ባሕር ዳር የሠፈሩ ተፈናቃዮች አቤቱታ
ከኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈናቅለው አማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ አካባቢ የሠፈሩ ተፈናቃዮች የቀበሌ መታወቂያ ካላመጣችሁ እርዳታ አታገኙም በመባላችን ተቸግረናል አሉ። የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን “የቀበሌ መታወቂያ የማደል ስልጣን የለኝም” ብሏል። የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የእርዳታ ድግግሞሽን ለመቀነስ ለባህር ዳር ተወላጅ ተፈናቃዮች ብቻ እርዳታ እንደሚሰጥ አመልክቷል። ሌሎችም ወደየትውልድ ቀያቸው በመሄድ እርዳታ ሊያገኙ እንደሚችሉ ገልጧል።
ከኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈናቅለው በባሕር ዳር የተለያዩ ቀበሌዎች ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል አንዳንዶቹ “የባሕር ዳር ተወላጅ አይደላችሁም” በመባላችን “እርዳታ እያገኘን አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡የጃራ መጠለያ ጣቢያ ተፈናቃዮች እንግልት
ከ30 ዓመት በላይ በኦሮሚያ ክልል እንደኖሩ የሚናገሩት አንድ ተፈናቃይ ንብረታችን ትተን፣ ህወታችን ይዘን አገር አቋርጠን መጥተን አስፈ፤ጊው እገዛ አልተደረገልንም ብለዋል፡፡
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙት ሌላው ተፈናቃይ በተመሳሳይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ነዋሪነት መታወቂያ ቢኖራቸውም የባህር ዳር ከተማ መታወቂያ ስለሌለኝ እርዳታ አላገኘሁም ብለዋል፡፡
የባህር ዳር መታወቂያ ባይኖረንም መንግስት እንደ ኢትዮጵያዊ ዜግነታችን ሊረዳን ይገባል ሲሉ ነው ተፈናቃዮቹ የመናገሩት፡፡በተፈጠረው ችግር ምክንያት እርዳታ ካገኙ ወራት መቆጠራቸውን ነው ተፈናቃዮቹ በምሬት የሚናገሩት፡፡የአማራ ክልል ተፈናቃዮች
ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የስራ ኃላፊ ተፈናቃዮች ወደ ትውልድ ቦታቸው እየሄዱ እርዳታ እንዲወስዱ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመው ኮሚሽኑ የቀበሌ መታወቂያ የማደል ኃላፊነት ግን እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አስራት ሙጨ ለፀጥታ ሲባል በአንድ ወቅት መታወቂያ መሰጠቱን ጠቁመው ሆኖም አሁን ያ እንደማይሰራ፣ ግን ደግሞ ተፈናቅለው ከሚመጡበት ክልል መታወቂያ ላይ ትውልድ ቦታቸው “ባሕር ዳር” ለሆኑ ተፈናቃዮች እርዳታው ይሰጣል፣ ሌሎችም በየትውልድ ቦታቸው ሄደው እርዳታ ማግኘት ይችላሉ ነው ያሉት፡፡
የወለጋዋ ተፈናቃይ ግን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ያን ማድረግ ስላማይቻል እርዳተው እዚሁ ይሰጠን ብለዋል፡፡የሱዳን ጦር ያፈናቀላቸው ባለሃብቶች ቅሬታ
ከማንነት ጋር በተያያዘ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በነበሩ ግጭቶች ከአንድ ሚሊዮን የማያንሱ ተፈናቃዮች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመጠለያና ከህብረተሰቡ ጋር እንደሚኖሩ ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ