1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ

ሰኞ፣ ኅዳር 3 2011

የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አመራሮችና አባላት ፣በሽብር ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎችን በሕግ በማይታወቁ በአገሪቱ የተለያዩ ስዉር እስርቤቶች ያስሩ እንደነበረ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ዛሬ በፅህፈት ቤታቸዉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/387f7
Logo FDRE Federal Attorney Äthiopien

«እስረኛ ወንድን ግብረሰዶም፤ ሴቶችን ይደፍሩ ነበር»

የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አመራሮችና አባላት ፣በሽብር ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎችን በሕግ በማይታወቁ በአገሪቱ የተለያዩ ስዉር እስርቤቶች ያስሩ እንደነበረ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ዛሬ በፅህፈት ቤታቸዉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ። በአዲስ አበባ ብቻ ከሰባት በላይ ስዉር እስር ቤቶች እንደሚገኙም በምሳሌኔት ጠቅሰዋል። ተጠርጣሪዎቹን ብዙ ግዜ በአምቡላንስ እንደሚያጓጉዟቸዉ ከተያዙ በኋላ አይናቸዉን በመሸፈን ለረዥም ጊዜ እንዲቆዩ  እንደሚደረግም ተናግረዋል። እስካሁን በአጠቃላይ 63 ሰዎች በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል።  በሌላ በኩል የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ያለ ህጋዊ የጨረታ ሂደት የ37 ቢሊየን ብር የውጭ ሃገር ግዢ መፈጸሙን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለፆአል። ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መካከል እንዲሁም በደላላዎች የተከናወኑ ናቸው። ዝርዝሩን ቦታዉ ላይ የተከታተለዉ የአዲስ አበባዉ ኪላችን ልኮልናል። 

Äthiopien verhaftet 63 wegen Verdachts auf Menschenrechtsverletzungen, Korruption. Der Generalstaatsanwalt Berhanu Tsegaye sagte heute (03.11.2018) lokalen Journalisten, dass die Inhaftierung nach fünf Monaten Ermittlungen erfolgt.
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሃመድ