1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሥራቅ አማራ ዞን ገበሬዎች አቤቱታ

ዓርብ፣ ጥቅምት 13 2013

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ከሰጡ አርሶ አደሮች መካከል በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ የ024 ቀበሌ ነዋሪ አቶ ይማም መሐመድ ሰብላቸው በአንበጣ ቢጎዳም እስካሁን እርዳታ አላገኙም።በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ የ012 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር እንዳሉት ሰብላቸው በአንበጣ በመበላቱ ለቀጣይ የምኸር ወቅት ለዘር የሚሆን ነገር አልተረፈም።

https://p.dw.com/p/3kLet
Äthiopien | Heuschreckenplage an der Grenze zu Tigray und Amhara
ምስል Million H. Silase/DW

የምሥራቅ አማራ ዞን ገበሬዎች አቤቱታ

በምሥራቅ አማራ ዞኖች ሰብላቸው በአንበጣ የተጎዳባቸው አርሶ አደሮች የእለት ድጋፍ እንዳላገኙ ተናገሩ።ዶቼቬለ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች እንዳሉት ሰብላቸው በመውደሙ ለዘር የሚሆን ምርትም የላቸውም። መንግስት በበኩሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቆ የእርዳታ አሰጣጡ ግን ሁሉንም እንደማያጠቃልል ገልጿል።
አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ በስልክ ከሰጡ አርሶ አደሮች መካከል በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ የ024 ቀበሌ ነዋሪ አቶ ይማም መሐመድ ሰብላቸው በአንበጣ ቢጎዳም እስካሁን እርዳታ አላገኙም።በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ የ012 ቀበሌ ነዋሪው አቶ ሀቢብ መሀመድም ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተዋል።በዚሁ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ሌላው አርሶ አደር እንዳሉት ሰብላቸው በአንበጣ በመበላቱ ለቀጣይ የምኸር ወቅት ለዘር የሚሆን ነገር አልተረፈም።በአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ኮሚሽን የደቡብ ወሎ ዞን አስተባባሪ አቶ መሳይ ማሩ እርዳታ መደረጉንና የእርዳታው አሰጣጡ ግን ሁሉንም እንደማያጠቃልል አመልክተዋል።የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ምግብ ዋስትና አስተባባሪ አቶ መሐመድ ይማም ዛሬ አልሚ ምግብና የትምህርት ቁሳቁስ ከአማራ ልማት ማህበር መቀበላቸውን ተናግረዋል።የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጃለም በበኩላቸው ችግሩ ገና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ለጊዜው አፋጣኝ የምግብ እርዳታ መደረጉን ተናግረዋል።የአንበጣ መንጋ በአማራ ክልል ምስራቃዊ ዞኖች በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የግብርና ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች ገልፀዋል፡፡ 
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ
 

Äthiopien | Heuschreckenplage an der Grenze zu Tigray und Amhara
ምስል Million H. Silase/DW