1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ቴክኒክአፍሪቃ

የዶቼ ቬለ አጭር ሞገድ ስርጭት ስንብት

ሸዋዬ ለገሠ Shewaye Legesse
ዓርብ፣ ጥቅምት 14 2018

ልዩ ዝግጅት የዶቼ ቬለ አጭር ሞገድ ስርጭት ስንብት ዶቼ ቬለ በአጭር ሞገድ በአማርኛ ቋንቋ ሥርጭት ከጀመረ 60 ዓመት አለፈው። ከ30 በላይ በሆኑ የዓለም ቋንቋዎች የሚያሰራጨው ዶቼ ቬለ ከኢንተርኔት እና ሳተላይት ቴክኒዎሎጂ ጋር በተገናኘ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአጭር ሞገድ ስርጭቶችን አቋርጧል።

https://p.dw.com/p/52YJr
ዶቼ ቬለ ስቲዲዮ
ጀርመኗ ቦን ከተማ የሚገኘው የዶቼ ቬለ ስርጭት ስቱዲዮምስል፦ Florian Görner/DW

ልዩ ዝግጅት

 

የዶቼ ቬለ አጭር ሞገድ ስርጭት ስንብት

ዶቼ ቬለ በአጭር ሞገድ በአማርኛ ቋንቋ ሥርጭት ከጀመረ 60 ዓመት አለፈው። ከ30 በላይ በሆኑ የዓለም ቋንቋዎች የሚያሰራጨው ዶቼ ቬለ ከኢንተርኔት እና ሳተላይት ቴክኒዎሎጂ ጋር በተገናኘ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአጭር ሞገድ ስርጭቶችን አቋርጧል። ከፊታችን እሑድ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ ደግሞ የአማርኛው የአጭር ሞገድ ስርጭት እንደሚቋረጥ ሰሞኑን ለመግለጽ ሞክረናል።

ለዚሁ የቴክኒዎሎጂ ሽግግር ሲልም ከአንድ ዓመት በፊት ገደማ ጀምሮ በኢትዮሳት የሳተላይት ስርጭት የጀመረ ሲሆን በዲጂታል አማራጮች ማለትም በፌስቡክ፤ በቴሌግራም፤ እንዲሁም በዩትዩብም የቀጥታ ስርጭቱን እያስተላለፈ ነው።

ራዲዮ
አፍሪቃ ውስጥ በተለይ ገጠር ለሚኖረው ኅብረተሰብ ራዲዮ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ነው። ፎቶ ከማኅደር ምስል፦ Tsvangirayi Mukwazhi/AP/picture alliance

እናም የዶቼ ቬለ አድማጮች ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የሚያገኙን በኢትዮሳት ወይንም (NSS-12) በ10,985.0 ሜጋ ኸርዝ፣ ሆሪዞንታል፣ DW-08 ላይ ይሆናል። ትራንስፖንደሩ፦ ደግሞ MEH 01 ወይንም EAH 01 መሆኑን በድጋሚ ለመግለጽ እንወዳለን። በፌስቡክ፤ በቴሌግራም እና በዩትዩብም በየቀኑ የቀጥታ ስርጭት መተላለፉን ይቀጥላል። ይህን በተመለከተ የአድማጮችን አስተያየት ያካተተውን ልዩ ዝግጅት የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ