1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመስከረም 20 ቀን 2017 የዓለም ዜና

Eshete Bekeleሰኞ፣ መስከረም 20 2017

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኻርቱም የሚገኝ የአምባሳደሯ መኖሪያ ቤት በወታደራዊ አውሮፕላን ተደብድቧል በሚል ያቀረበችውን ክስ የሱዳን ጦር አስተባበለ። በደቡብ አፍሪካ ምሥራቅ ኬፕ ክፍለ ግዛት በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 18 አሻቀበ። ርዋንዳ ኃይለኛ ተላላፊ በሆነው ኢቦላ መሰል የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን አስታወቀች። እስራኤል ሊባኖስን በእግረኛ ወታደሮች ከወረረች ሒዝቦላሕ ለውጊያ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት ሀገራቸው እግረኛ ወታደሮቿን ወደ ሊባኖስ ልታዘምት እንደምትችል ፍንጭ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ኢራንን አስጠንቅቀዋል

https://p.dw.com/p/4lGC0
ቀጣዩን ክፍል እለፈው ስለዚህ ዝግጅት

ስለዚህ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-News-DWcom

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።