የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና የመንግስት ምላሽ
ማክሰኞ፣ ጥር 24 2014
ማስታወቂያ
ሰሞኑን የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ከመንግስት ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር መጀመራቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ስለጉዳዩ ማረጋገጫ የተጠየቁት የመንግሰት ኮሚዩኒኬሽ አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መንግስት ሰላምን ለሚያመጣ የትኛውም አማራጭ በሩ ክፍት መሆኑን ገልፀው፤ እስካሁን ከህወሓት ጋር የተደረገ ንግግር አለመኖሩን ግን አስረድተዋል፡፡
ሰሞኑን በትግራይ እና አፋር አዋሳኝ ወረዳዎች ስላገረሸው ጦርነት ተጠይቀው በተለይም ለዶይቼ ቬለ ማብራሪያ የሰጡት ሚኒስትሩ አሁን ላይ ጦርነቱ እንዳይስፋፋ መገታቱንም ገልጸዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ