1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ጦር ያፈናቀላቸው ባለሃብቶች ቅሬታ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 7 2013

የሱዳን ወታደሮች በተቆጣጠሯቸው ምዕራባዊ የአማራ ክልል አካባቢዎች ከእርሻ ስራቸው ላይ የተፈናቀሉ ባለሀብቶች መንግስት ተገቢውን ድጋፍ አላደረገልንም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። አበዳሪ ባንኮች ቀደም ሲል በእርሻ ኢንቨስትመንት የወሰድነውን ብድር እንድንከፍል በተደጋጋሚ የሚያቀርቡልን ጥያቄ ችግሩን የበለጠ አወሳስቦብናል ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3s42Q
Äthiopien Sudan Grenzgebiet Landwirtschaft
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የሱዳን ጦር ያፈናቀላቸው ባለሃብቶች ተገቢው ድጋፍ አልተደረገልንም አሉ

የሱዳን ወታደሮች በተቆጣጠሯቸው ምዕራባዊ የአማራ ክልል አካባቢዎች ከእርሻ ስራቸው ላይ የተፈናቀሉ ባለሀብቶች መንግስት ተገቢውን ድጋፍ አላደረገልንም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። ከባለሀብቶቹ አንዳንዶቹ በተለይ ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት አበዳሪ ባንኮች ቀደም ሲል በእርሻ ኢንቨስትመንት የወሰድነውን ብድር እንድንከፍል በተደጋጋሚ የሚያቀርቡልን ጥያቄ ችግሩን የበለጠ አወሳስቦብናል ብለዋል። ነገር ግን ጉዳዩ የሚመለከተው የክልሉ መንግስት አካል ግን በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም ። አለምነው መኮንን ከባህርዳር ተከታዩን ዘገባ አድርሶናል። 
አለምነው መኮንን
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ