1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዜጠኞች እና ስነ ምግባራቸው

ቅዳሜ፣ ኅዳር 15 2011

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ትናንት በጠራው ባዘጋጀው መድረክ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጋዜጠኝነት ኹኔታን የሚዳስሱ 5 ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡ በውይይቱ ከባሕረዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ከሌሎች ተቋማትና የተጋበዙ እንግዶችና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

https://p.dw.com/p/38rGT
Die äthiopischen Medien in einem Zustand des Wandels
ምስል DW/A. Mekonneni

ለውጥ ቢታይም ከቆየው አሠራር መላቀቅ አልተቻለም

ባለፉት 8 ወራት የታዩ መልካም ጅምሮች ጋዜጠኛው በነፃነት እንዲሠራ መንገድ የከፈቱ መሆናቸውን ጥናቶች አመልክተዋል፣ ሆኖም ከቆየው አሰራር ያልተለወጡ አካሄዶችም እንዳሉ ምሁራኑ በጥናታቸው ጠቁመዋል፡፡ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ባዘጋጀው ጥናታዊ ውይይት ላይ ምሁራን የጥናት ጽሑፋቸውን አቅርበዋል።

ዶ/ር ሙላቱ ዓለማየሁ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ራዲዮ ጋዘየጠኛ ነበሩ አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን የትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት ባለፉት 8 ወራት በሚዲያው ዘርፍ መልካም ጅምሮች ታይተዋል፡፡

ሌላው ጥናት አቅራቢ ዶ/ር ጀማል ሙሃመድ ናቸው አሳቸውም ቢሆን በአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ለበርካታ ዓመታት በጋዜጠኝነትና በኃላፊነት ሠርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን መምህር ናቸው፡፡

ለውጡ ባለፉት ጥቂት ወራት መልካም ጅምሮች የታዩበት ቢሆንም ከቀድሞው አሠራር ያልተላቀቁ ሚዲያዎችና ባለሞያዎች መኖራቸውን አብነቶችን በመጥቀስ ይናገራሉ፡፡

የታየው መልካም ጭላንጭል ቀጣይነት እንዲኖረው ጋዜጠኛው በሙያ ተደራጅቶ የሞያ ነፃነቱን ማስከበርና ለማንም ሳይወገወን ለእውነት እንዲሠራ ዶ/ር ሙላቱ ተናግረዋል።

ዶ/ር ጀማል እንደሚሉት ደግሞ የተገኘውን መልካም አጋጣሚ ጋዜጠኛውም ሆነ መንግስት ሊጠቀምበት ይገባል፡ ሁሉንም ህብረተሰብ በእኩልነት ሊያገለግል የሚገባ የመገናኛ አውታር ለመገንባት የሁሉም ጥረት ያስፈጋል፡፡

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ትናንት በጠራው ባዘጋጀው በዚሁ መድረክ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጋዜጠኝነት ሁኔታን የሚዳስሱ 5 ጽሁፎች ቀርበዋል፡፡ በውይይቱ ከባሕረዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ከሌሎች ተቋማትና የተጋበዙ እንግዶችና ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ