1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጎ ፈቃደኛዋ ሲስተር ካሕሳ ሓጎስ ተሸለሙ

ረቡዕ፣ ግንቦት 7 2016

ሲስተር ካሕሳ ሓጎስ፥ ለተደፈሩ እና የተለያዩ የፆታ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች በጦርነቱ ወቅት እንዲሁም በኃላ እያደረጉ ላለው ድጋፍ በካናዳ መንግስት እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ሲስተር ካሕሳ እርሳቸው ባቋቋሙት እና በሚመሩት በበጎ ፍቃደኝነት የሚተገበር የፆታ ጥቃት ተጎጂዎችን የመደገፍ ስራ ከ400 በላይ ሴቶች አገልግሎት ማግኘታቸው ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/4fsd5
ሲስተር ካህሳ ሓጎስ  ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ
ሲስተር ካህሳ ሓጎስ ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ ምስል Million Hailesilassie/DW

በጎ ፈቃደኛዋ ሲስተር ካሕሳ ሓጎስ ተሸለሙ

ሲስተር ካሕሳ ሓጎስ በካናዳ መንግስት የሚዘጋጀውን የዓለም የሴቶች፣ ሰላምና ድህንነት ዓለምአቀፍ ሽልማት አሸነፉ። ሲስተር ካሕሳ ሽልማት የተበረከተላቸው በትግራዩ ጦርነት ወቅት የፆታ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እና እናቶች በበጎ ፍቃደኝነት በመደገፍ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ነው ። ሲስተር ካሕሳ  በትግራይ ክልል ዓዲግራት ከተማ በግል ተነሳሽነት ባቋቋሙት የፆታ ጥቃት ተጎጂዎች እንክብካቤ ማዕከል ከ400 በላይ የፆታ ጥቃት ተጎጂዎች ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተገልጿል። ትናንት በመቐለ በተደረገ ስነስርዓት ሲስተር ካሕሳ ከካናዳ ዓለምአቀር ልማት ሚኒስቴር የእውቅና ሽልማት ተቀብለዋል።ጾታዊ ጥቃት እና ማህበራዊ ችግር ያብቃ ፤ የትግራይ ሴቶች
በትግራዩ ጦርነት ወቅት በበርካታ ሴቶች ላይ ፆታዊ አመፅ መፈፀሙ እና ለተጎጂዎችም የሕክምና ድጋፍና ከለላ እንዲሁም ፍትሕ አለመሰጠቱ በተለያዩ ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጾታዊ ጥቃት እና ማህበራዊ ችግር ያብቃ ፤ የትግራይ ሴቶች እንዲሁም በፆታ ጉዳይ የሚሰሩ የሀገር ውስጥ እና ውጭ ተቋማት ሲገለፅ የቆየ ነው። ለነዚህ የፆታ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች በትግራይ ድጋፍ የሚያደርጉ የተወሰኑ ተቋማት ስራ ላይ ይገኛሉ። ከመካከላቸው በዓዲግራት ከተማ  ዋን ስቶፕ ሴንተር በተባለው ማዕከል የሚሰሩት ሲስተር ካሕሳ ሓጎስ፥ ለተደፈሩ እና የተለያዩ የፆታ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች በጦርነቱ ወቅት እንዲሁም በኃላ እያደረጉ ላለው ድጋፍ በካናዳ መንግስት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።የጦርነት ሰለባዎቹ ሴቶች ሰቆቃ ትላንት በመቐለ በተደረገ ስነስርዓት ከካናዳ የዓለምአቀፉ ልማት ሚኒስተር ሽልማት የተቀበሉት ሲስተር ካሕሳ እርሳቸው ባቋቋሙት እና በሚመሩት በበጎ ፍቃደኝነት የሚተገበር የፆታ ጥቃት ተጎጂዎች የመደገፍ ስራ ከ400 በላይ ሴቶች አገልግሎት ማግኘታቸው ተነግሯል።

ሲስተር ካህሳ ሓጎስ  ከሸላሚው ድርጅት ሃላፊዎችና ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር
ሲስተር ካህሳ ሓጎስ ከሸላሚው ድርጅት ሃላፊዎችና ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ምስል Million Hailesilassie/DW

 
ሲስተር ካሕሳ" በሽልማቱ ደስታ ተሰምቶኛል፣ ከዛ በላይ ደግሞ የተፈጠረው ሁኔታ በጣም ነው ያሳዘነኝ። ወደ ኃላ ተመልሼ እንዳይ እና መጥፎ ስሜት እንዲሰማኝ አድርጎኛል፤ ለሸልማት ብዬ የሰራሁት ስራ አልነበረም።ፍትህ ለጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች እንደትግራወይቲ ሚናዬ መወጣት አለብኝ በማለት የሰራሁት ነው። የተገፉ ሴቶች መጠልያ እንዲያገኙ እንክብካቤ እንዲያገኙ በሙያዬ ሞክሬአለሁ፤ በስራዬ የሴቶች ጉዳይ እንዲሁም ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ደግፈዋል። ሴቶች እናቶች ሚስጥራቸው ተጠብቆ፣ መቆያ ቤቱ የት መሆኑ ሳይታወቅ - ብዙዎች ድነው የወጡበት ሁኔታ ነበረ" ብላዋል።
በጦርነቱ ወቅት በትግራይ የተፈፀመው ሴቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ማንም ላይ ሊደገም የማይገባው፣ ዓለም ሊያወግዘው የሚገባ አስነዋሪ ድርጊት ነው የሚሉት ሲስተር ካሕሳ ለፆታዊ ጥቃት ተጎጂዎችም አስፈላጊ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪ የተሰጣቸው እውቅና በጎ ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያነሳሳቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ለሲስተር ካሕሳ ሽልማት ያበረከቱት የካናዳው ዓለምአቀፍ ልማት ሚኒስቴር አሕመድ ሑሴን የሕክምና ባለሙያዋን ተምሳሌት የሚሆኑና ለሰው ልጆች መብት ዘብ የቆሙ በማለት አድናቆታቸውን ገልፀውላቸዋል።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ