የአሜሪካና አውሮፓ የግሪንላንድ ውዝግብ ጫና ያሳደረበት የዳቮሱ አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጉባኤ
ሐሙስ፣ ጥር 14 2018
በፕሬዝዳንት ትራምፕ የግሪንላንድ ጥያቄ ላይ የተነሳው ክርክርና ተቃውሞ
ፕሬዝዳንት ትራም ቀደም ሲል ግርንላንድ ለአሜርካ ደህንነት ወሳኝ በመሆኗ የአሜሪካ ግዛት አካል መሆን አለባት በማለት እንድትሰጣቸው፤ ካልሆነም በማናቸውም አማራጭ የአሜርካ አካል መሆኗ እንደማይቀር ሲገልጹ ቆይተዋል። የአዎርፓና የኔቶ አባል መንግስታት ግን ይህ የሬዝዳንት ትራም አቋም የኔቶን ህግ የሚጥስና የአትላንቲክ ማዶና ማዶ ግንኑነትን የሚያፈርስ ነው በማለት ተቃውሟቸውን ከመግለጽ በተጨማሪ፤ የተወሰኑ አገሮች ወደ ግሪንላንድ ወታደሮችን በመላክ ጭምር ለዴንማርክ አጋርነታቸውን ገልጸዋል። ሆኖም ግን ትራም ከነዚህ አገሮች ወደ አሜሪካ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ የተጨማሪ ታክስ ውሳኔ በማስተላለፍ የግሪንላድ የይገባኛል ጥያቄያቸው የማይቀለበስ መሆኑን ነው የገለጹት። በዳቮሱ የምጣኔ ሀብት ጉባኤ ተገንተውም ይህንኑ ጥያቄያቸውን አስተጋበተዋል።
ተደረሰበት የተባለው ያልተጠበቀ ስምምነት
ፕሬዝዳንቱ በጉባኤው ባሰሙት ዘለግ ያለ ንግግራቸውየህብረቱና የኒቶ አባል አገራትመሪዎችን ወርፈዋል፤ አውሮፓን ባጠቃይም በአቅመቢስነት ፈርጀዋል፤። ምሽት ላይ ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ በአዋዛጋቢው ግሪንላንድ ላይ ወደፊት አሜሪካ ዴንማርክና ኔቶ ከስምምነት ለመድረስ በሚያስችል ማዕቀፍ ላይ የተስማሙ መሆኑን እራሳቸው ፕሬዝዳንት ትራም በማህበራዊ ገጻቸው ማስታወቃቸው ለብዙዎች እፎይታን አስገኝቷል። ፕሬዝዳንቱ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጀርመንን ፈረንሳይንና ብርታኒያን ጨምሮ በስምንት አገሮች ላይ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ሊጥሉት የነበረውን ታሪፍም ተግባራዊ እንደማይደርጉ አስታውቀዋል።
የስምምነቱ ይዘት
ትራምፕ ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ከኔቶ ዋና ጸሀፊ ሚስተር ማርክ ሩተ ጋር ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ መሆኑ ታውቋል። ማርክ ሩተ ዛሬ ክፕረዝዳንት ትሩምፕ ጋር ያደረጉትን ውይይት ይዘት ሲገልጹ” ትናንት ያደረግነው ውይይት በጣም ጠቃሚና ባጠቃላይም የኔቶ አገሮችና አሜርካ ጭምር የአርክቲክ አካባቢ ከሩሲያና ቻይና ስጋት ነጻ ስለሚሆንበት ነው” በማለት በግሪንላንድም ቻይናና ሩሲያ ምንም አይነት የኢኮኖሚና ወታደራዊ እንቅሳቅሴ እንዳይኖራቸው ማድረግ ላይ ያተኮረ እንደህነ ገልጸዋል። ፕሬዝዳን ትራምፕም ስምምነቱ የረጅም ግዜ ሂደት እንደሆነ አስታውሰው የኔቶ ዲነማርክና አሜርካ ሉካን ውይይት እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል ።
ስምምነቱ የፈጠረው የዕፎይታ ስሜት
የአውሮፓና የስሜን አትላንቲክ አገሮች ባጠቃላይ ሲስማሙ የተስማሙበት የግሪናልድ ጉዳይ ግልጽ ባይሆንም ጥያቄው ግን ከሀይል መልስ በውይይትና ድርድር እንዲመለስ ከስምምነት መደረሱ ባውሮፓና የነኔቶ ባል አመንግስታት ዘንድ ኧፎይታን አስገኝቷል። የተነቃነቀውን የኔቶና የአውሮፓና አሜርካ ግንኑነትንም ከመፈርስ ያዳነ ተደርጎ ተወስዷል። ሆኖም ግን የተፈጠረው ክስትት በተለይ ያውሮፓና አሜርካ ግንኙነት ላይ ጠባሳ ትቶ እንደሚያልፍ ነው በብዙዎች የሚነገረው። በጀርመን ቤርቴልስማን ስቲፈንግ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ብራንዶን ቦህን ስምምነቱ “ እ እ እ በ1951 ም ጀርመና ዴማርክ የደርሱበትን የመካለክያ ስምምነት ላይ እንደገና ለመደራደር ያለመ ነው። ይህን ከዚህ ሁሉ ሳይደረስ ማድረግ ይቻል ነበር” በማለት የደረሰው ጉዳት ቀላል እንዳልሆነ ገልጸዋል።
አሸናፊና ተሸናፊ
በዚህ ተደረሰ በተባለው ስምምነት አሸናፊው ማን ሊሆን እንደሚችል ተጠይቀው ሲመልሱም፤ “ የአሜሪካ ፍላጎት በአርክቲክ ክልል ወታደራዊ ይዞታ እንዲኖራት ነው፤ በዚህ በኩል ተሳክቶላት ሊሆን ይችላል። ግን ይህ ስምምነት ቀደም ሲል የነበረ በመሆኑ አዲስ ነገር የለውም። በአውሮፓውያን በኩልም እንደ ድል ሊወሰድ ይችላል፤ ምክኒያቱም አውሮፓውያን ክተባበሩና ከጸኑ የሚደርስባቸውን ማናቸውንም ጫና መቆቁቋም እንደሚችሉ አሳይተዋል” ብለዋል።
ዛሬ ማምሻውን እዚህ ብራስልስ በመካሄድ ላይ ያለው ያአውሮፓ ህብረት የመሪዎች አስቸኳይ ጉባኤም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀለበሱት የተባለው የግሪንላድ ጥያቄ ቀጣይ ሂደት ላይና ሊሎች አጣዳፊ አጅንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳልፎ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ