1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የዓለም የፕሬስ ነጻነት ሲዘከር የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ምኅዳር

ሰለሞን ሙጬ
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 25 2017

በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ላይ የሚደርሱ ጫናዎች እና የተሻሻለው የመገናኛ ብዙኃን ሕግ የሚዲያ ምኅዳሩን "ከፉኛ ይጎዱታል" ሲል የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ገለፀ። የመብት ተሟጋች ድርጅቱ የፕሬስ ነጻነት ቀንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የመንግሥት አካላት "ነጻና ገለልተኛ የመገናኛ ብዙኃን እንድኖር ጥበቃና ድጋፍ እንድያደርጉ" ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/4ttF3
EHRDC-Logo
ምስል፦ EHRDC

የፕረስ ነጻነት እና የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ያሉበት ሁኔታ

የኢትዮጵያ ወቅታዊ የመገናኛ ብዙኃን ምኅዳር

 

በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ላይ የሚደርሱ ጫናዎች እና የተሻሻለው የመገናኛ ብዙኃን ሕግ የሚዲያ ምኅዳሩን "ከፉኛ ይጎዱታል" ሲል የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ገለፀ። የመብት ተሟጋች ድርጅቱ የፕሬስ ነጻነት ቀንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የመንግሥት አካላት "ነጻና ገለልተኛ የመገናኛ ብዙኃን እንድኖር ጥበቃና ድጋፍ እንድያደርጉ" ጠይቋል።

የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ በበኩሉ "የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተላቸው የልማት ግቦችን እና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ለማሳካት የፕሬስ ነፃነት ትልቅ ሚና ይጫወታል" ብሏል።ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በዓመታዊ የፕሬስ ነጻነት ዘገባው ኢትዮጵያን ባለፈው ዓመት ከነበረችበት 141ኛ በአራት ደረጃዎች ዝቅ ብላ 145ኛ ደረጃ ላይ መሆኗን አስታውቋል።

አሳሳቢ እየሆነ የሄደው የፕረስ ነጻነት ይዞታ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዛሬ ሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ. ም የሚከበረውን የዓለም የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት ቀን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚደርሱ እንደ እሥር፣ እንግልት፣ አሳሪ ሕጎች መውጣት እና መገናኛ ብዙኃን ነጻና ገለልተኛ ሆነው ሥራቸውን እንዳይሰሩ የሚያደርጉ አሉታዊ ጫናዎች አሳሳቢ መሆናቸውን ጠቅሷል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም የመንግሥት  ኃላፊዎች ለነጻና ገለልተኛ መገናኛ ብዙኃን ጥበቃና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀው አሳሳቢ ያሏቸውን ጉዳዮች ዘርዝረዋል።

አሳሳቢው የጋዜጠኞች እስር በኢትዮጵያ

"ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞች በብዛት ይዋከባሉ፣ ይታሠራሉ፣ አንዳንድ ጊዜም በሚዲያ በሠሯቸው ዘገባዎች ብቻ እንደሽብርተኛ ተቆጥረው በሽብር ክስ በየ እሥር ቤቱ ገብተው እንዲሰቃዩ ይደረጋል"

የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ በፊናው "የፕሬስ ነፃነት እጦት መረጃ የማግኘት መብትን እና የመተቸት ነፃነትን ያጓድላል" ብሏል። አክሎም "የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተላቸው የልማት ግቦችን እና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ለማሳካት የፕሬስ ነፃነት ትልቅ ሚና ይጫወታል" በማለት ሕብረቱ "ለነፃ እና ገለልተኛ ጋዜጠኝነትን ያለውን ቁርጥኝነት" እንደሚያረጋግጥ ገልጿል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሳምንት በፊት ማሻሻያው ውድቅ እንዲደረግ ብርቱ ውትወታ ሲደረግበት የቆየውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ አጽድቆታል። ምክር ቤቱ የማሻሻያው ዓላማ "ጠንካራ ተቋም የመመሥረት ጥረት ነው" ቢልም ዘርፉ የሚመለከታቸው እንዲሁም አቶ ያሬድ የሚመሩት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ሥጋታቸውን አሁንም እየገለፁ ነው።

«የጋዜጠኞች መብት ይከበር» የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር

"በጠቅላላ የሚዲያ ነጻነት ኢትዮጵያ ውስጥ አደጋ ውስጥ ነው። ይሄ ነገር በአስቸኳይ እንዲለወጥ፣ እንዲሻሻል ትኩረት እንዲሰጥ ነው [የጠየቅነው]" ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በዓመታዊ የጋዜጠኝነት ነጻነት ዘገባው ኢትዮጵያ ከ180 ሀገራት የባለፈው ዓመት ደረጃዋ በዚህ ዓመት በአራት ደረጃ ወደ ታች ወርዳ 145ኛ ላይ መሆኗን ትናንት ይፋ አድርጓል።

ታምራት ዲንሳ

ሰለሞን ሙጬ