1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግንቦት 20 ፣ ዘንድሮ በአማራ ክልል

ዓርብ፣ ግንቦት 20 2013

የእስከዚያ ቀኑ አማፂ ቡድን ኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥልጣን የያዘበት ዕለት ነዉ።ዕለቱ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥና በየሐገራቱ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች  ለተከታታይ ዓመታት በደማቅ ሥርዓት ተከብሯል

https://p.dw.com/p/3u7XF
Äthiopien vor der Wahl EPRDF Anhänger in Addis Abeba
ምስል Getty Images/AFP/Z. Abubeker

ግንቦት 20 «በዓል መሆኑን የሚያዉቁ ጥቂት ናቸዉ»

ዛሬ ግንቦት 20 ነዉ።የዛሬ ሰላሳ ዓመት ግንቦት 1983 ሶሻሊስታዊዉን ርዕዮተ-ዓለም የሚከተለዉ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ (የደርግ) መንግስት በጠመንጃ ዉጊያ ከስልጣን የተወገደበት፣ የእስከዚያ ቀኑ አማፂ ቡድን ኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥልጣን የያዘበት ዕለት ነዉ።ዕለቱ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥና በየሐገራቱ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች  ለተከታታይ ዓመታት በደማቅ ሥርዓት ተከብሯል።አሁንም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ በዓል ነዉ።ይሁንና ወትሮ የነበረዉ የአደባባይ ሰልፍ፣ድግስ፣ትርዒት በአብዛኛዉ አካባቢ የለም።በአማራ ክልል በሶስት ከተሞች የሚኖሩ እንዳሉት ደግሞ ዕለቱ በዓል መሆኑን የሚያዉቁም ጥቂት ናቸዉ።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ