1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጦርነትና ድርድር እንዴት

እሑድ፣ ኅዳር 6 2013

ኢትዮጵያ ዳግም ተመልሳ ስለጦርነት የሚወራባት ሀገር ከሆነች ከሳምንት በላይ ቀናት ተቆጠሩ። ፌደራል መንግሥት ወደ ጦርነት የገባው በሰሜን ዕዝ የሀገር ዳር ድንበር ሊያስከብር የተሠማራው ጦር  በትግራይ ክልል ኃይል ጥቃት ስለተፈጸመበት መሆኑን ይፋ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/3lKVw
Karte - Äthiopien, Tigray - EN

ጦርነትና ድርድር እንዴት

ኢትዮጵያ ዳግም ተመልሳ ስለጦርነት የሚወራባት ሀገር ከሆነች ከሳምንት በላይ ቀናት ተቆጠሩ። ፌደራል መንግሥት ወደ ጦርነት የገባው በሰሜን ዕዝ የሀገር ዳር ድንበር ሊያስከብር የተሠማራው ጦር  በትግራይ ክልል ኃይል ጥቃት ስለተፈጸመበት መሆኑን ይፋ አድርጓል። ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብም በአጭር ጊዜ ጦርነቱ እንደሚቋጭ አመልክቷል። የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ ፌደራሉ መንግሥት ጥቃት ከፈተብኝ በሚል ይከሳል። ጦርነቱ መንግሥት እንደሚለው ወንጀል በፈጸመ በአንድ ቡድን ላይ ያነጣጠረ ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ መንግሥት በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል የሚሉም አሉ። በዚህ መሀልስ ድርድር እንዴት ይታሰባል? ሙሉውን ውይይት ከድምጽ ማዕቀፉ ያድምጡ።

 

ሸዋዬ ለገሠ