1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካእስያ

ሩስያ የዩክሬን 4 ግዛቶችን መጠቅለሏ

ዓርብ፣ መስከረም 20 2015

ሩስያ የዩክሬን አራት ግዛቶችን በይፋ ጠቅልላ ወደ ግዛቶቿ ማስገባቷን ይፋ አድርጋለች። የሩስያ ድርጊት፦ «ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጥስ ጥቅለላ» ነው በሚል በምዕራባውያን ሃገራት ዘንድ ብርቱ ተቃውሞ አስከትሏል። ሩስያ በከፊል በተወረሩት የዩክሬን አራት ግዛቶች ውስጥ በ«ሕዝበ ውሳኔ» አብዛኛው መራጭ ወደ ሩስያ መጠቃለል እንደሚሻ ዐሳይቷል ብላለች።

https://p.dw.com/p/4HbJb
የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በፓርላማ ንግግር እያሰሙ
ምስል Grigory Sysoyev/Kremlin/Sputnik/REUTERS

ግዛቶቹ ዶኒዬትስክ፣ ሉሃንስክ፣ ኬህርሶንና ዛፖሪዢያ ናቸው

ሩስያ የዩክሬን አራት ግዛቶችን በይፋ ጠቅልላ ወደ ግዛቶቿ ማስገባቷን ይፋ አድርጋለች። የሩስያ ድርጊት፦ «ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጥስ ጥቅለላ» ነው በሚል በምዕራባውያን ሃገራት ዘንድ ብርቱ ተቃውሞ አስከትሏል። ሩስያ በከፊል በተወረሩት የዩክሬን አራት ግዛቶች ውስጥ በ«ሕዝበ ውሳኔ» አብዛኛው መራጭ ወደ ሩስያ መጠቃለል እንደሚሻ ዐሳይቷል ብላለች። ሩስያ «ሕዝበ ውሳኔ»ውን አካኺጄባቸዋለሁ ያለቻቸው የዩክሬን ግዛቶች፦ ዶኒዬትስክ፣ ሉሃንስክ፣ ኬህርሶን እና ዛፖሪዢያ ናቸው። የዩክሬን መንግሥት እና ምዕራባውያን ምርጫው የተኪያኼደው በወረራ ውስጥ ነው እናም ማንንን የማይወክል የዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው ሲሉ ኮንነውታል። 

ሩስያ በወረራ በያዘቻቸው የዩክሬን አራት ግዛቶች ውስጥ ያደረገችው ምርጫ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንጻር እንዴት ይታያል?የምዕራባዉያን እና የሩስያ ዉዝግብ

የሩስያ ፕሬዚደንት ብላድሚር ፑቲን ከተጠቀለሉት አራቱ የዩክሬን ግዛትቶች መሪዎች መሀል ቆመው
ምስል Mikhail Metzel/AP Photo/picture alliance

ምርጫው በዩክሬን መንግሥት እና ምዕራባውያን ውድቅ ተደርጎ ቢኮነንም የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ለሀገራቸው ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር አራቱን ግዛቶች ወደ ሩስያ ለመቀበል ዕቅድ እንዳላቸው መግለጣቸውን የምክር ቤቱ ታዕታይ ክፍል ዐሳውቋል። የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እና የቭላድሚር ፑቲን ቀኝ እጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ቪያቼስላቭ ቮሎዲን በሩስያ ምክር ቤት ማለትም ዱማ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ላይ እንደጻፉት ከሆነ ፕሬዚደንቱ ከአራቱ ግዛቶች ሩስያን እንቀላቀል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል ብለው መጻፋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። በኋላ ላይም የአራቱ ግዛት መሪዎች ከብላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉት የፊርማ ስነሥርዓት ተከናውኗል። በመቀጠል ምንድን ነው የሚሆነው? ከዩክሬን አጠቃላይ ስፋት 15 በመቶ የሚሸፍኑት እነዚህ ግዛቶቹ ወደ ሩስያ ተጠቃለሉ ማለት ነው?

ዩክሬን፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ምዕራባውያን ሃገራት ሩስያ ግዛቶቹን ለመጠቅለል የኼደችበትን መንገድ ተቃውመው አውግዘዋል። ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላሉ?

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ