1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር

ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2018

በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር በፍራንክፈርት ከተማ ባዘጋጀው መድረክ ላይ 130 ኛዉ የአድዋ ድል በዓል ብሎም ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ታስቦ ዉሏል። በዝግጅቱ ላይ የፍራንክፈርት ከንቲባ በፍራንክፈርት የሴቶች ጉዳይ ዋና ተጠሪ ጨምሮ በጀርመን የኢትዮጵያ አንባሳደር እና ሌሎች ተጋባዥ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

https://p.dw.com/p/5AIlK
በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር (EDWA)
በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር (EDWA)ምስል፦ Marly Photography

በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር

 በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር

 

በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር (EDWA) በፍራንክፈርት ከተማ ባዘጋጀው Diaspora Impact Fair መድረክ ላይ 130 ኛዉ የአድዋ ድል በዓል ብሎም ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ታስቦ ዉሏል።  በዝግጅቱ ላይ የፍራንክፈርት ከንቲባ ዶ/ር ናርጊስ እስካንድሪ ግሩንበርግ ፤ በፍራንክፈርት የሴቶች ጉዳይ ዋና ተጠሪ ቲና ዛብ ሮድሪገስን ጨምሮ በጀርመን የኢትዮጵያ አንባሳደር አቶእስክንድር ይርጋ እና ሌሎች ተጋባዥ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።  

ባለፈዉ ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በፍራንክፈርት ከተማ በጀርመን በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር (EDWA) በተዘጋጀው መድረክ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ዜጎች ተሳትፈዉበታል። ወደ 180 ሴቶችን ያቀፈዉ ይህ ማህበር ከተመሰረተ ሁለተኛ ዓመቱን እንደያዘ የነገሩን  የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ራንያ ክንፈ፤ ማህበሩ የአድዋን የአድነት ኃይል እና የአድዋን ቆራጥነት ይዞ የተመሰረተ ማኅበር ነዉ።

በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር (EDWA) ባለፈዉ ዓመት የአድዋ ድል በዓልን ሲከበር የተጠነሰሰ እና በአምስት ሴቶች የተመሰረተ መሆኑን የነገሩን የማኅበሩ  ፕሬዚዳንት ራንያ ክንፈ፤  ፍራንክርት ጀርመን ላይ ማኅበሩ በጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት በ(GIZ)  ድጋፍ ምስረታዉ መጀመሩን ተናግረዋል። ማኅበሩ በሴቶች ይመስረት በሴቶች ይመራ እንጂ ወንዶችንም ብሎም ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ዜጎችም የሚሳተፉበት መሆኑን ተነግሯል። ማኅበሩ የዘንድሮዉን የዓለም አቀፍ የሴቶት ቀንን እና አድዋን በልዩ መንገድ ማሰቡንም ራንያ ክንፈ እንዲህ ተናግረዋል።

በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር (EDWA) በምን ምን ጉዳዮች ላይ ነዉ እየሰራ ያለዉ? በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር (EDWA) ፕሬዚዳንት ራንያ ክንፈ እንደገለፁት ማኅበሩ ወር በገባ በሦስተኛዉ ሳምንት ሃሙስ እለት በበየጊዜዉ በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ላይ ባለሞያን እየጋበዘ ገለፃን ያደርጋል። በዚህ ዝግጅትም በርካታ በዉጭ የሚኖሩ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

 በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር
በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበርምስል፦ EDWA

በጀርመን የኢትዮጵያዳያስፖራ ሴቶች ማህበር  በመኖርያ ፈቃድ አለማግኘት እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ከጀርመን የሚጠረዙ ወይም የተጠረዙ የተባረሩ ኢትዮጵያዉያንን በመዳቱም ይታወቃል።

ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ዜጎች በሚኖሩባት እና በዓለም አቀፋዊነትዋ በምትታወቀዉ በጀርመንዋ ፍራንክፈርት ከተማ ኢትዮጵያዉያን በከተማዋ እያደረጉት ያለዉ አስተዋፅኦ ብሎም በባህል፤ በኢኮኖሚ ረገዶች የዘረጉት ድልድይ በጀርመን እና በኢትዮጵያ መካከል የዳበረ  ግንኙነት እንዲኖር እያደረገ ያለዉ አስተዋፅኦ ቀላል እንዳልሆነ ተገልጿል።

 በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር
በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበርምስል፦ EDWA

በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር (EDWA) በፍራንክፈርት ከተማ የአድዋ ድል በዓልን እና ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስታኮ ባዘጋጀዉ መድረክ፤ የፍራንክፈርት የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ብሎም የፍራንክ ፈርት ከተማ ከንቲባ በጀርመን የኢትጵያ አምባሳደር፤ የንግድ ድርጅቶች፤ ሥራ ፈጣሪ ግለሰቦች፤ ንግድ ለመጀመር ፍላጎት ያላቸዉ የዉጭ ሃገር ዜጎች፤ ተገኝተዋል። ከተመሰረተ ሁለተኛ ዓመቱን የያዘዉን በጀርመን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሴቶች ማህበር (EDWA) እንዲያድግ እንዲመነደግ እየተመኘሁ የዛሬዉን ዝግጅቴን እዚህ ላይ አጠናቅቃለሁ። አዜብ ታደሰ ነኝ ጤና ይስጥልኝ።

አዜብ ታደሰ

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር