1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ ይሰገራል»

ሰኞ፣ ሚያዝያ 21 2016

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ቢሮ በበኩሉ በግድቡ ላይ በተገነባው ግዙፍ የዓሳ ምርት ላይ ለማሰማራት ከ2 መቶ በላይ ወጣቶችን ማደራጀቱን አመልክቷል፡፡ እስካሁን የተወሰኑት ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጿል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ በ8 ወራት ውስጥ 1ሺ7 መቶ ቶን የሚሆን ዓሳ ከግድቡ በተደራጁ ወጣቶች መገኙትን አመልክተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4fIOD
Äthiopien Guba GERD-See
ምስል AMANUEL SILESHI/AFP

ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ዓሳ እየተሰገረ ነው

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ   ግድቡ ውሀ መያዝ ከጀመረ ወዲህ በተለይም ለዓሳ ምርት ምቹ መሆኑን በአካባቢው በዓሣ ማስገር ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ይናገራሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  ከአንድ መቶ በላይ ወጣቶች በዚሁ ስራ መስክ እንዲሰማሩ በማህበር ማደራጀቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ አመልክቷል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ በ8 ወራት ውስጥ 1729 ቶን ዓሳ ምርት ከህዳሴ ግድብ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡ የሰላም ተመላሾች የተባሉ ከዚህ ቀደም ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩና ሌሎች ወጣቶች በሁለት ማኅበር ተደራጅተው ወደ ስራ መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

የህዳሴ ግድብ ዓሳ ምርት

በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘው የተላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት በተጨማሪ በዓሳ ምርት የአካባቢውን ወጣቶች ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጸዋል፡፡ በግደቡ ሐይቅ ላይ በዓሳ ማስገር ስራ ለማሰማራት በመቶዎች የሚቆሩ ወጣቶችን ማደራጀቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡ ወጣት ብርሀኑ እና ወጣት ኢትማን መሐመድ በአሁኑ ወቅት በሐይቅ ላይ ዓሳ በማስገር ስራ  ተሰማርተው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡የህዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ተጠናቋል መባሉ እና አንደምታዉ

ወጣቶቹ የተደራጁበት ማህበርም 56 የሚደርሱ ወጣቶችን ያቀፈ ነው፡፡ በግደቡ ዳርቻ በሚሰሩት የዓሳ ማስገር ስራ በቀን ከ2 እስከ 3 ኮንታል ዓሳ እንደሚያገኙ አመልክተዋል፡፡ ግድቡ ውሀ መያዝ ከጀመረ ወዲህ በአነስተኛ የሰው ኃይል ዓሳ በማስገር ለአካባቢው ገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ በአካባቢው የዓሳ ማስገር ስራውን በማህበሰረብ አቀም ለማድረግና ለማሻሻል ዘመናዊ ጅልባዎች እንደሚያስልጉም ወጣቶቹ ይናገራሉ፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ
ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብምስል Amanuel Sileshi/AFP/Getty Images

ለዓሳ ማስገር ስራ የተደራጁ ወጣቶች

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ቢሮ በበኩሉ በግድቡ ላይ በተገነባው ግዙፍ የዓሳ ምርት ላይ ለማሰማራት ከ2 መቶ በላይ ወጣቶችን ማደራጀቱን አመልክቷል፡፡ እስካሁን የተወሰኑት ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጿል፡፡በጣና ሐይቅ ህገወጥ ዓሳ ማስገር የደቀነዉ አደጋ የቢሮው ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ በ8 ወራት ውስጥ 1ሺ7 መቶ  ቶን የሚሆን ዓሳ ከግድቡ በተደራጁ ወጣቶች መገኙትን አመልክተዋል፡፡ ግድቡ ዙሪያው የሚገኙ ወረዳዎችን በተለያየ ዘርፍ  ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው 108 ወጣቶች በአሁኑ ወቅት ፈቃድ በማውጣት በስራው ላይ እንደሚገኙ አክለዋል፡፡

በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ውስጥ የሚገኙው የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ የሲቪል ስራ 98.9 በመቶ መድረሱን የግድቡ መሠረተ ድንጋይ የተቀመጠበትን 13ኛ ዓመት በሚከበርበት ወቅት ተገልጾ ነበር፡፡ የግድቡ 2 ዩኒቶች በ2014 ዓ.ም ስራ መጀመራቸውን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት ግድቡ 540 ሜጋ ዋጋት የኤሌትሪክ ኃይል እያመነጨ ይገኛል ተብሏል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ