1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰባቱ አንጋፋ ሰዓልያን አዉደ-ርዕይ

ሐሙስ፣ ኅዳር 22 2015

አዉደ-ርዕዩ፤ ከ1950ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1960ዎቹ መጨረሻ፤ በዓለ የሥነ-ጥበብ ዲዛይን ትምህርት ቤት፤ በስዕል ሞያ የተመረቁ ቀደምት ተማሪዎችና፤ ከፊሎቹም በአሁኑ ወቅት ትምህርት ቤቱ ዉስጥ በማስተማር ላይ የሚገኙ ናቸው። አውደ-ርዕዩን ማዘጋጀት ያስፈለገው ለኢትዮጵያ ባለውለታ የሆኑ አንጋፋ ሰዓሊዎችን እና ሥራዎቻቸውን ለማስተዋወቅ ነው።

https://p.dw.com/p/4KLj5
Äthiopien | Ausstellung verschiedener äthiopischer Künstler
ምስል Privat

የአንጋፋዎቹ የጥበብ ሥራ በአብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከል

«የኢትዮጵያ ህዝብ ለስዕል ያለዉ አመለካከት ቀድሞ ከነበረዉ እየተቀየረ እንደመጣ ነዉ እኔ የተረዳሁት በባለ ኃብቶችም፤ እንደዚሁ። ብዙ ነገሮችን ነግደዉ መኖር የሚችሉበትን ቦታ ለአርት ሲሰጡ ይስተዋላል። በዚህ ጉዳይ የአብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከል ተጠቃሽ ነዉ። ባለቤቱ የኢትዮጵያን አርት አስተዋዉቃለሁ ብሎ ባለሞያዎችን ሰብስቦ ነዉ እየሰራ የሚገኘዉ።»

Äthiopien | Ausstellung verschiedener äthiopischer Künstler
አብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከልምስል Privat

ሠዓሊ ለማ ጉያ ሲታወሱሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ስለተከፈተዉ የሥዕል አዉደ-ርዕይ የነገሩን፤ የሥነ-ጥበብ ታሪክ ባለሞያዋ፤ ወ/ሮ ዓይናለም እምሩ ናቸዉ። መዲና አዲስ አበባ የሚገኘዉ፤ አብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከል፤ ሰሞኑን  ሰባት አንጋፋና ታዋቂ ሠዓሊያን የተሳተፉበት፤ አውደ ርዕይን ለተከመልካች ከፍቷል። እስከ ህዳር 30 የሚዘልቀዉ ይህ አዉደ-ርዕይ፤ ከ1950ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1960ዎቹ መጨረሻ፤ በዓለ የሥነ-ጥበብ ዲዛይን ትምህርት ቤት፤ በስዕል ሞያ የተመረቁ ቀደምት ተማሪዎችና፤ ከፊሎቹም በአሁኑ ወቅት ትምህርት ቤቱ ዉስጥ በማስተማር ላይ የሚገኙ ናቸው። የአብራክ ሥነ-ጥበብ ማዕከል የቦርድ አባል ወይዘሮ ዓይናለም እምሩ፤ አውደ-ርዕዩን ማዘጋጀት ያስፈለገው ለኢትዮጵያ ባለውለታ የሆኑ አንጋፋ ሠዓሊዎችን እና ሥራዎቻቸውን ለማስተዋወቅ ነው ብለዋል። ሰዓሊዉና ቡሩሹ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት

Äthiopien | Ausstellung verschiedener äthiopischer Künstler
አብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከልምስል Privat

«በአዉደ ርዕዩ ላይ የተሳተፉት ሰዓሊዎች፤ በኢትዮጵያ የዓለ የስዕል መማርያ ተቋም ከተቋቋመ ጀምሮ የነበሩ ለኢትዮጵያ የስዕል ጥበብ ማደግ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ እና አሁንም በማስተማር ላይ የሚገኙ ሰዓልያን ናቸዉ። እነዚህ ሰዓልያን በዉጭ ሃገርም ይሁን በሃገር ዉስጥ ትልቅ እዉቅና እና ሽልማት ያገኙም ናቸዉ።»

በአብራክ ማዕከል ሠላሳ አራት ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡት ሠዓሊያን፤ አብዱራህማን መሐመድ ሸሪፍ፣ ወርቁ ጎሹ፣ ዘሪሁን የትምጌታ፣ ደስታ ሐጎስ፣ ቱሉ ጉያ፣ ጥበበ ተርፋና ልዑልሰገድ ረታ መሆናቸውን የሥነ-ጥበብ ታሪክ ምሁርዋ ወ/ሮ ዓይናለም እምሩ ተናግረዋል።ግዙፍ የሥዕል ዓዉደ ርዕይ በአዲስ አበባ

« ይህን የስዕል አዉደ ርዕይ እንዲመቻች እገዛ ያደረገዉ የአብራክ ጋለሪ ባለቤት፤ የሰዓሊዎቹን ስራ ከሌላዉ ዓለም ጋር ለማስተዋወቅ፤ ብሎም ራሳቸዉ ሰዓልያኑ በተሰጦዋቸዉ እንዲተነፍሱ ለማድረግ ጥበቡንም አጉልቶ ለማዉጣት ነዉ። »

ይህን የስዕል ኤግዚቢሽን ለመክፈት ከታሰበ ከአንድ ዓመት በፊት እንደሆነ የሚናገረዉ ሰዓሊ ለይኩን ግርማ በበኩሉ በስዕል አዉደ ርዕዩ የቀረቡት የአንጋፋዎቹ አስተማሪ ስራዎች፤ ለአሁኑ ዘመን  ባለሞያዎች ትልቅ ፈር ቀዳጅ በመሆናቸዉ እና፤ በሠዓሊ እና በገጣሚ ባለቅኔ  ገብረክርስቶስ ደስታ ዘመን የተካሄደን የስዕል እግዚቢሽንን ለማዉሳትም ያለመ መሆኑን ተናግሯል።ነፃ ጥበብን ፍለጋ - ኢትዮጵያ 

Äthiopien | Ausstellung verschiedener äthiopischer Künstler
አብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከልምስል Privat

በሥነ-ጥበብ ሞያ በኩዩባ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁት እና ስለ ተለያዩ የሥነ-ጥበብ ሥራ  ታሪኮች በመፃፍ ላይ የሚገኙት የሥነ-ጥበብ ታሪክ ምሁርዋ ወ/ሮ ዓይናለም እምሩ እንደሚሉት፤ በኢትዮጵያ ሰዎች ለሥነጥበብ ያላቸዉ ፍቅር እና ግንዛቤ እየጨመረ መጥቷል።

እምቅ እና ድንቅ እዉቀት ያላቸዉ ወጣት ሰዓልያን በኢትዮጵያ የሥነ-ጥበብ መድርክ እየታዩ መሆኑ ይነገራል። የተለያዩ ዓዉደ ርዕዩች እየተከፈቱ ነዉ ይሁና ሰዓሊዉ ለስዕሉ መገልገያ የሚሆን ቁሳቁስ ለማግኘት ችግር እንዳለበትም ይሰማል። «ጥበብ በአደባባይ» በጎተ ተቋምይህ እንዴት ይታይ ይሆን?  የሥነ-ጥበብ ታሪክ ምሁርዋ ዓይናለም እምሩ እንደሚሉት፤ ሰዓሊዉ ችግር አለበት።

Äthiopien | Ausstellung verschiedener äthiopischer Künstler
አብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከልምስል Privat

ወ/ሮ ዓይናለም እንደተናገሩት አንጋፋዎቹ ሰዓሊያን የሥነ-ጥበብ ሥራዎቻቸዉን ያቀረቡበት እንደ አብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከሎች ሰዓልያኑን ለመደገፍ ታልሞ  ሥዕሎቻቸዉን ለመሸጥ ብቻ የታሰበ ሳይሆን የሥነ-ጥበብ ማዕከሎች የሠዓልያን እምቅ እዉቀት ለዕይታ የሚቀርቡባቸው እንዲሁም ግንዛቤ ማግኛ ቦታዎችም እንደሆኑ ገልፀዋል። ሠዓሊ ለይኩን ግርማ የአብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከል መስራች እና አስተባባሪ ነዉ። ሰዓሊ ለይኩንን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሠዓልያን ህይወት ምን ይመስላል ስንል ጠይቀነዋል። «ስዕሎቼ ኢትዮጵያዊ ናቸዉ» ጌታቸዉ ብርኃኑ

Äthiopien | Ausstellung verschiedener äthiopischer Künstler
አብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከልምስል Privat

በአብራክ የሥነ-ጥበብ ማዕከል፤ ሰሞኑን  ሰባት አንጋፋና ታዋቂ ሰዓሊያን በተሳተፉበት፤ ዓውደ ርዕይ ላይ  ሰዓሊያኑ  በተናጥል ከ4 እስከ 5 በአጠቃላይ ወደ 34 የሥዕል ሥራዎች መቅረባቸዉ ተመልክቷል። ዓዉደ-ርዕዩ እስከ ህዳር ወር መጨረሻም ይዘልቃል። በዝግጅቱ ላይ ቃለ ምልልስ የሰጡንን በዶቼ ቬለ ሥም እያመሰገንን ፤ ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።    

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ