1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

“አገልግሎታችንን ወደ አምስት ኮከብ ማሳደግ እንፈልጋለን” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ሥዩም ጌቱ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 23 2018

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች አገልግሎቱን አሁን ካለበት አራት ኮከብ ወደ አምስት ኮከብ የአገልግሎት ደረጃ ለማሳደግ እንደምጥር አሳወቀ፡፡ የምስረታ 80ኛ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው አየር መንገዱ ከቋሚ ደንበኞቹ ጋር ስመክር የአገልግሎት ደረጃውን በማላቅ ከቀዳሚ አየርመንገዶች ተርታ መሰለፍ የሁል ጊዜ ጥረቱ እንደሆነም አስረድቷል፡፡

https://p.dw.com/p/5D85I
Äthiopien Addis Abeba | Ethiopian Airlines Customer Experience Day | Podiumsdiskussion
ምስል፦ Seyoum Getu Hailu/DW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገልግሎት ጥራቱን ከፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ አለ

“ደንበኛ ክብር ነው ብቻ ሳይሆን ንጉስም ነው ብለን ሁል ጊዜም ስንቀሳቀስ ቆይተናል” የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው 80ኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው አየር መንገዱ ትናንት ሓሙስ ሚያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቋሚ ደንበኞቹ ጋር ስለሚሰጠው አገልግሎት ቅልጥፍና እና ተግዳሮቱ በመከረበት ወቅት የተናገሩት ነው፡፡


የደንበኞች አገልግሎት ትኩረት


ኢትዮጵያእጅጉን ስኬታማ ኩባንያ ነው የሚባልለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተመሰረተበት የጎርጎሳውያኑ 1946 ጀምሮ ባለፉት 80 ዓመታት ባለፈባቸው ውጣውረዶች አብዛኛው ታሪኩ የስኬት እንደሆነም በርካቶችን ያስማማል፡፡ ታዲያ ይህን 80ኛ ዓመቱን የምስረታ በዓል በተለያዩ ስነስርዓቶች እያከበረ የሚገኘው አየር መንገዱ ትናንት ሓሙስ ከደንበኞቹ ጋር ፊትለፊት ተገናኝቶ በመከረበት ወቅት ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው አየርመንገዱ በመርህው ከደህንነት ስራዎች ቀጥሎ ትልቁን ትኩረት የሚሰጠው ለደንበኞቹ እርካታ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደህንነት ቀጥሎ ትልቁን ትኩረት የሚሰጠው ለደንበኞች አገልግሎት ነው” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ ይህም የሆነው ኢንደስትሪው ውስጥ ባለው እጅግ ጠንካራ ፉክክር ተወዳድሮ ደንበኞችን ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ማምጣት፤ ደጋግሞ እንዲጠቀሙ ማድረግ ካልተቻለ አየርመንገዱ ባለበትም መቀጠል አዳጋች ስለሚሆንበት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ “ላረጋግትላችሁ የምወደው የኢትዮጵያ አየርመንገድ አመራር የደንበኞቹን አያያዝ ምን ጊዜም ቢሆን ደረጃ በደረጃ ለማሳደግ ስጥር የቆየ መስሪያ ቤት ነው” በማለትም አየርመንገዱ ለደንበኞቹ የሚሰጠው ትልቅ ስፍራ የስኬቱ አንድ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

“አገልግሎታችንን ወደ አምስት ኮከብ ማሳደግ እንፈልጋለን” የኢትዮጵያ አየር መንገድ
“አገልግሎታችንን ወደ አምስት ኮከብ ማሳደግ እንፈልጋለን” የኢትዮጵያ አየር መንገድምስል፦ Seyoum Getu Hailu/DW


የደንበኞች አስተያየት


ታምሩ ሪቂታ የ20 ዓመት የኢትዮጵያ አየርመንገድ ደንበኛ ናቸው፡፡ አየርመንገዱ ቋሚ ካላቸው ደንበኞቹ ጋር በተወያየበትም መድረክ ከተሳታፊዎቹ አንዱ ናቸው፡፡ እንደ እሳቸው አስተያየት፤ “የኢትዮጵያ አየርመንገድን ሁሌም የምጠቀመው አንዱ እኛ ስለሆነ ነው፡፡ ሌላው ግን አገልግሎቱ፤ ደህንነቱ እና ምቾቹ ወደዚህ አከባቢ ከሚበሩ፣ አንዳንዱ ዋጋቸውም ቅናሽ ከሆኑ የበለጠ እንዲመርጠው ያስገድደኛል” የሚለውን ሃሳባቸውን አጋርተዋል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የአየር መንገዱ የአገር ባለቤትነት እኔነት ስሜት የሚፈጥርባቸው መሆኑ ወደውት እንዲገለገሉበት ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡
የ20 ዓመት የኢትዮጵያ አየርመንገድ ደንበኛው አቶ ታምሩ አየርመንገዱን ምንጊዜም ስመርጡት ግን እንከን አልባም ስለሆነ እንዳይደለ ያነሳሉ፡፡ “ለምሳሌ ስትወርድ ሻንጣ ለመውሰድ ያለው ረጅም ጊዜ እና እንግልት፤ በርግጥ አንዳንዴ ከደህንነት ጋር የተያያዘ ነው ቢሉንም እሱ መሻሻል አለበት” የሚለውን አስተያየታቸውን አጋርተውናል፡፡


የአየር መንገዱን አገልግሎት ወደ አምስት ኮከብ ለማሳደግ


የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰውም ከደንበኞቹ ጋር በተደረገው ውይይት የደንበኞች አገልግሎቱ አየር መንገዱን ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ ቢያበቃውም ግን በፍጹም በቂ ነው የሚል እምነት የላቸውም፡፡ በተለየ ሁኔታ ተመርጠው ለውይይት መድረኩ ለተጋበዙት ቋሚ ደንበኞቻቸው እንዳሉም፤ “ምናልባት የምትጠብቁትን ያህል አገለግሎት አግኝታችሁ ሳይሆን የኢትዮጵያ አየርመንገድን እንደ አገር ኤታችሁ ከኛ ጋር ስትበሩ ቆይታችኋል ዛሬም ብግልጽ ጥሩውን ጥሩ ደካማ ጎናችንን ሊሻሻል ገባል ብላችሁናል፡፡ አሁን ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ባለአራት ኮከብ አየርመንገድ ሆነን መቅርት አንፈልግም፤ በምንሰራው ስራ ካለቅን አጠቃላይ የደንበኞችን ባለ አምስት ኮከብ ለመሆን   አተቃላይ የደንበኞች ጉዞ በማሻሻል ህልማችን ወደ ሆነው ወደ አምስት ኮከብ ማደግ እንችላለን” የሚለውን ውጥናቸውን አጋርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች አገልግሎት
´´ባለአራት ኮከብ አየርመንገድ ሆነን መቅርት አንፈልግም፤ በምንሰራው ስራ ካለቅን አጠቃላይ የደንበኞችን ባለ አምስት ኮከብ ለመሆን   አተቃላይ የደንበኞች ጉዞ በማሻሻል ህልማችን ወደ ሆነው ወደ አምስት ኮከብ ማደግ እንችላለን”ምስል፦ Seyoum Getu Hailu/DW


ደንበኞች የሚሰጡትን የትኛውንም ጉድፍ አየርመንገዱ አቅልሎ እንደማይመለከተውም የገለጹት ስራ አስፈጻሚው፤ በደንበኞች አገልግሎት፣ በሰው ልማት፣ በቴክኖሎጂ በተለይም በዲጂታል አገልግሎቱ አየር መንገዱ የሚያደርገውን ኢንቨስትመንት እንደማያቋርጥም ገልጸዋል፡፡
አየርመንገዱ ከደንበኞቹ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ከተገኙ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፤ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በተደረገው የፓናል ውይይት የአየር መንገዱ ቁልፍ ስኬት ይህ ነው ብለዋል፡፡ “ተቋሙ መቶ በመቶ የመንግስት ነው መቶ በመቶ ግን በንግድ መርህ ነው የሚሰራው” በማለት በዚህም ተቋሙ አድጎም መንግስትም የኢትዮጵያ ህዝብም ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ