1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤኒሻንጉል 1.3 ሚሊዩን ሄክታርን በሰብል ለመሸፈን የተያዘ እቅድ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 21 2016

ለረጅም ዓመታት በጸጥታ ችግር ውስጥ የከረመው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከባለፉት ኣራት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ 1.3 ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን ማቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልፀ፡፡ እስካሁን ከ1.1 ሚሊዩን ያህል መሬት በሰብል መሸፈኑን እና ከባለፈው ዓመት የተሻለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4jyJb
Landwirtschaft in der Region Benishangul Gumuz, Äthiopien
ምስል Negassa Desalegn/DW

የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ተስፋ ተጥሎበታል

በቤኒሻንጉል 1.3 ሚሊዩን ሄክታርን በሰብል ለመሸፈን የተያዘ እቅድ

 
ለረጅም ዓመታት በጸጥታ ችግር ውስጥ የከረመው ቤኒሻንጉል  ጉሙዝ ክልል ከባለፉት ኣራት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ  1.3 ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን ማቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጸዋል፡፡ እስካሁን ከ1.1 ሚሊዩን ያህል መሬት በሰብል መሸፈኑን እና ከባለፈው ዓመት የተሻለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ሰላም በመስፈኑ ተከትሎ በሁሉም አካባቢዎች አርሶ አደሩ ወደ ስራ መግባቱን ኃላፊው አክለዋል፡፡ የሰላም ጥሪን ተቀብሎ ከትጥቅ እንቅስቃሴ የተመለሱ ወጣችም የትራክተር ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ግብርና ስራ መግባታቸውን አክለዋል፡፡

 ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ዓሳ እየተሰገረ ነው


በዘንድሮ የምርት ዘመን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁሉም አካባቢዎች አርሶ አደሩ ወደ ግብርና ምርት መግባቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡ የታጠቁ ሀይሎች ይንቀሳቀሱባቸው በነበሩ እንደ መተከል ዞን አንድ አንድ አካባቢዎች፣ በአሶሳ ዞንም የተወሰኑ ቦታዎች እና ካማሺ ዞን አምስት ወረዳዎች ውስጥ ዘንድሮው አርሶ አደሩ ወደ  ግብርና ስራ መግባቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ አመልክተዋል፡፡ በዚህ ምርት ዘመን ከ45 ሚሊዩን በላይ ኮንታል ሰብል ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ባለፉት አራት ዓመታት በምርት ከተሸነፈው መሬት  ጋር ሲነጻጸርም  የ3 መቶ ሺ ሄክታር ብልጫ ያለው እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ታጥቆ በተለያዩ ቦታዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ወጣቶች የሰላም ጥሪን ተቀብሎ ወደ ማህበረሰቡ የተቀላቀሉ ወጣቶችም በግብርና ዘርፍ እንዲሳተፉ የትራክተር ድጋፍ መሰጠቱን አቶ ባበክል ተናግረዋል፡፡ 

የበቆሎ እርሻ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ
በዘንድሮ የምርት ዘመን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁሉም አካባቢዎች አርሶ አደሩ ወደ ግብርና ምርት መግባቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡ምስል Negassa Desalegn/DW


በግብርና ምርት ከሚታወቀው የክልሉ አካባቢዎች አንዱ በሆነው መተከል ዞን ድባጤ ወረዳም አርሶ አደሩ ከባለፈው ዓመት በተሻለ ሁኔታ በእርሻ ስራ ላይ መሰማራቱን አቶ መልካሙ ደረሰ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ በስልክ ተናግረዋል፡፡ ወረዳው ለእርሻ ምቹ እና የተለያዩ ሰብሎች በማምረት የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ቀደም በነበረው የሰላም እጦት ምክንያት ከገጠራማ ቦታዎች ሰዎች ተፈናቅለው እንደነበር ነዋሪው ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ክረምት ወቅትም  ለአርሶ አደሩ የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት እንዳለ የተናገሩት ነዋሪው ወደ የአካባቢው የተመለሱ በርካታ አርሶ አደሮች በስራው ላይ መሰማራታቸው አብራርተዋል፡፡

የግብርና ኢንቨስትመንት መድረክ
በክልሉ በጸጥታ ችግር ምክያት   በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎቸ ተፈናቅሎ የነበረው ካማሺ ዞን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ግብርና ስራ ለውጥ ማሳየቱን አንድ ያነጋርናቸው የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ ወደቀያአቸው የተመለሱ ዜጎችም ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በስራ ላይ እንደሚገኙ ተገልጸዋል፡፡ በዞኑ የሰላም ተመላሽ የተባሉ ከዚህ ቀደም የትጥቅ እንቅስቃሴ ውስጥ የነበሩ ወጣቶች የትራክተር ድጋፍ ተደርጎላቸው  ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቅሎ በስራ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በዞኑ የግብርና ስራ የተሻለ እንደሆነ የተናገሩት ነዋሪው በስፍረው  የመንገድ እና ሌሎች መሰረተ ልማት ችግር በነዋሪ ላይ ተጽህኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ሰላም ሰፍኗል መባሉን ተከትሎ ባለፈው ሰኔ 16/2016 ዓ.ም በክልሉ ጠቅላላ ምርጫ  መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡ በክልሉ የግብርና ዘርፍን ጨምሮ በተለያዩ የኢቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለሚሳተፉ በመቶዎች ለሚቆጠሩ  ባለሀቶች ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም አስታውቋል፡፡ 

ነጋሳ ደሳለኝ 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ