1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ግፍ ያየችዉ ስደተኛዋ ደራሲ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 25 2016

ደራሲ ሙሉ ደርቤ በሳዊዲ በቤት ሠራተኝነት እያገለገለች ኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦችዋን ስትረዳ አስራ ሁለት ዓመት አለፋት። ወደ አገር ለመግባት ብትፈልግም ጦርነት ተቀሰቀሰና በትዉልድ ቦታዋ ያሰራቸዉ ነገር ሁሉ በመዉደሙ መመለስn አልቻለችም። በስደት የበረሃ መንገድ በህገወጥ ሰዎች መከራን አይታለች። በዚህ ሁሉ መሃል ግን መጻፍዋን አላቆመችም።

https://p.dw.com/p/4iynz
ደራሲ ሙሉ ደርቤ
ደራሲ ሙሉ ደርቤ በሳዊዲ በቤት ሰራተኝነት እያገለገለች ኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦችዋን ስትረዳ አስራ ሁለት ዓመት አለፋትምስል Mulu Derebe/DW

በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ግፍ ያየችዉ ስደተኛዋ ደራሲ

ደራሲ ሙሉ ደርቤ ትባላለች።  በሳዊዲ አረብያ በቤት ሠራተኝነት እያገለገለች ኢትዮጵያ የሚገኙ አባት እናትዋን ትንንሽ እህት ወንድሞችዋን ስትረዳ አስራ ሁለት ዓመት አለፋት። ወደ አገር ቤት ለመግባትም እቅድ ይዛ ነበር። ነገር ግን ለቤተሰቦችዋ ያሰራችዉ የመኖርያ ቤት፤ የእርሻ በሪዎች ፤ ያስቆፈረችዉ የዉኃ ጉድጓድ ሳይቀር በጦርነቱ ወደመባት። እንደገና ዛሬ ለቤተሰቦችዋ በላስቲክ የተሰራ ቤት ዉስጥ እንዲኖሩ አድርጋ ለለት ኑሮዋቸዉ የሚሆን ነገር እየላከት እየደገፈቻቸዉ ነዉ።

ደራሲ ሙሉ ደርቤ ከ 12 ዓመት በፊት የ 10ኛ ክፍል  ማጠቃለያ ፈተና  ነጥብ ሳይመጣላት ቀረ ። ሞከረች ሞከረች አልሆነም።  ከቤታችን ታላቅ ልጅ በመሆኔ ፤እኔንም ማዉጣት አለብኝ፤ ወንድም እህቶቼንም ማሳደግ አለብኝ፤ እናት አቤትንም መርዳት አለብኝ ብዩ፤  ግብርና ጀመረኩ፤ አልሆነልኝም፤ የግንባታ ስራም እንዲሁ ከዝያም ለመሰደድ ወሰንኩ ስትል አጫዉታናለች። ራያ ሴንዉኃ በሚባል ገጠር ዉስጥ እንደተወለደች የምትናገረዉ ደራሲ ሙሉ ፤በሳዉዲ ስትኖር 12 ዓመታት እንዳስቆጠረች እና ፤ በቤተ ሰራተኝነት ተቀጥራ እያገለገለች መሆኑን ለሊት በተፈቀደላት አራት አምስት የመኝታ ሰዓት ሁለቱን ቀንሳ መጽሐፍ ደርሳ ለአንባብያን አቅርባለች። የመጽሐፉ ሽያጭ ደግሞ ለልብ ህሙማን ማዕከል፤ ለአዕምሮ ህሙማን ማዕከል እንዲሁም ሦስተኛዉ መጽሐፍ ደግሞ ለካንሰር ህሙማን ማዕከል ሙሉ ገቢዉን ሰጥታለች። 

ደራሲ ሙሉ ደርቤ
ደራሲ ሙሉ ደርቤ በሳዊዲ በቤት ሰራተኝነት እያገለገለች ኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦችዋን ስትረዳ አስራ ሁለት ዓመት አለፋትምስል Mulu Derebe/DW


ደራሲን ሙሉ ደርቤን ለማነጋገር ስንደዉል አሰሪዬ ካልጠራችኝ እሺ፤ ስትጠራኝ ግን ስልኩን ዘግቼ እሄዳለሁ ብላ ቃለ ምልልሳችን ጀመርን። ከዝያም ሙሉ ደርቤ ማናት አልናት።  ሙሉ ደርቤ በገጠር ተወልዳ ያደገች የገበሬ ልጅ ነች ስትል ታሪኳን ዘርዝራ ተረከችልን። የትምhreት ዉጤት ስላልመጣላት ስደትን የመጨረሻ አማራጭ አድርጋም ተነሳች። ጊ ለደላላ የምትከፍለዉን ገንዘብ የግንባታ ስራን ሰርታ አጠራቀመችና ተነሳችች።  


ከ 10 ዓመት ጀምሮ የጎርጎረሳዉያኑ ሐምሌ 30 ቀን ዓለም አቀፍ የፀረ ህገወጥ ሰዎች ዝዉዉር፤ የሚታሰብበት ቀን ሲል የመንግሥታቱ ድርጅት ደንግጎ እለቱ በተለያዩ አገሮች ይታሰባል። ደራሲ ሙሉ ደርቤ ደላላን በሰዉ በሰዉ አግኝታ፤ ከምትኖርበት ከራያዋ የገጠር ከተማ ሴንዉኃ ላይ ሆና በአፋር በኩል ደላላን አግኝታ በግንባታ ስራ ያጠራቀመቻትን ቋጥራ ለደላላ ከፍላ ሳዉዲ አረብያ ለመግባት ለቤተሰቦችዋ ሳትናገር ጉዞ ጀመረች። 

ደራሲ ሙሉ ደርቤ
ደራሲ ሙሉ ደርቤ በሳዊዲ በቤት ሰራተኝነት እያገለገለች ኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦችዋን ስትረዳ አስራ ሁለት ዓመት አለፋትምስል Mulu Derebe/DW


ከዛ ተሳክቶ ከቀናት እንግልት በኋላ የመን ድንበር ደረሰች። የመን ድንበር የተቀበላቸዉ ሕገወጥ ሰዉ አዘዋዋሪ፤ ወደ ሳዉዲ ለመሄድ ሌላ ገንዘብ አምጡ፤ ካላመጣችሁ አትሄዱም እያለ፤ ፍልሰተኞቹ ቤተሰቦቻቸዉን እየደወሉ ገንዘብ አስልከዉ፤ በየመን ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ሳዉዲአረብያ ድንበር ደረሱ። ሙሉ ሳዉዲ ድንበር ከመድረስዋ በፊት ያየችዉ የስደት ሰቆቃ ዛሬም ከአዕምሮዋ አልተፋቀም።  ግድያ የሰዉ መደፈር፤ ሰዉነትን ማጉደል የሰዉን አይን ማጥፋት ሁሉ ደላላዎቹ በግላጭ በሰዉ ላይ ግፍ ሲፈጽሙ አይታለች።   
ሙሉ ሳዉዲ ስትደርስ የመን ይዟቸዉ የነበረዉ ህገወጥ አዘዋዋሪደላላ ሳዉዲ ዉስጥ ለሚገኝ ሌላ ደላላ ሸጣቸዉ። የሚገርመዉ በሳዉዲ የሚገኘዉ ደላላ አማርኛ የሚናገር፤ ኢትዮጵያዊ ነዉ አበሻ ነዉ።  አበሻዉ ከየመኑ ደላላ ተቀብሎ ገዝቻችሁ ነዉ ብሎ በሳዉዲ አረብያም ከስደተኞቹ ገንዘብ አምጡ እያለ ይቀበላቸዉ ጀመር።   


ከራያ አፋር፤ ከአፍር፤ የመን፤ ከየመን ሳዉዲ አረብያ፤ የዛሬ 12 ዓመት ግድም ፤ብርድ ሃሩር ወበቁን አልፋ፤ የህገወጥ ሰዉ አዘዋዋሪዎችን ግፍ ሁሉ ተሻግራ፤ ዛሬ ፈጣሪ ከልሎች ደላሎች መንጋጋ ወጥቼ ሰዉ ቤት እየሰራሁ ነዉ ስትል ደራሲ ሙሉ ሰርቤ ነግራናለች። ሙሉ በዚህ ሁሉ መከራ መሃል ግን በቀን በቀን ሳልጽፍ የነጋበት ቀን በጣት የሚቆጠር ነዉ ስትልም አጫዉታናለች።

ደራሲ ሙሉ ደርቤ
ደራሲ ሙሉ ደርቤ በሳዊዲ በቤት ሰራተኝነት እያገለገለች ኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦችዋን ስትረዳ አስራ ሁለት ዓመት አለፋትምስል Mulu Derebe/DW

ደራሲ ሙሉ 2010 «ጣፋጭ ስደተኛ ስኖች» የሚል የግጥም መድብል በመለጠቅ ከጓደኛዋ ጋር «ከራስ ሽሽት» የሚሰኝ  ልብ ወለድ፤ በመለጠቅ በያዝነዉ 2016 ዓመት «ጣፋጭ ሲቃ» የሚሰኝ ልብወለድ መጽሐፍ ለአንባብያን አቅርባለች።  ደራሲ ሙሉ ደርቤ የሦስቱንም መጽሐፎችዋን  ሙሉ ገቢ ለልብ ህሙማን ህጻናት እና ካንሰር ታማሚዎች አስረክባለች።  
ሙሉ ደርቤ ለሰጠችን ቃለ ምልልስ በዶቼ ቬለ ስም በማመስገን ሙሉዉን ዝግጅት እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። 


አዜብ ታደሰ  

ሸዋዬ ለገሠ