1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

አዲሱ የአውሮፓ ህብረትና የህንድ የንግድ ስምምነት

ገበያው ንጉሤ
ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2018

የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያሳለፉትን የታሪፍ ውሳኔ ቢያንስ እንዲያሻሻሽሉ እየጎተጎቱ ነው።በሌላ በኩል የአውርፓ ህብረት ከሌሎች አገሮች ጋር ሲካሂዱ የቆዩ የንግድ ድርድሮችን በመቋጨት አዳዲስ ስምምነቶንም በማድረግ አማራጭ የንግድ መስመሮች እና ገበያዎችን እያፈላለገ ነው።

https://p.dw.com/p/58T9C
ኦርሱላ ፎንዴር ላየን ፤የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት
ኦርሱላ ፎንዴር ላየን ፤የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንትምስል፦ Kenzo Tribouillard/dpa/Pool AFP/AP/picture alliance

አዲሱ የአውሮፓ ህብረትና የህንድ የንግድ ስምምነት

ከፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ  ትቀደም  ፍልስፍና የተቀዱት የአሜሪካ የንግድ፣ ደህንነትና የፍልስተኞች ፖሊሲዎች ከሁሉም በላይ የአሜሪርካ ወዳጅና አጋር ሆነው በቆዩት ካናዳ፣ ሜክሲኮና የአውርፓ ህብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳይ እንዳደረሱ መሆናቸው ነው የሚነገረው። ፕሬዝዳንቱ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስልጣን እንደመጡ ብዙ  ሳይቆዩ በማናቸውም ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የገቢ ታክስ ወይም ታሪፍ መጣላቸው በተለይ እንደ አውርፓ ህብረት ላሉት ከፍተኛ የንግድ ልውውጣቸው ከአሜሪካ ጋር ለሆኑት አገሮች ትልቅ ዱበዳ ሲሆን፤ ከፍተኛ ቅውስም አስከትሏል።  ሩሲያ በዩሩክሬን ላይ በክፍተችው ጦርነት ምክኒያት በክፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ላሉት የአውርፓ ህብረት አባል መንግስታት ይህ የፕሬዝዳንት ትራም እርምጃ ያልተጠበቀ ነው።

የንግድ አጋሮችን ማስፋት ያስፍለገበት ምክንያት   

 እንደዚህ አይነት እርምጃ ለዘመናት የጋራና የኢኮኖሚና የፖለቲካ መርሆችን ሲያራምዱ በቆዩ አገሮች ቀርቶ በባላንጣ መንግስታ ላይ እንኳ ሊወሰድ የማይገባው ነው በማለት የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያሳለፉትን  የታሪፍ ውሳኔ ቢያንስ እንዲያሻሻሽሉ እየጎተጎቱ ሲሆን፤  ከዚሁ ጋር ግን የአውርፓ ህብረት ከሌሎች አገሮች ጋር ሲካሂዱ የቆዩ የንግድ ድርድሮችን በመቋጨት አዳዲስ ስምምነቶንም በማድረግ አምራጭ የንግድ መስመሮችምና ገበያዎችን እያፈላለገ ነው። ካንድ ወር በፊት ህብረቱ ለአመታት የቆየውን ክደቡብ አሚሪካ አገሮች ጋር የነበረውን የንግድ ድርድር ቋጭቶ ተግብራዊ ማድረግ የጀመረ ሲሆን፤ ባለፈው የጥር ወር መጨረሻ ደግሞ ከህንድ ጋር የንግድ ስምምነት በማድረግ ትልቅ የገበያ ትሥስር መፍጠር ችሏል።

ከህንድ ጋር የተደርሰው ስምምነነት የሁሉም ስምምነቶች እናት ነው ስለመባሉ

ከህንድ ጋር የተደረሰው የንግድ ስምምነት ከሁሉም የላቀና ሁለቱንም ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ፤ የሁለቱን ወገኖች ትብብርም ወደላቀ ደረጃ የሚያሻግር እንደሆነ ነው በህንድና ያውሮፓ ህብረት መሪዎች የተነገረው። ያውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንዴር ሌየን ከስምምነቱ የፊርማ ስነራት በኋላ በሰጡት መግለጫ ተሳክቶልናል ነበር ያሉት፤ “፤ተሳክቶልናል ከሁሉ ስምምነቶች የሚበልጣውንና የስምምነቶች ሁሉ እናት የሆነውን ስምምነት ተፈርርመናል። ይህ ሁለቱ ትልልቆች እኩል ተጠቃሚዎችና አሸናፊዎች የሆኑበትና አጋርነት የመረጡበት ክስተት ነው። ትብብር በአለማችን ላሉ ተግዳሮቶች ዋናው መፍሄ መሆኑንም ያሳየ ነው” በማለት ሌሎች የህንድና አውሮፓ ህብረትን የንግድ ስምምነትን ባራያነት ሊወስዱት እንደሚገባ አሳስበዋል።የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ሚስተር አንቶኒዮ ኮስታ በበኩላቸው ባሰሙት ንግግር የስምምነቱን ታሪካዊነት አጽናኦት ስተዋል። ። በስምምነቱ አውሮፓና ህንድ በንግድ በደህንነትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አዲስ ምራፍ የክፈቱ መሆኑን በ፣እጥቀስ በተለይ በአሁኑ የአለማቀፉ ስራት እየዋዠቀ ባለበት ወቅት ያውሮፓ ህብረትና ህንድ በመተማመን አንድ ላይ የቆሙ መሆናቸው በአራያነት ሊታይ የሚገባው መሆኑን ገልጸዋል።  


የህንድና የአውሮፓ ህብረት የንግድ መጠንየህንድና አውሮፓ ህብረት የሁለትዮሽ  የንግድ ልውውጥ በአመት 180 ቢሊዮን ኢሮ የሚደርስ ሲሆን በዚህ ስምምነት እ እ እ በ2032 በእጥፍ ይጨምራል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በጠቃላይም ለሁለት ቢዮን ወይም የዓለም አንድ አራተኛ ህዝብ የነጻ ገበያ ዕድል ይፈጥራል፤  የዓለምን አጠቃላይ ምርት ጂዲፕ 25 ይሸፍናል ነው የተባለው ።

ባለፈው የጥር ወር መጨረሻ ህብረቱ ከህንድ ጋር የንግድ ስምምነት በማድረግ ትልቅ የገበያ ትስስር መፍጠር ችሏል።
ባለፈው የጥር ወር መጨረሻ ህብረቱ ከህንድ ጋር የንግድ ስምምነት በማድረግ ትልቅ የገበያ ትስስር መፍጠር ችሏልምስል፦ Altaf Hussain/REUTERS

ሁለቱም ወገኖች ከስምምነቱ የሚያገኙት ጠቀሜታ

በተለይ ለአውሮፓ የመኪና ፋብሪካዎች ትልቅ ጠቀሜታ የሚኖረው ሲሆን ክ አንድ መቶ አስር ከመቶ ወደ አስር ከመቶ ታሪፍ ሊወርድ እንደሚችል ነው እየተገለጸ ያለው።  በህንድ በኩል እንደዚሁ 99 ከመቶ በሚሆኑ ከህንድ ወደ አውሮፓ በሚገቡ  ሸቀጦች ላይ ምንም አይነት ታሪፍ እንዳይጠየቅ ወይንም በጣም ዝቅተኛ ታሪፊ ብቻ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ በስምምነቱ ተካቷል ተብሏል።  ነገር ግን ደግም ሁለቱም ወደ የአገሮቻቸው እንዳይገቡ የሚከልክሏቸው የተወሰኑ ሸቀጦች ወይም ምርቶች እንዳሏቸውና ከስምምነት የተደረሰውም ሁለቱም ወገኖች የማይነኩ ወይንም ካንዱ ወዳንዱ ወገን እንዲገቡ በማይፈቅዷቸው ሸቀጠቾ ወይም ምርቶች ላይም በመግባባትና በመስማምት እንደሆነ ተገልጿል።  በጠቃላይ ግን በዚህ ስምምነት ሁለቱ  ትልልቅ የአለም ዴሞክርሲዎች   እያውሮፓ ህብረትና ህንድ ሁለት ቢዮን የሚሆኑ ዚጎቻቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ፣ የአለምን ሰላም የሚያናጋውንና የኢኮኖሚ እድገትን እየገታ ያለውን የዓለም ስራት ለማስተካከል ጭምር በጋራ እየሰሩ መሆኑን  የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ሚስተር አንቶኒዮ ኮስታ አስረድተዋል።፡ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ስምምነት የሚገኘውን ጥቅም በማብራራትም ሶስት ያሉዋቸውን መልክቶች አስተላለፍዋል ።በፊርማ ስነስራቱ ላይ በሰጡት መግለጫ፤ “አንደኛው የአውሮፓ ህብረትና ህንድ ለጋራ ደህንነትና እድገት በአንድነት የቆሙ መሆናቸውና ይህም የተረጋጋ የንግድ ስራት ለመፍጠር አይነተኛ መሳሪያ መሆኑ  ነው፤  ሁለተኛ,የአውሮፓ ህብረትና ህንድበመንግስታቱ ድርጅት ቻርተር መሰረትየዓለማቀፍ ህግን የማክበር ሀላፊነት የለባቸው መሆኑን የሚያምኑ መሆኑ ነው ሶስተኛው፤  አንድ ላይ በመሆን በዓለማቀፍ አጀንዳዎች ግምባር ቀደም ተስታፊዎችና አመራር ሰጭዎች እንደምንሆን መረጋገጡ  ነው” በማለት የአውሮፓ ህብረትና ህንድ ትብብር  ሁለቱ ችግሮችን የሚቋቋም፤ አቃፊና ሚዛናዊ አልማቀፍ ስራት ለመፍጠር በአራአያነት የሚሰሩ መሆኑን  የሚያረግግጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

የስምምነቱ ታሪካዊነት 

ስምምነቱ የብዙዎችን ትኩረት ያገኘውና ታሪካዊም የተባለው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ህንድና አውርፓ ህብረትንጨምሮ በርካቶች አገሮች ወደ አሜሪካ በሚልኳቸው  ምርትና ሸቀጦች ወይም ያግልግሎት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ በመጣል የንግድ ጦርነት በከፈቱበት ወቅት በመሆኑ ነው።። ከአውሮፓ ህብረት ወደ አሜርካ  የሚገቡ ሸቀጦች  በአሁ ወቅት 15 ከመቶ ታሪፍ መክፍል የሚጠበቅባቸው ሲሆን  በህንድ ሸቅጦች ላይ ደግሞ ታሪፉ ከአምሳ ከመቶ በላይ እንደሆነ ነው የሚታወቀው።በሌላ በኩል ግን ከዚህ ስምምነት የተደረሰው የዓለም የንግድ ስራት ስጋት ውስጥ ባለበትና፤  የጂኦፖልቲካ ውጥረቶችም ባየሉበትት ግዚ መሆኑ አሁንም የነጻ ገበያና ንግድ ስራት አዋጭ ብቻ ሳይሆን ለችግሮችም መፍትሄ መሆኑን የሚያመላክት ነው በማለት አገሮች ሰላማቸውንና እድገታቸውን ማረጋገጥ የሚችሉት ነጻ  ገበያንንና ንግድን በመገደብ  ሳይሆን ይልቁንም መሰናክሎቹን በማስወገድ  የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ስምምነቶች  በማድረግ ግብይቱንና ንግዱን በማሳለጥ መሆኑን ይህ ስምምነት አይነተኛ ማሳያ ነው እየተባለ ነው።

 የአውርፓ ህብረት ከሌሎች አገሮች ጋር ሲካሂዱ የቆዩ የንግድ ድርድሮችን በመቋጨት አዳዲስ ስምምነቶንም በማድረግ አምራጭ የንግድ መስመሮችምና ገበያዎችን እያፈላለገ ነው
የአውርፓ ህብረት ከሌሎች አገሮች ጋር ሲካሂዱ የቆዩ የንግድ ድርድሮችን በመቋጨት አዳዲስ ስምምነቶንም በማድረግ አምራጭ የንግድ መስመሮችምና ገበያዎችን እያፈላለገ ነውምስል፦ Altaf Hussain/REUTERS

ስምምነቱ የንግዱን ጦርነት ያበርደው ይሆን?

በዴልሂ ዩንቨርስቲ የህንድና አውሮፓ  ህብረት ጥናት ክፍል ሀላፊ የሆኑት ፕሮፊሰር ኡሙ  ሳላባም ይህ ስምምነት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ ንግድን ለማስፋትና በዶናልድ ትራምፕ ከታወጀው የንግድ ጦርነት ለመላቀቅ የሚረዳ፤ ሁለቱም ወገኖች አሸናፊዎች ሆነው የወጡበት ነው በማለት ትብብርን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።  ፕሮፈሰር ሳላባ ይህ ስምምነት በአሜሪካና  ቻይና እንዴት እንደሚታይና ግብረመልሳቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ሲናገሩም፤ “ ሁሉም የንግድ ስምምንት በድርድር ሰቶ መቀበል ነው።  ሁለት ተደራዳሪዎች ታሪፍ በመቀነስ የሚስማሙ ከሆነ ሌሎች አገሮችም ተመሳሳይ እርምጃዎችን ለመውሰድ ሊገደዱ ይችላሉ” በማለት በዶናልድ ትራምፕ የታሪፍ ፖሊሲስ ላይ አዎንታዊ ተጽኖ ሊኖረው እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋልይህ ብዙ የተባለለት የአውርፓ ህብረትና የህንድ የንግድ ስምምነት በአባል አገሮችና ያውሮፓ ፕርላማ ማለፍና መጽደቅ የሚኖርበት ሲሆን ተግባራዊ ይህናል ተብሎ የሚጠበቅውም እ እ እከ2027 ጀምሮ ነው።  

ገበያው ንጉሴ                                                                                                      
ፀሐይ ጫኔ