1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሰሜን ሸዋና  የኦሮሚያ ዞኖች ግጭት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 13 2014

ካለፈዉ ዕሁድ ማታ እስከ ለማክሰኞ አጥቢያ ድረስ በቀጠለዉ ግጭት በሰሜን ሸዋ ዞን ብቻ 9 ሰዎች ተገድለዋል፤ 125 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 3ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቅለውም።በኦሮሚያ ዞን ደግሞ ቢያንስ የሁለት ቀበሌ ነዋሪዎች መፈናቃለቸዉ፣ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰዉ መሞቱንም ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/4AFOW
Äthiopien | ausgebrannte Häuser in Molale
ምስል፦ Efratana Gidm woreda Communication

ለተፈናቃዮቹ የደረሰ ርዳታ የለም

ሰሞኑን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች በተደረገዉ ግጭት የተፈናቃሉ ሰዎች ዕርዳታ እንዲሰጣቸዉ እየጠየቁ ነዉ።ካለፈዉ ዕሁድ ማታ እስከ ለማክሰኞ አጥቢያ ድረስ በቀጠለዉ ግጭት በሰሜን ሸዋ ዞን ብቻ 9 ሰዎች ተገድለዋል፤ 125 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 3ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቅለውም። በኦሮሚያ ዞን ደግሞ ቢያንስ የሁለት ቀበሌ ነዋሪዎች መፈናቃለቸዉ፣ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰዉ መሞቱንም ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ