በስፔን ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለው የሙቀት ወጀብ በፈረንሣይስ ምን አደረሰ?
ሐሙስ፣ ሰኔ 18 2018
እጅግ ኃይለኛ የበጋ ንዳድ አብዛኛው አውሮጳን ካለፈው የሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በብርቱ በመምታት የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል ። የአዉሮጳ ሐገራትን የመታዉ የሙቀት ማዕበል በተለይ ስፔን እና ፈረንሣይ ውስጥ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት በማጥፋት ሥራና እንቅስቃሴን አስተጓጉሏል ። ስፔን ውስጥ ከ45 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ባለፈው የሙቀት ንዳድ የተነሳ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ኹኔታ በአራት ቀናት ብቻ ከ200 በላይ ሰዎች ሕይወት መቀጠፉ ተዘግቧል ።
ፈረንሳይ ውስጥ ደግሞ በዚሁ የሙቀት ወጀብ የተነሳ ዛሬም ጭምር ከቤት ውጪ መኪና ውስጥ ሕጻናት ሞተው ተገኝተዋል ። ለመኾኑ የሙቀቱ ወጀብ ከበረታባቸው የአውሮጳ አገራት መካከል ፈረንሳይ ውስጥ የሟቾች ቁጥር ስንት ደርሷል ፥ ትናንት እጅግ ከፍተኛ ነበር የተባለው የሙቀቱስ መጠን? የፓሪስ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህን: በተለይ ከትናንት ጀምሮ የሙቅርት ወጀቡ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ ነበር ብላለች ።
የሙቀቱ ወጀብየበርካታ ሰዎችን ሕይወት ሳይቀጥፍ ብዙዎችን ሳይጎዳ መከላከል ይቻል እንደነበር በመጥቀስ ፖለቲከኞች ላይ ተቃውሞዎች ተሰምተዋል ። ፈረንሳይ ውስጥ ተቃዋሚዎች ብርቱ ትችት ሲሰነዝሩ መንግሰትም ትችቱን ተቀብሎ ለማስተካከል መስማማቱ ተገልጧል ።
አሁን የሙቀት መጠኑ በአብዛኛ የአውሮጳ ክፍል የሚቀንሰው ከዐርብ ወዲህ ነው ተብሎ ተገምቷል ። እስከዚያ ድረስ አደጋውን ለመቀነስ ሰዎች በወንዞች እና ፏፏቴዎች ራሳቸውን እንዲያቀዘቅዙ ተመክረዋል ። ወደፊት ለረዥም ጊዜ ፈረንሳይ ውስጥ ሕንጻዎችን ለሙቀት በሚመቹ መልኩ ማደስ ያሻል ተብሏል ።
67 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ፈረንሳይ 63 ሚሊዮኑ በዚሁ ከ30 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ በተመዘገበ የሙቀት ወጀብ ተጋላጭ መኾኑ ተዘግቧል ። ጀርመን ውስጥ ሙቀቱ ከ30 ዲግሪ በላይ አሻቅቦ 70 ሚሊዮን ሰዎችን ተጋላጭ አድርጓል ። ጣሊያንr ውስጥ 38 ሚሊዮን ሰዎች እንዲሁም ቤልጂየም፣ ሉግዘምበርግ እና ኔዘርላndeም የሙቀት ወጀቡ ካስጨነቃቸው የአውሮጳ አገራት ይመደባሉ ። የሙቀቱ መጠን በምዕራብ አውሮጳ ከዐርብ ጀምሮ ቢቀንስም በምሥራቁ ክፍል ግን በሳምንቱ መጨረሻ ጭምር የሚያሳየው ቀይ እንደሆነ ተገልጧል ።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ