1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደተኛዉ ማስታወሻ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 9 2012

ደራሲዉ በማስታወሻ የያዘዉ አባቱ የነገሩት ታሪክ በአብዛኛዉ ኢትዮጵያዉያን  እናት አባቶች፤ ያለፉበት በመሆኑ ማስታወሻዎቹን አሰባስቦ ማገር ወጋግራዉን ሰርቶለት በመጽሐፍ  መልክ እንዳቀረበዉ ይናገራል። የዋንቃ ጉዞ የሚለዉ ሁለተኛ መጽሐፉ ስያሜዉን ያገኘዉ በቀድሞ አጠራሩ በጌምድር ማለትም ጎንደር በሚገኘዉ የዓባይ ገባር ወንዝ በሆነዉ ዋናቃ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3fRur
Buchcover Tales from the Diary of the Ethiopian Diaspora
ምስል DW/E. Lisanu

«ሠላሳ በሦስት» የስደተኛዉ ማስታወሻ

 

« ሁሉ ነገር ተቀይሮአል፤ ሕንጻዉ ተቀይሮአል። ቢሆንም ሁሉ ነገር አለ። እኔ እንደዉም አዲስ አበባን ሳያት ሁሉ ነገር ያላት ግን ሁሉ ነገር ስርዓት የሌለበት ሆና ነዉ የታየችኝ። ይልቁኑ ትልቁና ዐብዩ ነገር በሞራል ተቋም በኩልያለ ያለማወቅ ነገር ፤ ለምሳሌ የራስን ታሪክም ያለመረዳት አብዝቶ ይታያል።»  

ከ 30 ዓመታት የስደት ኑሮ በኋላ ለሦስት ሳምንታት ሃገሩን ጉብኝት የጉዞ ማስታወሻዉን ሠላሳ በሦስት ሲል ሰሞኑን በመጽሐፍ መልክ ለአንባብያን ይፋ አድርጎአል። ደራሲና ጋዜጠኛ ኢሳያስ ልሳኑ። ሃገር በሰዎች ታሪክ ትገነባለች። እንደ ወንዝ በፈሰሱ ሰዎች መስዕዋትነትም ትጌጣለች ይላል ደራሲ ኢሳያስ ልሳኑ። የዓባይ ገባር የሆነዉን የዋንቃ ወንዝን ይዞ አባቱ የነገሩትን ታሪክ በመጽሐፍ መልክም ለአንባብያን አቅርቦ ተወዳጅነትን አግኝቶአል። የዋንቃ ጉዞ ይሰኛል መጽሐፉ። ደራሲ እና ጋዜጠኛ ኢሳያስ ልሳኑ  እንደነሚለዉ በማስታወሻ የያዘዉ አባቱ የነገሩት ታሪክ በአብዛኛዉ ኢትዮጵያዉያን  እናት አባቶች፤ አያቶች ቅድመ አያቶች ያለፉበት በመሆኑ ማስታወሻዎቹን አሰባስቦ ማገር ወጋግራዉን ሰርቶለት ነዉ በመጽሐፍ  መልክ ያቀረበዉ። ዋናቃ በቀድሞ አጠራሩ በጌምድር ማለትም ጎንደር  የሚገኝ የዓባይ ገባር ወንዝ መሆኑንም ነግሮናል።

ጋዜጠኛ ኢሳያስ ልሳኑ የዋንቃ ወንዝን ይዞ በብዕሩ የዋንቃ ጉዞን ከትቦ በሁለተኛነት ከሠላሳ ዓመታት በዩናይትድ ስቱትስ የስደት ኑሮ በኋላ ለሦስት ሳምንት እትብቱ የተቀበረበትን ሃገሩን ጎብኝቶ ከተመለሰ በኋላ «ሠላሳ በሦስት» ሲልም ለአንባብያን ያቀረበዉ መጽሐፍ ባለፈዉ ሰሞን ነዉ አንባብያን እጅ የገባዉ። ጋዜጠና ኢሳያስ ልሳኑ በአንድ ጊዜ ለአንባቢያን  ለገበያ ካቀረበዉና  መንትያ ካልነዉ መጽሐፍቶቹ የቱን ታበልጣለህ ለሚለዉ ጥያቄ ልጅን ከልጅ ማስበለጥ ባይቻልም ሰላሳ በሦስትን ታሪካዊ ሲል እንደሚያበልጠዉ አይሸሽግም። ሠላሳ በሦስት። ምን ይሆን?   

ሠላሳ በሦስት እዉነትም ታሪካዊ ይመስላል። ኢትዮጵያዉያን የዛሬ ሁለት ዓመት በስልጣን ላይ ለ ሃሰባት ዓመታት የነበረዉን በንግሥት በትግል እና በሰላም የስልጣን አዉርደዉ ለዉጥን ያዩበትን ጊዜ ይተርካል መጽሐፉ። ደራሲዉ ለዉጡን በቅርበት መዲና አዲስ አበባ ላይ ተገኝቶ፤ አይቶአል። ሠላሳ በሦስት ይህን የዓይን ምስክርነት ይዞ ፤ ለአንባብያን የቀረበበት ወቅት ደግሞ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፖለቲካዊ ዉጥንቅጥ ከመከሰቱ  ከሳምንታት በፊት ነበር። ይሁንና ደራሲዉ፤ በለዉጡ ሰሞን በሃገር ቤት የቃኘዉ የለዉጥ ጎርፍ ያለዉ ነገር የጠራ አለመሆኑ ምናልባትም ይህን ጊዜ ሊያመጣ እንደሚችል በምናቡ አይቶ በብዕሩ ከትቦታል። ከደራሲ እና ጋዜጠኛ ልሳኑ ጋር ያደረግነዉ ቃለ ምልልስ የተካተተበትን ሙሉ ጥንቅር  የድምጽ ማድመቻ ማዕቀፉን ተጭነዉ እንዲከታተሉ እናጋብዛለን።

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ