ግዕዝ በኮንፒዉተር ያስተዋወቁት ኢትዮጵያዊ
ሐሙስ፣ መጋቢት 10 2012ማስታወቂያ
በዩናትድ ስቴትስ ኮለራዶ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያዊዉ ሳይንቲስት ዶ/ር ኣበራ ሞላ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ መናገሻ ኣውራጃ፣ ሰንዳፋ ከተማ መወለዳቸዉን ሲናገሩ በደስታ ነዉ። በሰሜን አሜሪካ ሲኖሩ ከአራት አስርተ ዓመታት በላይ የሆነቻቸዉ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ኮምፕዩተሮችና የእጅ ስልኮች በግዕዝ ፊደል እንዲጽፉ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ናቸው። ዶ/ር አበራ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን የተከታተሉት የእንስሳ ሕክምናን ሞያ ነዉ። የግዕዝ ፊደልንና ሥነ ጽሑፍ በኮምፕዩተርና በእጅ ስልክ ውስጥ መጠቀም እንዲቻል አድርገዋል። ዶ/ር አበራ እንደነገሩን በምርምር ባገኝዋቸዉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ሰባት የዩናይትድ እስቴትስና ኢትዮጵያ ፓተንቶች ብቻቸውን ይዘዋል። የአክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ብዙ ትግል ያደረጉ መሆናቸዉን ተዘግቦአል። በእዚህ ቅንብር ዶ/ር ኣበራ ሞላን በቅድምያ ግዕዝን በኮምፒዉተር መተየብ ስለሚያስችል ፈጠራ ዉጤታቸዉ ጠይቀናቸዋል።
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ