1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ በቀለ ለሐምሌ 20፣አቶ ጃዋር ደግሞ ለሐምሌ 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።

ሐሙስ፣ ሐምሌ 9 2012

ዛሬ ያስቻለው ፍርድ ቤቱ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የፈቀደው ፖሊስ እስካሁን በምርመራ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ በማሳወቅ ከወንጀሉ ውስብስብነት አንጻር ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ነው።የአቶ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ኢብሳ ገመዳ ክሱን ተቃውመው ለችሎቱ  መከራከሪያ ማቅረባቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3fRRK
Symbolbild Justiz Gericht Richterhammer
ምስል picture alliance/imageBROKER

አቶ በቀለ ለሐምሌ 20፣አቶ ጃዋር ደግሞ ለሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ የቀጠሮ ችሎት ፖሊስ በአቶ ጀዋር መሐመድ ጉዳይ ላይ የጠየቀውን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።ዛሬ ያስቻለው ፍርድ ቤቱ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የፈቀደው ፖሊስ እስካሁን በምርመራ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ በማሳወቅ ከወንጀሉ ውስብስብነት አንጻር ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ነው።ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት የአቶ ሃጫሉ ሁንዴሳን አስከሬን አቶ ጃዋር መሐመድ  ወደ ኦሮምያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ባመጡበት ወቅት ከጠባቂዎቻቸው በተተኮሰ ጥይት በአንድ የኦሮምያ ፖሊስ ህይወት ማለፍ ወንጀል እንደጠረጠራቸው ገልጿል።ከዚህ ሌላ ርሳቸው በሚመሩት OMN  በተባለው ቴሌቪዥን በተለላለፈ የሁከት እና የአመፅ ጥሪ በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን አካልም መጉደሉንና ንብረትም መውደሙን በሪፖርቱ አስታውቋል። የአቶ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ኢብሳ ገመዳ ክሱን ተቃውመው ለችሎቱ  መከራከሪያ ማቅረባቸውን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።አቶ ኢብሳ አቶ ጀዋር ከታሰሩ በኋላ በተፈጸሙ ጉዳዮች መከሰሳቸው ተገቢ እንዳልሆነ ፍርድ ቤቱን መሞገታቸውን ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በ3 መዝገቦች የተጠረጠሩ 17 ሰዎች ጉዳይ ላይ ፖሊስ የምርመራ ቀጠሮ  እንዲሰጠው ባቀረበው ጥያቄ ላይም ከ11 እስከ 12 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።በዚሁ መሠረት ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ በቀለ ገርባን ጉዳይ ሐምሌ 20 እንዲሁም የእነ አቶ ጀዋር መሐመድን ጉዳይ  ሐምሉ 22 ለማየት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ