1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውሳኔ

ገበያው ንጉሤ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 14 2018

በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት ተነፍጎት አራተኛ ዓመቱን የደፈነው የሱዳን ጉዳይም አንስተው የተወያዩ ሲሆን በ3 መሰረታዊ ጉዳዩች ላይ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

https://p.dw.com/p/5Cdvd
የአውሮፓ ሕብረት ባንዲራ
የአውሮፓ ሕብረት ባንዲራምስል፦ Jana Rodenbusch/REUTERS

የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውሳኔና አንደምታው

የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መደበኛ ስብሰባ ትናንት ሉግዘምበርግ ውስጥ አካሂደዋል። በውይይታቸው በዩክሬይና ሩስያ ጦርነት፣ በመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታና በሱዳን ላይ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ አንስተዋል። ዩክሬይንን በተመለከተ ካነሷቸው ጉዳዩች አንዱ ለዩክሬይን የሚሰጠው ድጋፍ መቀጠል እንዳለበት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በአንጻሩ በሩስያ ላይ የተጀመሩ ማዕቀቦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። 
የአውሮጳ ኅብረት በጀትን በመሳሰሉ ዐበይት ጉዳዮች የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች የሁሉም አገራት ይሁንታ እንደሚያስፈልግ ይታወቃል።  የሃንጋሪው ፕሬዚደንት ቪክቶር ኦርባን ከዚህ ቀደም በዩሮ ቦንድ ተሰባስቦ ለዩክሬይን እንዲሰጥ በታቀደው 90 ቢልዮን ዩሮ ድጋፍ በመቃወማቸው እስከ አሁን ታግዶ ቆይቶ ነበር። ሰሞኑ በሃንጋሪ በተካሄደው ምርጫ አፍቃሬ ሩስያ የሆኑት ኦርባን በፒተር ማግያር መሸነፋቸውን ተከትሎ ይህ ድጋፍ ለዩክሬይን ሊለቀቅ የሚችልበት ሁኔታ ፍንጭ ታይቷል። 
በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት ተነፍጎት አራተኛ ዓመቱን የደፈነው የሱዳን ጉዳይም አንስተው የተወያዩ ሲሆን በ3 መሰረታዊ ጉዳዩች ላይ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። አንደኛው የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግ፤ ሁለተኛው በሱዳን ስቪል አስተዳደር እንዲመሰረትና በሱዳን ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነትን እንዲረጋገጥ የሚሉ ናቸው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ከብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ጋር የነበረን አጭር ቆይታ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን እንድታደምጡት በአክብሮት እንጋብዛለን።
ገበያው ንጉሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ