የሐይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች አዲስ አበባና መቐለን ሊያሸማግሉ ነው
ሰኞ፣ ሰኔ 8 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የአገር ሽማግሌዎች ጥምረት በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፌድራል መንግሥት እና በትግራይ መካከል የተካረረውን ልዩነት ለማስታረቅ ወደ መቐለ ሊያመሩ ነው። የኢትዮጵያ የየሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሐጂ መስዑድ አደም የኢትዮጵያ ነባራዊ ፖለቲካ የሐይማኖት መሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎችን "ጣልቃ ገብነት ይፈልጋል" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ለሽምግልናው ይሁንታ የሰጡት የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎች በሚያደርጉት ጥረት እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ