1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ተፈናቃዮች

ዓርብ፣ ነሐሴ 14 2013

ከአማራ ክልል እንደተፈናቃለ ለሚገመተዉ ከ480 ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብን ለመርዳት የክልሉ መስተዳድርና ይመለከታቸዋል ያላቸዉ ወገኖች እየጣሩ መሆኑ ተነግሯል።ይሁንና በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች  በከባዱ ክረምት በመጠለያ፣ምግብና መድሐኒት እጦት እየተሰቃዩ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል

https://p.dw.com/p/3zHZR
Gondar Amhara Region Konflikt Versorgung
ምስል DW/A. Mekonnen

የተፈናቃዮች ስሞታና የርዳታ አቅርቦት በአማራ

ባለፈዉ ጥቅምት ትግራይ ክልል የተቀጣጠለዉ ጦርነት እዚያዉ ትግራይ ዉስጥ ካጠፋዉ ሕይወትና ሐብት በተጨማሪ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅሏል፣አሰድዷልም።ጦርነቱ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ከተዛመተ ካለፈዉ ወር ወዲሕ ደግሞ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል።ከአማራ ክልል እንደተፈናቃለ ለሚገመተዉ ከ480 ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብን ለመርዳት የክልሉ መስተዳድርና ይመለከታቸዋል ያላቸዉ ወገኖች እየጣሩ መሆኑ ተነግሯል።ይሁንና በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች  በከባዱ ክረምት በመጠለያ፣ምግብና መድሐኒት እጦት እየተሰቃዩ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል።

 ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ