1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የዓለም የሰላም ኖቤል አሸነፉ

ዓርብ፣ መስከረም 30 2012

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የዘንድሮውን የዓለም የሰላም ኖቤል አሸነፉ። ጠ/ሚ ዐቢይ ለዚህ የበቁት በዋናነት ሃያ ዓመታት በዘለቀው የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ውዝግብ ሰላም እንዲወርድ ላበረከቱት አስተዋጽኦ መኾኑ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/3R7r6
Friedensnobelpreis 2019 Äthiopien | Ministerpräsident Abiy Ahmed
ምስል Getty Images/AFP/E. Soteras

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የዘንድሮውን የዓለም የሰላም ኖቤል አሸነፉ። ጠ/ሚ ዐቢይ ለዚህ የበቁት በዋናነት ሃያ ዓመታት በዘለቀው የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ውዝግብ ሰላም እንዲወርድ ላበረከቱት አስተዋጽኦ መኾኑ ተገልጿል። ምሥራቅ አፍሪቃን በዲፕሎማሲ ለማስተሳሰር ጥረት ማድረጋቸውም ተጠቅሷል። በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉን ከተቃዋሚዎች ጋር ማስማማታቸውም ሽልማቱን እንዲያሸንፉ ረድቷቸዋል ነው የተባለው። ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን ከእስር መልቀቃቸው፤ በስደት የነበሩ የተቃዋሚ ኃይሎች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ማድረጋቸውም ተጠቅሷል። አብይ አህመድ 100ኛው የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሲሆኑ 900,000 የአሜሪካን ዶላርም ይበረከትላቸዋል።

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ