፣ የምርጫ ዘመቻዎችንና ፣የቴሌቪዥን ክርክርም በአካል ተገኝተው ተከታትለዋል።
ጋዜጠኞቹ በበርሊንና በማይንዝ ከተሞች ቆይታቸው ታሪካዊ ቦታዎችንና ቤተ መዘክሮችንም ጎብኝተዋል። በዛሬው አውሮጳና ጀርመን ዝግጅታችን ኂሩት መለሰ ከጋዘጠኞቹ ጋር በጉብኝቱ የተካፈለውን የአዲስ አበባውን የዶቼቬለ ዘጋቢ ሰሎሞን ሙጬን አነጋግራዋለች። ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ
ኂሩት መለሰ
ፀሐይ ጫኔ