1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥምቀትን በጎንደር 

ማክሰኞ፣ ጥር 11 2013

ጥምቀት በጎንደር ከተማ በድምቀት ተከብሯል። የከተማ አስተዳደሩ በርካታ የመከላከያ ቁሰቀቁሶችን ቢያቀርብም ኅብረተሰቡ አሁንም ለኮሮና የሰጠው ትኩረት አናሳ ነው ተብሏል። 400 ሺህ የፊት ጭምብል ቢከፋፈልም ኅብረተሰቡ ግን እምብዛም ሲጠቀምበት አልተስተዋለም።

https://p.dw.com/p/3o8Ya
BdTD Äthiopien Timkat Parade
ምስል Eduardo Soteras/AFP/Getty Images

ኅብረተሰቡ ለኮሮና የሰጠው ትኩረት አናሳ ነው

ጥምቀት በጎንደር ከተማ በድምቀት ተከብሯል። የከተማ አስተዳደሩ በርካታ የመከላከያ ቁሰቀቁሶችን ቢያቀርብም ኅብረተሰቡ አሁንም ለኮሮና የሰጠው ትኩረት አናሳ ነው ተብሏል። 400 ሺህ የፊት ጭምብል ቢከፋፈልም ኅብረተሰቡ ግን እምብዛም ሲጠቀምበት አልተስተዋለም። 

የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በደመቀና በተለየ ሁኔታ ከሚከበርባቸው ከተሞች መካከል የጎንደር ከተማ እንዱ ነው፡፡ በዓሉ ዘንድሮም በርካታ ምዕመናን በተገኙበት መከበሩን የከተማ አስተዳደሩና ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

ለመሆኑ የጥምቀትን በዓል በጎንደር ከተማ ልዩ የሚያደርገው ምንድነው ስንል አቶ ባዩ በዛብህ የተባሉ የከተማዋና ነዋሪ ጠይቀናል፡፡ ጥምቀትን በጎንደር የተሳካና ማራኪ ለማድረግ ከተሰሩ ሥራዎች መካከል አንዳንዶቹን የከተማ አስተዳደሩ የባህል እሴቶችና እንዱስትሪ ልማት ቡድን መሪ አቶ ልዕልና ገብረ መስቀል ያስረዳሉ፡፡

ኅብረተሰቡ ኮሮናን እየተከላከለ በዓሉን በሰላም እንዲውል በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን የከተማ አስተዳደሩ የጤና መምሬ ኃላፊ አቶ ገበያው አሻግሬ ተናግረዋል፣ በዚህም ከ400 ሺህ በላይ ማሰከ፣ 5 ሺህ የእጅ ንፅህና መጠበቂያ አልኮል ኅብረተሰቡን ከመጠጋጋት ለመጠበቅ 4 ታላላቅ የቴሌቪዥን ሰክሪኖች እንዲሁም 4 የፀበል መርጫ ፓምፖች ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡

 Äthiopien | Lonely Planet | Reiseziele für 2021
ምስል Karsten Wrobel/imageBROKER/picture alliance

ይሁን እንጂ ምዕመናን እንደሚሉት ኅብረተሰቡ ማስክ የመጠቀም ልምዱ የለም፣ በጥምቀቱም እጅግ ቁጥራቸው ያነሱ ሰዎች ናቸው ማሰክ አድርገው የሚታዩት፡፡ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኚኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ቻላቸው ዳኛው እንዳሉት ኅብረተሰቡ ሰለበሽታው አስከፊነት ቢነገረውም አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ አመልክተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ገበያው አሻግሬም በጥምቀት ላይ የታየው መዘናጋት ብዙ ያልተሰራ ሥራ አመላካች ነው ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ በተከበረው የጥምቀት በዓል ላይ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ እንደታዘበው ኅብረተሰቡ ስለ በሽታው የሰማ በማይመስል መንገድ ምዕመኑ የኮሮና መከላከያ ጭምብል አላደረገም፡፡

ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ