ስደተኞችና የባህር ጠረፏን ጥበቃ ያላረጋገጠችው ሊቢያ30 ሚያዝያ 2007ዓርብ፣ ሚያዝያ 30 2007ባለፉት አራት ወራት ብቻ ከ1,600 የሚበልጡ ስደተኞች ሜድትሬንያን ባህርን አቋርጠው ወደ አውሮጳ ለመግባት ሲሞክሩ ህይወታቸው አልፋለች። በአደገኛው የባህር ጉዞ የሚሞቱት ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ ከመጣ ወዲህ፣ የአውሮጳ ሀገራት መሪዎች ለዚሁ አሳሳቢ ውዝግብ መፍትሔ ፍለጋ ባለፈው ሳምንት ጉባዔ አካሂደዋል።https://p.dw.com/p/1FFlDምስል MAHMUD TURKIA/AFP/Getty Imagesማስታወቂያ 18394915በዚሁ ጉባዔ ላይ ለስደተኞቹ መርጃ ተጨማሪ ገንዘብ ለመመደብ እና በሕገ ወጦቹ ሰው አሸጋጋሪዎች አንጻር ርምጃ ለመውሰድ መስማማታቸው ይታወሳል። ይሁንና፣ ስደተኞቹ በብዛት የሚነሱባት ሊቢያ የባህር ጠረፏን እንኳን በሚገባ የመጠበቅ አቅሙ ተጓድሏት ትገኛለች። ሜሪሊን ዲውማ/ይልማ ኃይለሚካኤል አርያም ተክሌ ሸዋዬ ለገሠ