1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኮሮና ስርጭት አብቅቶለታል አሉ

ሰኞ፣ መስከረም 9 2015

በዩናይትድ ስቴትስ የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት አብቅቷል ሲሉ ፕሬዚዳንት ጆ ቢደን ተናገሩ። ጆ ባይደን በአሜሪካ ምንም እንኳ አሁንም ከኮሮና ጋር በተያያዘ ችግሮች ቢኖሩም ወረርሽኙ ስርጭቱአብቅቷል ብለዋል። በአሜሪካ ሰዎች የኮሮና ተሐዋሲን ለመከላከል የሚጠለቀዉ የአፍ መሸፈኛ ጭንብልን ማድረግ አቁመዋል ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4H4d4
USA Washington | Joe Biden
ምስል Jim LoScalzo/ZUMA Wire/IMAGO

በዩናይትድ ስቴትስ የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት አብቅቷል ሲሉ ፕሬዚዳንት ጆ ቢደን ተናገሩ። ባይደን ከ«ሲ ቢ ኤስ»  የቴሌቭዥን ጣብያ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፤ እንደገለፁት በሀገራቸዉ በዩናይትድ ስቴትስ ምንም እንኳ ከኮሮና ጋር በተያያዘ አሁንም ችግሮች ቢኖሩም ወረርሽኙ ስርጭቱን አብቅቷል ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዩናይትድ ስቴትስ በሚወጡ ዘገቦች መሰረት፤ በአሜሪካ ሰዎች የኮሮና ተሐዋሲን ለመከላከል የሚጠለቀዉ የአፍ መሸፈኛ ጭንብልን ማድረግ አቁመዋል፤ ሰዎች ለወረርሽኙ ያላቸዉ ስጋት ጠፍቶ ጥሩ ስሜት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።  ይሁንና ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአሜሪካን አስተዳደር በቀጣይ እየገባ ባለዉ የበልግ ወራት የኮሮና ተሐዋሲ ወረርሽኝ ሊከሰት የሚችል ከሆነ ወረርሽኙን ለመከላከል ለምርመራና ለክትባት አቅርቦት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲሰጠው ምክር ቤቱን ጠይቆ እንደነበር የሚታወስ ነዉ።

 

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሰ