1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሮብ አኒና ሲቪል ማህበረሰብ አቤቱታ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 17 2016

ከ60 በመቶ በላይ የኢሮብ ወረዳ አካባቢ በኤርትራ ተይዞ ይገኛል፤ ለዚህ የኢትዮጵያ መንግስት መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል ሲል ኢሮብ አኒና ሲቪል ማሕበረሰብ ገለፀ። ሲቪል ማሕበረሰቡ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ እና የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በላከው ግልፅ ደብዳቤ መንግስት አደጋ ላይ ያለው የኢሮብ ብሔረሰብ ይታደግ ብሏል።

https://p.dw.com/p/4e8rv
Karte Äthiopien Region Tigray DE

የኢሮብ የሲቪል ማህበረሰብ ለጠቅላይ ሚንስትሩ የጻፉት ግልጽ ደብዳቤ

ከ60 በመቶ በላይ የኢሮብ ወረዳ አካባቢ በኤርትራ ኃይሎች ተይዟል

ከ60 በመቶ በላይ የኢሮብ ወረዳ አካባቢ በኤርትራ ተይዞ ይገኛል፤ ለዚህ የኢትዮጵያ መንግስት መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል ሲል ኢሮብ አኒና ሲቪል ማሕበረሰብ ገለፀ። ሲቪል ማሕበረሰቡ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ እና የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በላከው ግልፅ ደብዳቤ መንግስት አደጋ ላይ ያለው የኢሮብ ብሔረሰብ ይታደግ ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ተቃዋሚው ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፥ የኢትዮጵያ መንግስት በአልጀርሱ ውል ላይ ያንፀባረቀው የቅርብ ግዜ አቋም ኮንኗል።

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ ጦርነቱ ቆሞ አንፃራዊ ሰላም በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ሰፍኖ፥ መደበኛ እንቅስቃሴ በከፊል የሚታይ፥ ከኤርትራ ጋር በምትዋሰነው፣ በትግራይ ምስራቃዊ ዞን በምትገኘው፣ በዋነኝነት የኢሮብ ብሄረሰብ መኖርያ በሆነችው ኢሮብ ወረዳ ግን አሁንም በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስራ ሆና፥ የነበሩ ሁሉም የመንግስት አገልግሎቶች ተቆርጦ፣ ህዝቡ በአስከፊ ሁኔታ መቀጠሉ ይገለፃል። አናሳ ቁጥር ያለው የኢሮብ ብሄረሰብ በተለይም ጦርነቱ ተከትሎ በደረሰበት ጥፋት በከፍተኛ የህልውና አደጋ ላይ ይገኛል የሚለው ፥ በብሄረሰብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ዙርያ ለመስራት መቋቋሙ የሚገልፁ ኢሮብ አኒና ሲቪል ማሕበረሰብ፥ አሁን ላይ ከአጠቃላይ ኢሮብ 60 በመቶ የሚሆነው በኤርትራ ጦር ስር ሆኖ፣ ህዝቡ ያለ መሰረታዊ የሕክምና፣ ትምህርት፣ ባንክ እና ሌሎች አገልግሎቶች እየኖረ ፥ ጥቂት የማይባለው ደግሞ ከቀዬው ተሰዶ በመጠልያዎች እንዳለ ባወጣው መግለጫ አትቷል። ኢሮብ አሁንም በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር ነዉ-ነዋሪዎች

በኢሮብ የሰብአዊ እርዳታ መድረስ አልቻለም

ያነጋገርናቸው የኢሮብ አኒና ሲቪል ማሕበረሰብ አመራር የሆኑ አቶ አለማ ጊደይ የኢሮብ ብሄረሰብ፥ ሰብአዊ እርዳታ እንኳን እንዳይደርሰው በኤርትራ ጦር በሐይል ተይዞ፥ አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ያነሳሉ። አቶ አለማ "ከዛላምበሳ ወደ ኢሮብ ዓሊቴና፣ ደውሃን የሚወስደው ዋናው መንገድ በሻዕቢያ ተዘግቷል። ይህ ያደረጉት ደግሞ በሐሳብ ከተሰመረው አስር ኪሎሜትር አልፈው ገብተው ነው። ሰብአዊ እርዳታ እንኳን ቢኖር ግማሽ እዛ ለቀረው ህዝብ ሊደርስ አይችልም" በማለት ያለው የከፋ ሰብአዊ ሁኔታ ገልፀዋል።

ኢሮብ አኒና ሲቪል ማሕበረሰብ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር እና ለትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ብሎ በፃፈው ግልፅ ደብዳቤ፥ ከሶስት ዓመት በፊት ጦርነቱ ሲጀመር ወደ ኢሮብ ወረዳ የገባው የኤርትራ ጦር እንዲወጣ፣ በረሃብ፣ በአገልግሎቶች መቋረጥ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ያለው ህዝብ አስፈላጊ ድጋፍ እንዲደረግለት፣ ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ፣ በግድ ተጠልፈው ወደ ኤርትራ የተወሰዱ ሰላማዊ ሰዎች ያሉበት ሁኔታ እንዲታወቅ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።የትግራዩ ጦርነት እና የነዋሪዎች የሰላም ጥሪ

ኢሮብ በታሪክ የኤርትራ ግዛት ሆኖ አያውቅም

በሌላ በኩል ኢሮብ በታሪክ የኤርትራ ግዛት ሆኖ አያውቅም ያለው ትላንት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ መግለጫ ያወጣው ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፥ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ከኢሮብ ጨምሮ ከጉሎመኸዳ፣ ዛላምበሳ፣ እገላ፣ ባድመ እና ሌሎች አካባቢዎች የኤርትራ ጦር ማስወጣት ሲገባው፥ በአልጀርስ ውል መሰረት ለኤርትራ ተላልፈው የተሰጡ አድርጎ ወስዶ አቋም መያዙ ኮንኗል። በመሰረቱ የአልጀርሱ ውል አንድ የሆነው የኢሮብ ብሄረሰብ ለሁለት የሚከፍል ነው ያለው ዓሲምባ፥ የኤርትራ መንግስት የአልጀርሱ ውል በመጣስ በትግራይ ላይ ወረራ መፈፀሙ ተከትሎ ውሉ የፈረሰ እንደሚያደርገው ገልጿል።

ሊቀመንበሩ ጨምረውም የድንበር ጉዳዮች የሚወሰኑ ከሆነም በህዝብ ተሳትፎ፣ በህዝብ ፍላጎት ብቻ መሆን እንዳለበት ይገልፃሉ። የኢሮብ ሕዝብ ተቃዉሞ

"ሰዎች ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ይቅርና፣ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ሲካለሉም በህዝብ ፍላጎት መሰረት ነው" የሚሉት አቶ ዶሪ አስገዶም "ለኢትዮጵያ ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈለ የኢሮብ ህዝብ፥ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ትግራዋይ ነኝ እያለ አንተ ኤርትራዊ ነህ ብሎ መወሰን ከፍተኛ የመብት ጥሰት ነው" ሲሉ አክለዋል።

የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶች ሊመለሱ ይገባል 

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በኤርትራ የተያዙ የኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት የሆኑ የትግራይ አካባቢዎች እንዲመለሱ በተደጋጋሚ ይጠይቃል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ በቅርቡ ከትግራይ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ከአልጀርሱ ስምምነት ውጭ የሆነ የተያዘ ቦታ ካለ ለማጣራት ኮሚቴ መቋቋሙ ገልፀው ነበር። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ በቅርቡ በኢንግሊዝ በሚገኘው ኤምባሲው በኩል ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ግዛት የሆነ የትግራይ አካባቢ አለመያዙ በመግለፅ ባድመ ጨምሮ አሁን ላይ የኤርትራ ጦር ተቆጣጥሮት ያለው ቦታ የኤርትራ ግዛቶች ናቸው ማለቱ ይታወሳል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ