1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና የኢትዮጵያ አቅም

ረቡዕ፣ ጥቅምት 6 2017

በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከምርታማነት ባሻገር የህብረተሰቡን የአመጋገብ ስርዓት መቀየር ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከዓመት አመት ምርታማነትን እያሳደኩ ነው ብትልም፤ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚታዩ ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ ካልተቀመጠ የትም እንደማይደርስ ነው ባለሞያዎች የሚናገሩት ።

https://p.dw.com/p/4lrlF
Äthiopien Adama | Welt ohne Hunger | Traditionelle Weizenernte
ምስል Stefan Trappe/Imago Images

የምግብ ዋስትና ተረጋግጧል የሚባለው ምን ሲሟላ ነው ?

የምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና የኢትዮጵያ አቅም

በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከምርታማነት ባሻገር የህብረተሰቡን የአመጋገብ ስርዓት መቀየር ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከዓመት አመት ምርታማነትን እያሳደኩ ነው ብትልም፤ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚታዩ ግጭቶች ዘላቂ መፍትሄ ካልተቀመጠ የትም እንደማይደርስ ነው ባለሞያዎች የሚናገሩት ። ሰላም ካለ በዘርፉ የሚታዩ ተስፋ ሰጭ ዉጤቶች ዘላቂነት ሊኖራቸው ይችላል ።  

 

የምግብ ዋስትና ምንነት

አፍሪካ የምግብ ዋስትና ጥያቄ በመሰረታዊነት ስነሳባት አህጉሪቱ ለዚሁ በርካታ ዜጎቿን ለስደት በመዳረግ ለምግብ ቁሳቁሶች ልመናም እጆቿን ወደ አደገው ዓለም ስትዘረጋ ጎልቶ ይስተዋላል፡፡ የአጉሪቱ አካል የሆነችው ኢትዮጵያም ከዚህ አኳያ ጉልህ ጥያቄ ነው የሚነሳባት፡፡ ይሁንና አገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምግብ እራስን በመቻል “የምግብ ዋስትና ሉዓላዊነት” ባለችው ግብርናው ላይ በስፋት እየሰራች ስለመሆኑ በስፋት ይደመጣል፡፡ የሆነ ሆኖ አንድ ግለሰብ ወይም ዜጎች እና አገር በምግብ ዋስትና እራሳቸውን ችለዋል ወይም የምግብ ዋስትናቸውን አረጋግጠዋል ስንል ምን ማለታችን ነው? በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምግብ ዋስትና ማዕከል የምግብ ዋስትና ልማት እጩ ዶ/ር የሆኑት በዳዳ ከበበ ዜጎች ወይም አገር የምግብ ዋስትናቸውን አረጋግጠዋል የሚባለው ይህ ስሟላ ነው ይላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ግብርናን የማዘመን ውጥን

“እንደ አገር የምግብ ዋስትና ተረጋገጠ የሚባለው እያዳንዱ ዜጎች የሚፈልጉትን ነገር ከባህላቸው ጋር ሳይጣረዝ የሚፈልጉትን ያህል መመገብ ስችሉ ነው” የሚሉት ባለሙያው አማራጭ ምግቡ (ግብዓቶቹ) በተለይም እንደ አገር የምግብ ተደራሽነት ከቦታ ቦታ ያለምንም ገደብ ስንቀሳቀስና በበቂ ሁኔታ ስገኝም ነው ይላሉ፡፡

የስንዴ የእርሻ ማሳ በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምግብ እራስን በመቻል “የምግብ ዋስትና ሉዓላዊነት” ባለችው ግብርናው ላይ በስፋት እየሰራች ስለመሆኑ በስፋት ይደመጣልምስል Gudrun Krebs/PantherMedia/Imago

 

ምግብ ዋስትና፤ በብዛት ከማምረትም በላይ

በብዛት ማምረት፣ የተመረተውን የምግብ እህል በአግባቡ ማሰራጨት (ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ)፣ የአጠቃቀምና የምርታማነት ቀጣይነት መኖር ለምግብ ዋስትና ወይም በምግብ ራስን መቻል እንደ ምሰሶዎችም ይጠቀሳሉ፡፡ እንደ ባለሙያው አስተያየት የምግብ ዋስትና አሁን አሁን የአገር ሉዓላዊነት መገለጫ መሰረትም ሆኖ እየታዬ ነው፡፡ “አንድ አገር አሁን ላይ ከጦር መሳሪያ ልቅ ሉዓላነቷን አረጋገጠች የሚባለው በምግብ እራሷን ስትችል ነው” በማለት አስተያየታቸው አክለዋል።

ዓለምን ያሳሰበው የምግብ ዋስትና

የኢትዮጵያ መንግስት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በምግብ ዋስትና እራስን ለመቻል በሚል ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ የእህል ዝርያዎች ላይ በማተኮር ምርታማነትን በማሳደግ ላይ እገኛለሁ ይላል፡፡ ሆኖም በአገሪቱ ምርታማ በሆኑ አከባቢዎች ጭምር በተለይም በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ባለው ግጭት አለመረጋጋቱ በርካታ አርሶ አደሮች ግጭቶቹን ሽሽት ከገጠር ወደ ከተሞች በመሸሹ በነዚህ አከባቢዎች ምርታማነት በእጅጉ መፈተኑ ይገለጻል፡፡ የምግብ ዋስትና ባለሙያውም የዚህን ተጽእኖ ጉልህነት አይሸሽጉም፡፡

ሰብላቸው በአንበጣ የወደመባቸው ገበሬዎች አቤቱታ 

“አለመረጋግትና ግጭት ካለ እንኳን ልታመርት ያመረትከውንም አትበላም” የሚሉት ባለሙያው፤ ሰላም ባለባቸው አከባቢዎች እንኳ ያለውን አቅም አውጥቶ በስፋት ማምረት ከተቻለ ግን በቂ ምርት ማግኘት እንደሚቻል ያስረዳሉ፡፡ የተመረተውን ምርት ከቦታ ቦታ ወስዶ አለመሸጥ ግን ትልቁ አሁናዊ ተግዳሮት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ የምግብ ባህል ማሻሻል ከተቻለ እና መረጋጋትም በመላ አገሪቱ ከሰፈነ ኢትዮጵያ ምግብን ከውጪ የአለማስገባት አቅም ላይ መድረስ አይቀረ እንደሆነም አመለክተዋል፡፡

የምግብ ዋስትና ቀውስ ድሐ ሃገራትን ወደ ቻይና?

የምግብ ዋስትና ከማህበረሰባዊ ውቅር አንጻ

በኢትዮጵያ ከምርታማነትም ባሻገር ያለው የአመጋገብ ባህል ለምግብ ዋስትናው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የሚስረዱት ደግሞ በሙያቸው ሶሻል አንትሮፖሎጂስት የሆኑና ናይሮቢ ላይ መቀመጫውን ባደረገው በአፍሪካ ብዝሃህይወት መረብ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ፋሲል ገበየሁ ናቸው፡፡ “ምግብ መወሰድ ያለበት ሆድ ለመሙላትና ርሃብ ለማስታገስ ብቻ መሆን የለበትም” የሚሉት ዶ/ር ፋሲል አገር በቀል እውቀቶችን ተጠቅሞ የተሻለ ግንዛቤን ማህበረሰቡን ማስጨበጥ እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ በሙያቸው አብራርተዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ