1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካናዳ መንግሥት እርዳታ ለቀድሞ ተዋጊዎች

ረቡዕ፣ ግንቦት 7 2016

የካናዳ አለምአቀፍ ልማት ሚኒስቴር አሕመድ ሐሰን በመቐለ እንዳስታወቁት፥ በሀገር ደረጃ ሂደት ላይ ላለ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደሰላማዊ ሕይወት የመመለስን ስራ ለመደገፍ ሀገራቸው 14 ሚልዮን ዶላር መድባለች።ገንዘቡም በተመድ የልማት ፕሮግራም በኩል በመላ ሀገሩቱ ትግራይን ጨምሮ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ የሚያስችል ነው።

https://p.dw.com/p/4ftS6
የካናዳ መንግሥት ልዑካን በመቀሌ
የካናዳ መንግሥት ልዑካን በመቀሌ ምስል Million Hailesilassie/DW

የካናዳ መንግሥት እርዳታ ለቀድሞ ተዋጊዎች

የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ እና ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ 14 ሚልዮን ዶላር መመደቡ አስታውቋል። ይህ የተገለፀው የካናዳ ዓለምአቀፍ ልማት ሚኒስቴር በመቐለ በነበራቸው የስራ ጉብኝት ነው። ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በኃላ ይተገበራል የተባለው የቀድሞ ተዋጊዎችን በመደገፍ ወደ ሰላማዊ ሕይወት የመመለስ ስራ በተለያዩ ምክንያቶች የታቀደውን ያክል ሊሳካ እንዳልቻለ ይገለፃል።የቀድሞዉ የህወሓት ተዋጊዎች አቤቱታ

ትላንት በመቐለ ጉብኝት ያደረገው የካናዳ መንግስት ልዑክ ትኩረት ካደረገባቸው አጀንጃዎች መካከል የቀድሞ ተዋጊዎች ያሉበትን ሁኔታ መመልከት እና ቀጣይ ድጋፍ ማድረግ አንዱ ነበር። የካናዳ መንግስት ልዑክ የመሩት የካናዳ አለምአቀፍ ልማት ሚኒስቴር አሕመድ ሐሰን በመቐለ እንዳስታወቁት፥ በሀገር ደረጃ ሂደት ላይ ላለ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደሰላማዊ ሕይወት የመመለስን ስራ ለመደገፍ ሀገራቸው 14 ሚልዮን ዶላር መመደብዋን አስታውቀዋል።

75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ከኅብረተሰቡ ጋር ሊቀላቀሉ ነው ተባለሚኒስትሩ "ከቀድሞ ተዋጊዎቹ የተረዳሁት፥ ለሰላም፣ ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው እና ሕብረተሰባቸው መፃኢ መልካም ሁኔታ ቁርጠኛ መሆናቸው ነው። የካናዳ መንግስት ከሀገራዊ ተሃድሶ ኮምሽን እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም በጋራ በመሆን በሂደት ያለው የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ኑሮ የመመለስ ስራ እያገዛ በቅርበት እየተከታተለ ነው። ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም በኩል በመላ ሀገሩቱ ትግራይን ጨምሮ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ የሚያስችል 14 ሚልዮን ዶላር መመደቡ ማስታወቅ እፈልጋለሁ" ብለዋል።

የካናዳ መንግሥት ልዑካን በመቀሌ
የካናዳ መንግሥት ልዑካን በመቀሌ ምስል Million Hailesilassie/DW

በትግራይ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የቀድሞ ተዋጊዎች፥ ከትግራይ ሐይሎች ከተሰናበቱ በኃላ የተደረገላቸው ድጋፍ እንደሌለ በማንሳት ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበረ ይታወሳል።ከዚህ ውጭ ካናዳ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ፥ በጦርነቱ ይበልጥ በተጎዳችው ትግራይ የሚከወኑ የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ለማጠናከርም የገንዘብ ድጋፍ እንደምታደርግ የካናዳው ዓለምአቀፍ ልማት ሚኒስቴር ገልፀዋል። ለቀድሞ ተዋጊዎች አቀባበል ተደረገጦርነቱ በትግራይ ያደረሰውን የከፋ ሁኔታ እንደሚረዱት ሚኒስቴሩ አሕመድ ሐሰን ጨምረው ተናግረዋል። ሚኒስትሩ "ሁሉም እንደሚያውቀው በ2020 ዓመተምህረት በትግራይ ግጭት ተነስቶ በመቶ ሺዎች ተገድለዋል። በርካቶች ተጎድተዋል ተፈናቅለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች አሰቃቂ ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። እንደ ካናዳ የምናስበው ግጭት ሲከሰት ሴቶች የበለጠ ይጎዳሉ" ብለዋል።በትግራይ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የሚከወኑ ስራዎች ለማገዝም ካናዳ 65 ሚልዮን ዶላር በተባበሩ መንግስት ድርጅት በኩል ድጋፍ እንደምታደርግ ሚኒስቴሩ ገልፀዋል።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ