1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ኢራን ለሟቹ አያቶላህ አሊ ካሜኒ የስድስት ቀናት የሽኝት ሥነ ስርዓት ዛሬ በይፋ ጀመረች

ቅዳሜ፣ ሰኔ 27 2018

ኢራን ለሟቹ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ ከዛሬ ጀምሮ ለስድስት ቀናት የሚዘልቅ ህዝባዊ የሀዘን ሥነ ሥርዓት በይፋ መጀመሯን የሀገሪቱ የመንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል።ካሜኒ በጎርጎሪያኑ የካቲት 28 ቀን 2026 ዓ ም ቴህራን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ላይ በተደረገ የጋራ የአየር ጥቃት ነበር የተገደሉት።

https://p.dw.com/p/5GZih
ቴህራን፤የአያቶላህ ካሚኒ የሽኝት ሥነስርዓት
በ86 ዓመታቸው በእስራኤል እና በአሜሪካ የአየር ድብደባ የተገደሉት  ካሜኒ ኢራንን ከጎርጎሪያኑ 1989 ዓ ም ጀምሮ እስከ ዕለተሞታቸው ድረስ  መርተዋል። ምስል፦ Mohammed Salem/REUTERS

ኢራን ለሟቹ መንፈሳዊ  መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ የስድስት ቀናት ህዝባዊ የሽኝት  ሥነ ስርዓት በይፋ ጀመረች።ኢራን ለሟቹ መንፈሳዊ  መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ ከዛሬ ጀምሮ ለስድስት ቀናት የሚዘልቅ ህዝባዊ የሀዘን ሥነ ሥርዓት በይፋ መጀመሯን የሀገሪቱ የመንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል።ካሜኒ በጎርጎሪያኑ የካቲት 28 ቀን 2026 ዓ ም ቴህራን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ላይ በተደረገ የጋራ የአየር ጥቃት ነበር የተገደሉት።ይህም አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ  ጦርነት የጀመሩበት  ቀን ነበር።

የበቀል ምልክት የሆነውን ቀይ ባነር የያዙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሐዘንተኞች የቴህራንን ሰፊ የግራንድ ሞሳላ ሃይማኖታዊ ሕንፃ ግቢ ሞልተው የካሜኒ አስከሬን እስኪመጣ ድረስ ሲጠባበቁ እንደነበር የፈረንሳዩ የዜና ወኮል የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ  ጋዜጠኛ ተመልክቷል። ሐዘንተኞች የካሜኔይ እና በአየር ድብደባው የተገደሉት ቤተሰቦቻቸው አስከሬን በቦታው ሲደርስ ከምሬት ለቅሶ ባሻገር “ቃላችን አንድ ነው! ይህም በቀል! በቀል!” ነው የሚል መፈክር በተደጋጋሚ ማስተጋባታቸውን ዘገባው አመልክቷል።እንደ ዘገባው በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኑት የኢራን ከፍተኛ ተደራዳሪ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ በሚገኘው የባህር ወሽመጥላይ የጋራ ቅኝት  ሊጀመር እንደሚችል  አስተያየት ለሰጡት ለፈረንሳይ እና ለብሪታኒያ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ኢራን ህራን ፤ የአያቶላህ ካሚኒ ሽኝት
በሽኝት ሥነስርዓቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን ተገኝተዋል።ምስል፦ Mohammed Salem/REUTERS

 

የካሜኔይ አስከሬን  እስከ መጭው ሰኞ ቴህራን  የሚቆይ ሲሆን፤ ሐሙስ ዕለት በሰሜን ምስራቅ ኢራን በምትገኘው ማሽሃድ ከተማ ግብዓተመረታቸው ከመፈፀሙ በፊት፤ ለሺዓ ሙስሊሞች ቅዱስ ወደሆነችው ከተማ  ወደ ኩም እንዲሁም ወደ ጎረቤት ኢራቅ እንደሚወሰድ ዘገባው አመልክቷል።በሀዘን ሥነ ሥርዓቱ ወቅት የኢራን የአየር ክልል እና ከተማ ውስጥ ያሉ በርካታ  መንገዶች ለደህንነት ሲባል ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተብሏል።

ለካሜኔይ ሽኝት የፓኪስታን፣የሩሲያ፣የቻይና፣ የህንድ እና የአፍጋኒስታን ተወካዮች እና በእስራኤል ጥቃት የተገደለው የሂዝቦላህ መሪ የሃሰን ናስራላህ የቤተሰብ አባላት ተገኝተዋል።በካሚኒ እግር የተተኩት ሞጅታባ ካሜኔይ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደሚገኙ አላረጋገጡም። ለወራትም በይፋ አልታዩም።

በ86 ዓመታቸው በእስራኤል እና በአሜሪካ የአየር ድብደባ የተገደሉት  ካሜኒ ኢራንን ከጎርጎሪያኑ 1989 ዓ ም ጀምሮ እስከ ዕለተሞታቸው ድረስ  መርተዋል። 

 

ፀሐይ ጫኔ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ