1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዩጋንዳ የቶማስ ክዎዬሎ ፍርድ ፍትህ አስገኝቶ ይሆን ?

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 11 2016

የዩጋንዳ ፍርድ ቤት የሎርድ ሬዚስታንስ ጦር (LRA) አዛዥ የነበሩትን ቶማስ ክዎዬሎ በሰው ልጆች ላይ በተፈጸሙ በርካታ ወንጀሎች ጥፋተኛ ብሏቸዋል። "በተመሰረተባቸው 44 ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው እንደተፈረደባቸው ዓለማቀፍ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ሚካኤል ኢሉቡ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4jZuT
Uganda Thomas Kwoyelo
ምስል GAEL GRILHOT/AFP

የዩጋንዳ ፍርድ ቤት በሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ ወታደር ላይ በ44 ወንጀሎች ጥፋተኛ አለ

የዩጋንዳ ፍርድ ቤት የሎርድ ሬዚስታንስ ጦር (LRA) አዛዥ የነበሩትን ቶማስ ክዎዬሎ በሰው ልጆች ላይ በተፈጸሙ በርካታ ወንጀሎች ጥፋተኛ ብሏቸዋል።
"በተመሰረተባቸው 44 ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው እንደተፈረደባቸው ዓለማቀፍ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ሚካኤል ኢሉቡ ተናግረዋል። 
በሰሜናዊ ዩጋንዳ በምትገኘው ጉሉ ከተማ የተሰየመው ፍርድ ቤቱ የቀድሞው የታጣቂ ቡድኑ መሪ ጥፋተኛ ከተባሉባቸው ወንጀሎች ውስጥ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየት፣ መዝረፍ፣ አፈና እና የተፈናቃዮችን ሰፈራ ማውደም ይገኙበታል ። ፍርድ ቤቱ ክዎዬሎ በሶስት የነፍስ ግድያ ክሶች ጥፋተኛ  ሳይባሉ ቀርተዋል። በተጨማሪም "31 ተለዋጭ ወንጀሎች" ውድቅ መደረጉን ዳኛው አክለው ተናግረዋል።  

የሙሴቬኒ ያገዛዝ ስልት
ከኮዎዬሎ ልጆች መካከል አንዱ የሆነው ሙሴ ራካራ የማክሰኞው ፍርድ  ብዙም እንዳልደነቀው ነው የተናገረው ። 
የ27 ዓመቱ አርሶ አደር ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በሰጠው ቃለ ምልልስ እንዳለው 
"አባታችው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ በደል ሲፈጸምበት እንደቆየ ተመልክተዋል ። ምክንያቱን ሲገልጹም ምልክቶች ሁሉ እርሱን ጥፋተኛ የሚደርጉ እንጂ ፍትህ የሚያሰጡት አልነበሩም ብለዋል።   በፍርዱም እንዳልተደነቁ ገልጸዋል። 
በቤልጂየም አንትወርፕ ዩኒቨርሲቲ የልማት ፖሊሲ ኢንስቲትዩት የፖለቲካ ተመራማሪ  የሆኑት ክሪስቶፍ ቲቴካ በበኩላቸው ፍርዱ የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ  በሰዎች አእምሮ ውስጥ ያለውን ህልውና በመቀነሱ ረገድ ትልቅ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን እና ወደ ዕርቅ በሚደረገው ጉዞው ወሳኝ ምዕራፍ ነው ይላሉ።

ቶማስ ክዎዬሎ
ፍርድ ቤቱ ክዎዬሎ በሶስት የነፍስ ግድያ ክሶች ጥፋተኛ  ሳይባሉ ቀርተዋል። በተጨማሪም "31 ተለዋጭ ወንጀሎች" ውድቅ መደረጉን ዳኛው አክለው ተናግረዋል።  ምስል GAEL GRILHOT/AFP

የዩጋንዳ ምርጫና የሰብዓዊ መብት ጥሰት  

« አሁን በሰሜናዊ ዩጋንዳ የቀሩ እና ሊፈወሱ የሚገባቸው ቁስሎች አሉ ። በሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ እና በዩጋንዳ መንግስት መካከል የተደረጉ ግጭት ጦርነቶች በእርግጥ ፈውስ ይፈልጋሉ ። ከዚህ አንጻር የኩዮሎ ፍርድ ጠቃሚ ሚና ሊጫወት ይችላል። »
ክዎዬሎ በምስራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር  በጦር ወንጀሎች ክስ የቀረበበት የመጀመሪያው እና ብቸኛው ከፍተኛ የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ ወታደር ነው ። 
ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ በዩጋንዳ የተመሰረተው በጎርጎሪያዉያኑ በ1980ዎቹ በጆሴፍ ኮኒ አማካኝነት ሲሆን ዓላማውም  በአስርቱ ትእዛዛት ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ለመመስረት ነው። በዚህ ደግሞ  የኡጋንዳውን ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ከስልጣን ማባረር እና የክርስቲያናዊ መንግስት  መመስረት የተልዕኮው አካል አድርጓል።።
አማጺ ቡድኑ በፕሬዚደንት ሙሴቬኒ  መንግስት ላይ ባካሄደው ደም አፋሳሽ አመፅ ከ100,000 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ60,000 በላይ ህጻናት ታግተው ከዩጋንዳ ወደ ሱዳን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ  እና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ተወስደዋል።

የዩጋንዳ ምርጫ እና ስጋቱ
ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ ወንድ ልጆችን ለወታደርነት በመመልመል እና ሴት ልጆችን ደግሞ ለጾታዊ ዓላማ  የመግዛት ውንጀላ ቀርቦበታል። ከዚህ በተጨማሪ ታጣቂ ቡድኑ  በዋናነት በአቾሊ ጎሳ  ላይ ያነጣጠረ ከፍተኛ  ጭፍጨፋዎችን ፈጽሟል ተብሎ ተከሷል።
የ49 አመቱ ቶማስ ክዎዬሎ  ጠበቆች እንደሚሉት ገና የ12 አመት ልጅ ሳለ ነበር ከትምህርት ቤት ሲመለስ ታግቶ ተወስዶ የአማጺ ቡድኑ ወታደር እንዲሆን የተገደደው ። 
ክዎዬሎ  የቡድኑን ታዋቂው መሪ ኮኒን ጨምሮ በአለምአቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) በአስገድዶ መድፈር፣ በባርነት፣ በአካል ማጉደል፣ በግድያ እና በግዳጅ ህጻናትን በመመልመል ከሚታወቁት ከሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ ከፍተኛ አዛዦች መካከል እንደ አንዱ ተቆጥሮ አያውቅም።  

የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ
የ49 አመቱ ቶማስ ክዎዬሎ  ጠበቆች እንደሚሉት ገና የ12 አመት ልጅ ሳለ ነበር ከትምህርት ቤት ሲመለስ ታግቶ ተወስዶ የአማጺ ቡድኑ ወታደር እንዲሆን የተገደደው ። ምስል MATT BROWN/AFP/Getty Images

የዩጋንዳ የፖለቲካ ውጥረት

በኡጋንዳ ጦር ሽንፈት የደረሰበት አማጺ ቡድኑ የፖለቲካ መረጋጋት ወዳልነበራቸው የጎረቤት ሀገራት ለመሸሸግ ተገዶ ነበር። 
ክዎዬሎ  ቡድኑን የተቀላቀለው በጎርጎርሳዉያኑ 1987 ሲሆን በመጋቢት 2009 በቁጥጥር ስር ዋለ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ያለፉትን  14 አመታት በእስር አሳልፏል።
 ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ የሀገሪቱ አቃቤ ህግ  በክዎዬሎ ላይ ያቀረበውን ክርክር ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር  ማጠናቀቁን አስታውቋል።
ነገር ግን አወዛጋቢው የፍርድ ሂደት የሰብዓዊ መብት ተከታታይ ድርጅቶችን ስጋት ውስጥ የከተተ ሲሆን በእስር ላይ ያሳለፈው ረጅም ጊዜ ፍትሃዊ ፍርድ ያስገኘ እንዳልነበርም ተገልጿል።
እንደ ቲቴካ ያሉ አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንደ ክዎዬሎ ያሉ ግለሰቦች በልጅነታቸውም ቢሆን፣ አንዳንድ ውሳኔ የመስጠት ችሎታቸውን ይዘው ይቆዩ እንደነበር ይከራከራሉ።
እንደዚያም ሆኖ ግን አንስቲ ኢንተርናሽናል የሰላም ሂደቱን በማሳለጥ ረገድ በጎ ሚና መጫወቱን ቲቴካ ይናገራሉ። 

የዩጋንዳ ምክር ቤት ውሳኔና ያስከተለው ውዝግብ
3 "ዩጋንዳ ቸር የሆነ የይቅርታ ህግ አላት ።  ይህም ማንኛውም እጁን የሰጠ የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ ተዋጊ  ምህረት ሊደረግለት ይችላል የሚለው ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ከተዋጊዎቹ መካከል አብዛኞቹ ታግተው እና በልጅነታቸው የተወሰዱ በመሆናቸው ነው። » 
ቲቴካ አክለው ሲናገሩ በማንኛውም ሁኔታ ዉስጥ ፍትህ ሊሰፍን ይገባል። 

«በሌላ በኩል ብዙ ሰዎች እንደሚያምኑት፣ መቼም ሰላም ማግኘት የምትችለው ፍትህ ከተገኘ ብቻ ነው፣ ለዚህም ነው አንድ ሰው በልጅነቱ ታፍኖ ተወስዶ እንኳ ቢሆን ፍትህ  ያስፈልገናል።»
ዩጋንዳ አሁንም ያልወጣላት ስጋት አለባት ። 

በዩጋንዳ ሕ/መንግሥት ላይ የታሰበው ለውጥ እና ተቃውሞ
የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ  መሪ የሆነው ጆሴፍ ኮኒ በማዕከላዊ አፍሪካ  ምንግስት በማይደርስበት አካባቢ ተደብቋል ተብሎ ይታመናል። በዓለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት  በጣም ከሚፈለጉት ሰዎች አንዱ ሆኖ የቆየው ጆሴፍ ኮኒ ያለበትን ለሚጠቁም አሜሪካ  እስከ አምስት ሚሊዮን ዶላር ወሮታ ለመስጠት ቃል ገብታለች። 
አብዛኞቹ የአማጺ ቡድኑ አባላት በሱዳን ዳፉር ክልል ለረጅም ጊዜ መቆየታቸው ይነገርላቸዋል።  የተቀሩት ተዋጊዎች በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን እና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ መካከል ባሉ የድንበር አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ሲሆን በዋናነት ወርቅ እና የዝሆን ጥርስን ጨምሮ በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ መሰማራታቸውን የቡድኑን እንቅስቃሴ የሚከታታሉ ዓለማቀፍ ድርጅቶች ሪፖርት አድርገዋል። 
የቡድኑ መሪ ኮኒም በዓለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት መያዣ ከወጣበት ከጎርጎርሳዉያኑ  2005 ጀምሮ በሽሽት ላይ ይገኛል። 
ሺቪኮስቪኪ ማርቲና 

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ