በአዲስ አበባ እና ደሴ መንገድ የአሽከርካሪዎች የደኅንነት ሥጋት አይሏል
ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2018
በአዲስ አበባ እና በደሴ መካከል ባለው የኢትዮጵያ የፌዴራል የሀገር አቋራጭ መንገድ ላይ በተለይም ከሸዋ ሮቢት ከተማ በኋላ ባሉ አካባቢዎች የሚፈጸሙ እገታዎች፣ ድብደባዎችና ዝርፊያዎች በመንገደኞችና በአሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት እየፈጠሩ መሆኑ ተነገረ ።
ታጣቂዎች ተሽከርካሪዎችን በማስቆም ተሳፋሪዎችን ወደ ጫካ በመውሰድ እንደ ሚደበድቡ፣ በሞባይል ባንኪንግ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ እንደሚያስገድዱ እና ከፍተኛ የገንዘብ ክፍያ (እስከ 100 ሺህ ብር) እንደሚጠይቁ ተጎጂዎች ገልጸዋል ። በተለይ በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ አካባቢዎ ጥቃቶቹ በብዛት እንደሚፈጸሙ ተጠቁሟል።
የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል እንድሪስ፣ በሁለቱ ዞኖች አመራሮች ቅንጅት የታገቱ ሰዎች የተለቀቁበት ሁኔታ መኖሩን ገልጸው፣ በዝርፊያ የተሳተፉ 7 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።
ከሰሞኑ ከአዲስ አበባ ደሴ የፌዴራል ሀገር አቋራጭ መንገድ ላይ የሚስተዋለው የሰዎች እገታ እና ዝርፊያ በመንገዱ ለሚጓዙ መንገደኞች እና አሽከርካሪዎች ትልቅ ስጋት መፈጠሩ ተጓዦች ይገልፃሉ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ ከአዲስ አበባ ደሴ እየተጓዘ የነበረ ተጓዥም በታጣቂዎች ጀውሃ ከተማ መግቢያ ላይ የደረሰባቸውን እገታ ዝርፊያና ድብደባ እንዲህ ይናገራሉ፡፡ «ያው ድልድይ ጀውሃ ወንዝ ጋር አስከሬን ስለያዘ ቀስ ብሎ ነበርና አስቆሙን በጫካው ይዘውን ገቡ ያው የአቅማቸውን ደበደቡን ሞባይል ባንኪንግ አስተላልፉ አሉን እኔ ጉልበቴን ነው ሾፌሩ አንገቱን ጀርባው አካባቢ በጩቤ ወግተውታል ሌላው ብትር ነው ከኛ በኃላ ይሄው እራሱ ጊዮን ባስን አስቁመው ሙሉ ስልካቸውን ወሰዱ፡፡»
በተለይም ከሸዋ ሮቢት ከተማ በኋላ ባሉ አካባቢዎች ላይ የእገታና የዝርፊያ ተግባሩ እንዳለ የሚናገሩ አሽከርካሪዎች በተደጋጋሚ የሚፈጠር የፀጥታ መደፍረስ አሽከርካሪዎች እንዲታገቱ እያደረገ ሲሆን ተሸከርካሪዎችን በማስቆም ተሳፋሪዎችን ወደ ጫካ በመውሰድ እንደሚያቆ‘ዮቸው ነው አሽከርካሪዎች የሚገልፁት፡፡ «አልተለቀቁም ጨፋ ግን ብር አስገቡ ብለው ለሹፌሩ መቶ ሺህብር ገብቷል፡፡ ተሳፋሪውም እንዳለ ነው አልተለቀቁም ተኩስ ነበር የዛሬ ሁለት ቀን ቆሬ አካባቢ የነዛም ሰዎች ተይዘው ነበርና አውርደው እንዳለ መኪናውን አስቁመው የወሰዷቸው ወደ ሦስት ሰዓት መንገድ ነው ዞሮ ዞሮ ብር ትናንት መቶ ሺህ ብርአስገብተዋል እስካሁን ምንም ነገር የለም፡»›
አሁን ላይ ለየብስ ትራንስፖርት ከደሴ አዲስ አበባ ለመጓዝ ሁኔታውአስተማማኝ አይደለም የሚሉት አስተያየት ሰጭዎች ተደጋጋሚየመንገድ መዘጋትና እገታ መኖሩን ይናገራሉ፡፡ «አያስተማምንም በየቦታው የገታ አደጋዎች አሉ በተለይም 200 ኪሎ ሜትር ከሄድክ በኋላ ከሰሜን ሸዋ ጀምሮ እስከ ደብረብርሃንባሉት መካከል አስቸጋሪ ነው አምነህ አትሄድም ይዘጋል፤ ይከፈታልሲቀጥል ሰው ታፍሶ ይወሰዳል ብቻ ሰላምህን ያሳጣል፡፡»
የእገታ ተግባሩ በሰሜን ሸዋ እና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ከሰሞኑ መኖሩን የገለፁትየኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊአቶ አወል እንድሪስ በሁለቱም አካባቢዎች ያሉ ታጣቂዎችንእገታውን መፈፀማቸውን ይናገራሉ፡፡ «አልፎ አልፎ እገታዎችና ዝርፊያዎች እያጋጠሙ ነው ያሉትእገታ በሰሞኑ ተፈፅሟል እገታውን የሁለቱ ዞን አመራሮች በአንድላይ በመሆን የሰሜን ሸዋና የኛዞን አመራር ሰዎች ዛሬ የወጡበትሁኔታ ነው የተፈጠረው በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል ያው ከዚህም ነበር እነዛ ሲታገሩ ከዚህም የማገት ሁኔታዎች ነበሩየሁለቱም ያኛው ሲለቅ ይሄኛውም ለቆ የሁለቱም ታጋቾች ወደቤተሰቦቻቸው ወደ አካባቢያቸው የተመለሱበት ሁኔታ ነውያለው፡፡»
እንዲሁም በዞኑ የሚፈፀሙ ዝርፊያዎችን በመከላከል እረገድጠንካራ ስራ ተሰርቷል የሚሉት አቶ አወል እንድሪስ በዘርፉ ተግባርላይ የተሰማሩ ሰዎችን አድኖ የመያዝ ስራ እየተሰራ ነው ይላሉ፡፡ «መንገድ ላይ አስቁሞ ዘረፋ ጋር ተያይዞ እሱ አንድ ሁለት ቀንአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ልዩ ስሙ ቦርከና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ አንድ ሁለት ቀን አጋጥሟል ወዲያው ወደ 7 ሰዎችገደማ በቁጥጥር ስር ውሎ ህግ የተከበረበት ሁኔታ ነው ያለውአሁን ሰላም ነው መንገዱ፡፡»
የኢትዮጵያ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ባንብረቶች ማኅበር በበኩሉ በአሽከርካሪዎች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን እገታ፣ ዝርፊያና፣ ሞት በተመለከተ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ጋር እየተወያየን ነው ይላሉ የማኅበሩ ሰብሳቢ አቶ ተካደበሌ፡፡ «ጫናው ይኖራል እንግዲህ ያው በውይይት በጋራ መንግስትም ተጨምሮበት የሚፈታ ነው እኛ እንደ ሀገር ህዝብ መጓጓዝ አለበት እንንቀሳቀሳለን እየሞትንም ያገር ጉዳይ ስለሆነ ሌላውን ደግሞ እንዳልኩህ የመንግስት አካላት ችግሩን ትኩረት ሰጥተው ፕሮግራም ስለያዙልን በዛ በዛ ይፈታል የሚል እምነት ስላለኝ፡፡»
ኢሳያስ ገላው
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር