1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈረንሳይ ውስጥ የተቀጣጠለው ተቃውሞ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 1 2012

በትናንትናው ዕለት በፓሪስ ጎዳናዎች በርካቶች ለተቃውሞ የወጡ ሲሆን የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎቶች የሥራ ማቆም አድማው ያነጣጠረባቸው እንደሆነ እና ይህም ለሳምንታት ይቀጥላል የሚል ስጋት መኖሩን ዘገባዎች ያመለክታሉ። 

https://p.dw.com/p/3UdY7
Frankreich l Streiks und Protest gegen die geplante Rentenreform
ምስል Reuters/J. Pelissier

«አዲሱ የጡረታ ሕግ ተቃውሞ ገጥሞታል»

በፈረንሳይ አዲሱን የጡረታ ሕግ በመቃወም የሚደረገዉ አድማ ቀጥሏል። የፕሬዝደንት ኢማኑዌል ማክሮ መንግሥት በመላው ሀገሪቱ የሥራ ማቆም አድማ እና ተቃውሞ የቀሰቀሰውን የዚህን ሕግ ይዘት ለማስረዳት  እየጣረ ነው። በትናንትናው ዕለት በፓሪስ ጎዳናዎች በርካቶች ለተቃውሞ የወጡ ሲሆን የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎቶች የሥራ ማቆም አድማው ያነጣጠረባቸው እንደሆነ እና ይህም ለሳምንታት ይቀጥላል የሚል ስጋት መኖሩን ዘገባዎች ያመለክታሉ።  አዲሱ የጡረታ ሕግ ከጎርጎሪዮሳዊው 1975 ዓ,ም ወዲህ የተወለዱ እስከ 64 ዓመት ከሠሩ ብቻ ሙሉ የጡረታ ገንዘብ ሊያገኙ እንደሚችሉ ሲያመለክት፤ ከዚያ በፊት ያሉት በ62 ዓመታቸው ይህን ደረጃ እንደሚያገኙ መግለፁ በሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሷል። የፓሪሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዘገባ ልካልናለች። 

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ