1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፖለቲካ ተንታኞች ስለ ሹም ሽሩ ምን ይላሉ?

ሐሙስ፣ ጥር 11 2015

«ከሦስት የመንግስት አውታሮች መካከል አንዱ የሆነው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው ሁለቱ ከፍተኛ አመራር በአንድ ጊዜ መነሳታቸው ፖለቲካችን ያለበት ሁኔታ ጥሩ እንዳልሆነ የማሳያ ምልክት ነው።»

https://p.dw.com/p/4MRqm
Äthiopien - Federal Supreme Court Meaza Ashenafi  Solomon Areda
ምስል Seyoum Getu/DW

«ጥሩ እንዳልሆነ የማሳያ ምልክት ነው»

ላለፉት አራት ዓመታት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ እና ምክትላቸው አቶ ሰለሞን አረዳና አራት የተለያዩ ሚኒስትሮች ከስልጣናቸው ተነስተዋል  የሚኒስቴሮቹ መነሳት በአገር ላይ እንዲሁም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል ምን ጉዳትስ አለው  ይህ ሹም ሽረት የምንስ ማሳያ ነው ስንል ለሶስት የፖለቲካ ተንታኞችን ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር።

መጀመሪያ  አስተያየታቸውን የሰጡን የፖለቲካ ሳይንስ አስተማሪ የሆኑት ዶክተር ደጉ አስረስ  «ብልፅግና ፓርቲ በተለያየ ግዜ አላማዬን ለመፈፀም ይመቹኛል ያላቸውን ሰዎች ማቀያየር መዘዋወር ይችላል ። የመንግስት አፈፃፀም ደከም በሚልበት ወቅት አይደለም ሚኒስቴር  ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከነካቢኔው ይለቃል » ሲሉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትን እና ምክትል ፕሬዚዳንቱን በተመለከተ ሲገልፁ « ህግ አስፈፃሚው  አካላት እራሳቸውን ችለው የሚሰሩ ናቸው ብሎ ነው ህገመንግስቱ ያስቀመጠው። እራሳቸው መልቀቂያ አቀረቡ ነው የተባለው ይህ ምን አልባት አገራችን ባለችበት የፍትህ ስርአት እንደተፈለገው እየሄደ አለመሆኑን ማሳያ ነው ። ሚኒስቴሮች መቀያየራቸውን ግን ህገ መንግስቱም ይፈቅድላቸዋል» ብለዋል

የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እንዲሁም የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አቶ አብዱራህማን አህመዲን የወይዘሮ መዓዛ እና ምክትላቸው በአንድነት መልቀቅ  ጥሩ ምልክት አይደለም ሲሉ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል «ሶስት የመንግስት አውታሮች  መካከል አንዱ የሆነው  የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው  ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች  በአንድ ግዜ መነሳታቸው የፖለቲካችን ጥሩ ምልክት አይደለም ምን አልባት ግፊቶች ይኖርባቸው ይሆን  የሚል ሀሳብ አለኝ»

የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ተስፋዬ ከበደ  በበኩላቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራቱን ሚኒስቴሮች በክብር ከሸኘ በኋላ እካሁን ሌሎች የልሾመበት ምክንያት ግልፅ አይደለም ሲሉ ገልፀዋል «የፌደሬሽን ምክር ቤት አራት  ሚኒስቴሮቹን ማንሳቱን ከገለፀ በውኃላ  የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት እና ምክትላቸው ላይ ሹም ሽረት አድርገዋል ለምን ግን ያቦታ ክፍት እንዲሆን ለምን  እንደተፈለገ ግልፅ  አይደለም» ብለዋል ወይዘሮ መዓዛ ደግሞ ከባድ ጊዜ ነው ያሳለፉት የፍርድ ቤቶች ትእዛዝ በፖሊሶች የማይከበሩበት ግዜ አለ አዲስ የሚመዙት ሰዎች ከሳቸው የተሻለስራ ይሰራሉ የሚለው ነው ለኔ ወሳኙ ጥያቄ»  ብለዋል

ማኅሌት ፋሲል

ኂሩት መለሰ