1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
የምግብ ዋስትናኢትዮጵያ

ግብርና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ

ነጋሣ ደሳለኝ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 2 2018

አቶ አወቀ ኃይሉ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ነዋሪ ሲሆን በ2013 ዓ፣ም ተፈናቅለው የነበሩና ወደቀያቸው ከተመለሱት መካከል ናቸው፡፡ በወረዳው የግብርና ስራ ከባለፈው ዓመት በተሻለ መልኩ አርሶ አደሩ ስራውን መቀጠሉን ገልጸው በወረዳው የጸጥታ ስጋት በሚታይባቸው ሁለት ቀበሌዎች ግን በተሟላ መልኩ አርሶ አደሩ ወደ ስራ አለመግባቱን ጠቁመዋል ፡፡

https://p.dw.com/p/5GpvG
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ዘርፍ ከባህላዊ የአስተራረስ ዜዴም በተጨማሪ በትራክተር እየታረሰ እንደሚገኝ |የተገለጸ ሲሆን በግብርናው ዘርፍ ከዚህ ቀደም ከነበረው ሰፊ ለውጥ እየታየ እንደሚገኝ የክልሉ ግብርና ቢሮ አመልክቷል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ዘርፍ ከባህላዊ የአስተራረስ ዜዴም በተጨማሪ በትራክተር እየታረሰ እንደሚገኝ |የተገለጸ ሲሆን በግብርናው ዘርፍ ከዚህ ቀደም ከነበረው ሰፊ ለውጥ እየታየ እንደሚገኝ የክልሉ ግብርና ቢሮ አመልክቷል፡፡ ምስል፦ Negasa Dessalegn/DW

ግብርና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ

በቤኒሻንጉል ክልልበዘንድሮው የምርት ዘመን ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት በምርት ለመሸፈን ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አመልክቷል፡፡ ይህም ከባለፉት አምስት ዓመታት ከነበረው የተሻለ ነው የተባለ ሲሆን በክልሉ ተፈናቅለው የነበሩ ወደቀያቸው የተመለሱ ዜጎችም ወደ ስራ መግባታቸው እና እንደትክተር ያሉ የእርሻ መሳሪያዎችን አንድ አንድ የክልሉ ቦታዎች አርሶ አደሩ መጠቀም መጀመሩም ተገልጸዋል፡፡ የግብርናው ዘርፍ ለውጥ እያሳየ እንደሚገኝ የተገልጸ ሲሆን ያነጋርናቸው አርሶ አደሮች በተማላ መልኩ ወደ ስራ የገቡ እንዳሉ ሁሉ፣ አንድ ቦታዎች እንደ መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ገጠራማ ቦታዎች እንደ ጊፖ፣ጫንጮ፣በጫቲ የተባሉ ቀበሌዎች በዞኑ ቡሌን ወረዳ ጎንጎ የተባለ ቀበሌ ደግሞ የአፈር ማዳሪያ እጥረት እና በስጋት ምክንያት በተሟላ መንገድ ወደ ስራ እንዳልገቡ ጠቁመዋል፡፡

‹‹ሁለት ሚሊዪን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ዝግጁ ሆነዋል›› የክልሉ ግብርና ቢሮ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 70 ሚሊዪን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የገለጸው የክልሉ ግብርና ቢሮ በዘንድሮ የምርት ዘመን በዘር ለመሸፈን የታቀደው መሬት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ400 ሺ ሄታር ብልጫ እንዳለው አስታውቋል፡፡ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ባበክር ሀሊፋ በክልሉ ከ2015 ዓ.ም በፊት በነበሩት አለመግባባቶች ምክንያት የግብርና ምርት መጠን አስተኛ እንደነበር በመግለጽ ከ2017 ዓ.፣ም ወዲህ የግብርና ምርት መጨመሩን ገልጸዋል፡፡ ከባለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ የዘንድሮ በዘር ለመሸፈን የተዘጋጀው መሬትም በሄክታር ከፍተኛው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከግብአት ጋር ተያይዞም በቂ የግብርና ምርት መቅረቡን የተናገሩ ቢሆን ከተያለዩ አካባቢዎች የአፈር ማዳበሪያ እና የስራ መሳሪያ እጥረት እንደለም አርሶ አደሮች ገልጸዋል፡፡

ከቤኒሻንጉል ክልል ተፈናቅለው የነበሩ ወደቀያቸው የተመለሱ ዜጎችም ወደ ስራ መግባታቸው እና እንደትክተር ያሉ የእርሻ መሳሪያዎችን አንድ አንድ የክልሉ ቦታዎች አርሶ አደሩ መጠቀም መጀመሩም ተገልጿል፡፡
ከቤኒሻንጉል ክልል ተፈናቅለው የነበሩ ወደቀያቸው የተመለሱ ዜጎችም ወደ ስራ መግባታቸው እና እንደትክተር ያሉ የእርሻ መሳሪያዎችን አንድ አንድ የክልሉ ቦታዎች አርሶ አደሩ መጠቀም መጀመሩም ተገልጿል፡፡ ምስል፦ Negasa Dessalegn/DW

አቶ አወቀ ኃይሉ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ነዋሪ ሲሆን በ2013 ዓ፣ም ተፈናቅለው የነበሩና ወደቀያቸው ከተመለሱት መካከል ናቸው፡፡ በወረዳውየግብርና ስራ ከባለፈው ዓመት የተሻለ መልኩ አርሶ አደሩ ወደ ስራ መግባቱን ጠቁመዋል፡፡ በወረዳው የጸጥታ ስጋት በሚተስዋልባቸው ሁለት ቀበሌዎች ደግሞ በተሟላ መልኩ አርሶ አደሩ ወደ ስራ አለመግባቸውን ጠቁመዋል ፡፡
በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ጊጶ፣ ጌሸ፣ጫንጮ ቀበሌዎችና ሌሎች እንዲሁም በዞኑ ቡሌን ወረዳ ጎን የተባለ ቦታዎች ከአራት ወራት በፊት ተከስቶ በነበረው ግጭቶች ሳቢያ አርሶ አደሩ በእነዚህ ገጠራማ ቦታዎች ተፈናቅለው እንደነበር የተናገሩት አንድ ነዋሪ አብዛኛው የቀበሌው ነዋሪዎች ወደቀያቸው ባለመመለሳቸው ወደ ስራ አለመግባታቸውን ተናግረዋል፡፡ ነዋሪ አብዛኛው የቀበሌው ነዋሪዎች ወደቀያቸው ባለመመለሳቸው ወደ ስራ አለመግባታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህ አካባቢ በነበረው ግጭቶች ሳቢያ በርካታ መኖሪያቤቶችም ተቃጥለው የበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቦታ ላይ ከተወሰኑት አርሶ አደሮች በስተቀር መደበኛ ስራ አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡

በከማሺ ዞን ውስጥ በግብርና ስራ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ ጅሩ ካባ የተባሉ ነዋሪ በዞኑ ግብርና በስፋት የሚሰራበትና በእርሻ በሚታወቁት ዛይ እና ሚዥጋ በተባሉ የዞኑ ወረዳዎች የግብርና ስራ የተሻለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው የጸጥታ ሁኔታ የተረጋጋ መሆንንና የተናገሩት ነዋሪው የግብርና ግብዓት እጥረት እንዳለም ገልጸዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ዘርፍ ከባህላዊ የአስተራረስ ዜዴም በተጨማሪ በትራክተር እየታረሰ እንደሚገኝ |የተገለጸ ሲሆን በግብርናው ዘርፍ ከዚህ ቀደም ከነበረው ሰፊ ለውጥ እየታየ እንደሚገኝ የክልሉ ግብርና ቢሮ አመልክተዋል፡፡ በ2017 ዓ.ም ምርት ዘመን 56 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን የቢሮው መረጃ ያመለክታል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ