1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የየካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም የዜና መፅሄት

ሰኞ፣ የካቲት 2 2018

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያቀረቡትን ክስ ዛሬ ሰኞ “ሐሰት” በማለት አጣጥሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ሰሜን ምሥራቅ የድንበር አካባቢ ከዚህ ቀደም ከተቆጣጠሩት “የበለጠ ዘልቀው” እንደገቡ ገልጸው ነበር። በጉዳዩ ላይ የተንታኞች እና የፓለቲከኞች አስተያየቶች የተካተቱባቸው ዘገባዎች ለዛሬ ተዘጋጅተዋል። የአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 625,000 የሥራ ዕድሎች በክልሉ እንደተፈጠሩ አስታውቋል። ይህን የተመለከተው ዘገባ በዜና መጽሔት ከሚቀርቡት መካከል ነው።

https://p.dw.com/p/58OjM
ቀጣዩን ክፍል እለፈው ስለዚህ ዝግጅት

ስለዚህ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-Zeitfunk-DWcom

ዜና መጽሄት

በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪቃ፣ የአውሮጳ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜና ዘገባዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መጽሄት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል።