1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ዲጂታል ዓለምአፍሪቃ

የ«ፋይዳ» ዲጂታል መታወቂያ፡ በቴክኖሎጂ እድገት እና በዜጎች መብት መካከል ያለው ሚዛን

ሐና ደምሴ
ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2018

መንግስት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን በሚል «ፋይዳ» የተሰኘውን ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ከባንክ አገልግሎቶች ጋር በግዴታ እያስተሳሰረ ይገኛል ። ። ይህ አሠራር የፋይናንስ ስርዓቱን ደህንነት እንደሚያጠናክር ቢነገርም፤ ሂደቱ እንዲሁም ፍጥነቱ የመረጃ ደኅንነት ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው ።

https://p.dw.com/p/5AHf7
መንግስት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን በሚል የተገበረው «ፋይዳ» ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ
መንግስት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን በሚል «ፋይዳ» የተሰኘውን ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ከባንክ አገልግሎቶች ጋር በግዴታ እያስተሳሰረ ይገኛል ምስል፦ Privat

ስለ «ፋይዳ» ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚዎች ምን ይላሉ?

መንግስት የኢትዮጵያ  ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን በሚል «ፋይዳ» የተሰኘውን ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ከባንክ አገልግሎቶች ጋር በግዴታ እያስተሳሰረ ይገኛል ። ከቅርብ ግዜ ወዲህ የኢትዮ ቴሌ ኮም አካል የሆነው ቴሌ ብር ደንበኞቹ የብሔራዊ መታወቂያቸውን እንዲያያይዙ እየጠየቀ ነው ።

ይህ አሠራር የፋይናንስ ስርዓቱን ደህንነት እንደሚያጠናክር ቢነገርም፤ ሂደቱ እንዲሁም ፍጥነቱ የመረጃ ደኅንነት ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው ።  መንግስት ይህንን ግዴታ የጣለው የአንድ ሰው አንድ ማንነት ስርዓትን ለመዘርጋት፣ መሆኑን ደጋግሞ ሲገልፅ ይሰማል ። ተጠቃሚዎች ግን ስጋት አላቸው ።

የተጠቃሚዎች ስጋት ፋይዳ አንድም ይህንን ሁሉ የግል መረጃ ለማይገባው አካል አሳልፎ መ ስጠት ላልተፈለገ አካል እራስን ያጋልጣል በሚል ነው ።  በሌላ  በኩል ደግሞ መንግስት ያልተገባ ቁጥጥር እና ክትትል ሊያደርግብን ይችላል የሚል ነው። ሁሉም የመንግስት አገልግሎቶችን ለማግኘት ፋይዳ መታወቂያ  ግድ እንደሚለው ሁሉ የትኛውንም የባንክ አገልግሎት ለማግኘትም  ይህ ብሔራዊ መታወቂያ ግድ ይላል ። በተለይ በገጠር የሚኖሩ፣ የቴክኖሎጂ ዕውቀት የሌላቸው እና አረጋውያን ላይ ሊፈጥር የሚችለው ጫና እንዳለ ሆኖ ።

ሌሎች ደግሞ የመረጃ ደህንነት ስጋት አለባቸው ። መንግስት በእጁ ያለውን የዜጎች የግል መረጃ በምን መልኩ ይጠበቃል? ለሦስተኛ ወገን ባንኮች የሚጋራው መረጃ እስከምን ድረስ እንደሆነ ማወቅ አንችልም ይላሉ ያነጋገርኩዋችው ግለሰቦች ።

መንግሥት «አንድ ሰው - አንድ ማንነት» የሚለውን መርህ መከተሉ የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከል ይረዳል ። ሆኖም፣የዜጎች እጅግ ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎች በአንድ ቋት ውስጥ ሲቀመጡና ለባንኮች ሲጋሩ፣ የመረጃው ደህንነትእንዴት ይጠበቃል?  የሚለው ስጋት አሁንም ምላሽ አላገኘም። የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሌለውከሆነ፣ ዜጎች በዲጂታል ሥርዓቱ ላይ ያላቸው እምነት ሊሸረሸር ይችላል።

የፋይዳ መታወቂያ በራሱ ችግር አይደለም፤ ችግሩ ያለው  በአተገባበሩና በዜጎች ዘንድ ያለውን ስጋት በመቅረፍ ረገድበሚታየው የግልጽነት ጉድለት ነው። የዲጂታል ሽግግር ስኬት የሚለካው በቴክኖሎጂው ውስብስብነት ሳይሆን፣ ዜጎችበሥርዓቱ ላይ በሚኖራቸው አመኔታና በሚያገኙት እኩል ተጠቃሚነት ነው።

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ አግዚአብሔር